120,429 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 1.486 ሰዎች ተጠቅተዋል፤ ሟቾች 17 ደርሰዋል፤ 120 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የተመርማሪዎችን ቁጥር ብትጨምር ምን እንደሚሆን በግልጽ እየታየ ፖለቲከኞቿ የጅምላ ሰልፍ ያደራጃሉ፤ በዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ሆነው መንግስት ፈርሷል የሚል እብለት ውስጥ ገብተዋል።

ተጨማሪ 142 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውንና ሦስት ሰዎች መሞታቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 4 ሺህ 120 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ142 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፤ ሦስት ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል፤ በዚህም በቫይረሱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል፡፡

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ7 እስከ 78 ዓመት የሚገኙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል 140 ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ቀሪዎቹ አንድ የፖርቹጋል፣ አንድ ደግሞ የጅቡቲ ዜጎች ናቸው፡፡ ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 126 ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው፤ ቀሪዎቹ ስድስት ከአማራ፣ ሰባት ከኦሮሚያ፣ ሁለት ከአፋር፣ አንድ ከሶማሌ፣ ክልሎች ናቸው፡፡

ትናንት 15 ሰዎች (ዘጠኝ ከሶማሌ እና ስድስት ሰዎች ከአዲስ አበባ) ከቫይረሱ ማገገማቸውንም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዚህም አጠቃላይ ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት 246 ደርሰዋል ብሏል ጤና ሚኒስቴር በመግለጫው፡፡በኢትዮጵያ እስከዛሬ ድረስ ለ120 ሺህ 429 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 486 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፤ 17 ሕይወታቸው አልፏል፤ 1 ሺህ 219 ሰዎች ደግሞ በሕክምና ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

foto file AP

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *