ሰሞኑንን አምነስቲ ይፋ ያደረገው ሪፖርት መንግስት ምላሽ ለመስጠት በቀረቡለት ጥያቄዎች መሰረት ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑ ተመለከተ። የመንግስትን ምላሽ ሳያካትትና በመላው አገሪቱ በዜጎች ላይ የደረሰውን ግፍ፣ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ አፈና እንዲሁም ዝርፊያ ያላከተተበት ምክንያት አነጋጋሪ ሆኗል።

ሪፖርቱ ኦነግ ሸኔ በሚል ስያሜ በውል በማይታወቅ ጥያቄ ጠብ መንጃ አንስቶ ጫካ የገባው ድርጅት የፈጸማቸውን ኢሰብአዊ ድርጊቶች አለማካተቱ የሪፖርቱን ሚዛናዊነትና ልዩ ፍላጎት ዜጎች እንዲመረምሩት እድል ከፍቷል።

በአማራ፣ በሶማሌ፣ በቤኒሻንጉል፣ በወለጋ፣ በሞያሌ፣ በሻሸመኒ፣ ሃዋሳና አካባቢው፣ በኦሮሚያ በጉጂና በጊዲዖ እንዲሁም በድሬደዋ አስተዳደር ማን እንዳደራጃቸው በውል በሚታወቁ ሃይሎች የደረሰውን አስከፊ ጭፍጨፋና ግፍ ያካትት ዘንድ ዜጎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ይህ በንዲህ እያለ ነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት የማጣራት ስራ መጀመሩን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የገለጹት።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ሰሞኑን አመነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ላይ ይዞ በወጣው ሪፖርት ዙሪያ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “ሰበዓዊ መብት የምናከብረውና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችንና ለፍትህ ስንል ነው” ብለዋል።

“በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣውን መግለጫ ተመልክተነዋል” ያሉት ወይዘሮ አዳነች፥ ሪፖርቱን የማጣራት ስራ መጀመሩንም አስታውቀዋል።

“የማጣራት ስራችንን አጠናቀን ምላሽ ለመስጠት በሂደት እያለን መግለጫው በተለያዩ ሚዲያ ተሰራጭቷል” ሲሉም ጠቅሰዋል።

“አሁንም ቢሆን ዘገባውን ከይዘቱ፣ ከአካሄዱ፣ እንዲሁም የጉዳዩን እውነተኛነት እና ገለልተኛነት የማጣራት ስራችንን በቶሎ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

“በማጣራት ስራችን በሚገኘውም ውጤት፣ ሪፖርቱ እውነት በሆነበት ልክ፣ መወሰድ ያለበቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን” ብለዋል ወይዘሮ አዳነች በመልእክታቸው።

ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል ለማድረግ እንደሚጥሩ በመግለፅ፤ “ይህ ባይቻል እንኳን ህዝቡ እና አለም ዓአፉ ማህበረሰብ እውነቱን እንዲያውቀው በመረጃ አስደግፈን እናሳያለን” ሲሉም አስታውቀዋል።

#FBC

Related stories   Justice minister Sylvi Listhaug removes Facebook post after scandal

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *