እያደር እየተካረረ የመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከጀርባው ያዘለው ጉድ ከሃሜት ወደ ቀጥተኛና ተቋማዊ ግጥሚያ እየተሸጋገረ ነው። ለዚህም ይመስላል ሶስቱ ኢትዮጵያን ሊውጡ የተነሱ ናቸው የተባሉ ሃይሎች በገሃድ ለህዝብ ይፋ ሆነዋል። ጉዳዩም ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ከግብጽ እገዛ የሚደረግላቸውና ማስረጃ የተያዘባቸው፣ ወያኔና በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሆናቸውን ስም ጠቅሰው ይፋ ያደረጉት አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው። በምክትል ፕሬዚዳንትነት ማዕረግ የማህበራት ዘርፍ አስተባባሪው እንዳሉት የሁሉም ጉዳይ መረጃ በመንግስት እጅ ይገኛል።

ከመስከረም 30 በሁዋላ መንግስት እንደሌለ በይፋ የሚገልጹት ውስን የኦሮሚያ ክልል ተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች ሕዝብን ለሰላማዊ ስልፍ ማነሳሳታቸው፣ የተደነገገውን የአስቸኳይ አዋጅ መተላለፍ መሆኑም፣ ይህንን ጉዳይ አደብ ለማስያዝ መንግስት ሙሉ አቅሙን ወደ መጠቀም እንደሚዛወር፣ ይህ ከመሆኑ በፊት ዜጎች የሚቀርብላቸውን ሁሉ ዝም ብለው ከመቀበል እንዲቆጠቡ ነው ጥሪው የተላለፈው።

የኮቪድ ወረርሺኝ በሚያስደንቅ ፍጥነት እየቀጠፈ ባለበትና ሰፊ ቁጥር ያለው ሕዝብ ይጠቃል የሚል ፍርሃት ባለበት በአሁን ሰዓት ውስን ሃይሎች ኦሮሚያን ለማተራመስ፣ ኦሮሚያን ለማናጋት እየሰሩ መሆኑንን ሕዝብ እንዲገነዘብ አቶ አዲሱ ሲያሳስቡ ክልሉ ሲተራመስ የሚከተለውን መዘዝ አላብራሩም።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

በኦሮሚያ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፓርቲ የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ ጃዋር መሃመድና ኦነግ ሸኔን የሚደጉሙ መኖራቸውን የሚረዱ ሁሉም ወገኖች መስከንና ይህን ክፉ ወቅት ለመሻገር ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ያሳስባሉ።

ጃዋርንም ሆን የጃዋርን ቡድን የማይቀበሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች በርካታ መሆናቸውን፣ ” ዲቃላ ” በሚል የተፈረጀው የኦሮሞ ህዝብና ከተሞች አሁን ካለው መንግስት ጋር መሆንን ስለሚመርጡ ወደ እርስ በርስ ግጭት የማምራት አዝማሚያ እንዳይከሰት በግፊትና በሴራ የተጠለፉ ፖለቲከኞች እንዲያስቡበት ውስጥ አዋቂዎች ደጋግመው እየመከሩ ነው። አቶ አዲሱን ጠቅሶ ፋና የሚከተለውን ዘግቧል

ሕዝቡ የተጠራው ሰልፍ ለኮሮናቫይረስ እንደሚያጋልጠው አውቆ ቅድሚያ ለጤንነቱ ሊሰጥ ይገባል- የኦሮሚያ ክልል መንግስት

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሕዝቡ በአንዳንድ ሃይሎች እየተጠራ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ ለኮሮናቫይረስ እንደሚያጋልጠው አውቆ ቅድሚያ ለጤንነቱ ሊሰጥና ጥያቄውን በትክክለኛ መንገድ ሊያቀርብ እንደሚገባ አሳስቧል።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

የክልሉ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምንት የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ቦታዎችን ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኮሮናቫይረስ መከላከልና ሰሞኑን በክልሉ በተለያዩ አካላት እየተጠሩ ያሉ ሰላማዊ ሰልፎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫውን የሰጡት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ”ሕዝቡ ከአገር ጥቅም በተቃራኒ ከቆሙት አካላት ሊጠነቀቅ ይገባል” ብለዋል።የተቃውሞ ሰልፉን እያስተባበሩ ያሉ ቡድኖች ሕዝቡን ተጠቅመው የራሳቸውን የስልጣን ፍላጎት ለማሟላት እየተንቀሳቀሱ ያሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።“ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዱ በግብጽ የሚደገፍ ሲሆን ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳጣት የሚንቀሳቀስ ነው” ብለዋል።

አቶ አዲሱ ሁለተኛውን ቡድን ‘ወያኔ’ በማለት የገለጹት ሲሆን ”ይህ ቡድን ከዚህ በፊት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያሰቃይና ሲበዘብዝ የቆየ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።ይኸው ቡድን የለመደው ጥቅም ስለቀረበት ‘ስልጣን ይዞ ያለውን መንግስት ለማዳከም በተለያየ መንገድ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።“ሶስተኛው ቡድን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ መራዘሙን መነሻ ምክንያት በማድረግ በአቋራጭ ስልጣን የሚፈልጉ አካላት ናቸው” ብለዋል።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

በመሆኑም ሕዝቡ እየተጠራ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ እነዚህ ሶስት ቡድኖች ተሰባስበው የጠሩት መሆኑን አውቆ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።”የክልሉ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄ ካለው በትክክለኛው መንገድ ያቅርብ” ያሉት አቶ አዲሱ፤ ከዚህ ውጪ ባሉት ጉዳዮች ላይ መንግስት ሕግን ለማስከበር ‘አቅሙም፤ ችሎታውም’ አለው ብለዋል።በክልሉ እስካሁን የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የተሰራውን ስራ በተመለከተም በመግለጫቸው አካተዋል።በዚህ ረገድ እስካሁን በክልሉ ሰፋ ያሉ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎች ቢከናወኑም የሚፈለገውን ያህል የባህሪ ለውጥ እንዳልመጣ ጠቁመዋል።

አሁንም የገበያ ቦታዎች፣ ሰርግ መሰረግ፣ ለቅሶ ማከናወንና በትራንስፖርት አጠቃቀም በኩል አሳሳቢ ሁኔታ እየተስተዋለ እንደሆነ ተናግረዋል።ሆኖም የክልሉ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው የተገኙ 3 ሺህ 700 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ተገቢውን ቅጣት ማሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *