በጤና ተቋማት የሚሰሩ 65 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስትሯ አስታወቁ። በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት 49 የጤና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ያስታወቁት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ናቸው።

ባለሙያዎቹ በአብዛኛው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት እየሰሩ የነበሩ መሆናቸውን ሲሆን፣ የጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት ሠራተኞች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እያደረጉት ላለው ተጋድሎም ምስጋና አቅርበዋል።

Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

መንግሥት የጤና ተቋማት ሠራተኞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከሚያደርገው ሥራ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ራሱን በመጠበቅ የባለሙያዎቹን ጫና እንዲቀንስም ጠይቀዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለይ ማህበረሰቡ የቫይረሱን ስርጭት የሚመጥን ጥንቃቄ አለመደረጉ እንደሚያሳስባቸው ሚኒስትሯ ተናግረዋል።”ጥንቃቄ የምናደርገው የጸጥታ አካላት ወይም የጤና ባለሙያዎችን ትዕዛዝ ለማክበር ሳይሆን፤ ለራሳችንና ለምንወዳቸው ወገኖቻችን ብለን መሆን አለበት” ሲሉም ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *