በደቡብ ክልል ከፋ ዞን በድንገተኛ ፀብ ህይወቱ ያለፈ አንድ ግለሰብ በተደረገ የአስከሬን ምርመራ የኮረና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑ ታወቀ። ከሳምንት በፊትም አንድ ባልታወቀ ምክንያት ህይወቱ አልፎ በተገኘ ሰው ላይ ተመሳሳይ የአስከሬን ምርመራ ሲደረግ የቫይረሱ ተጠቂ እንደነበር መታወቁ ተጠቁሟል።

የዞኑ የጤና መምሪያ ሃላፊ ዲድብሊው እንዳስታወቁት በድንገተኛ ጸብ ሕይወቱ ያለፈው ሰው የ40 ዓመት እድሜ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነበር። በገበያ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ቅዳሜ በዞኑ አዲዮ ወረዳ ቦቃ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ህይወቱ ያለፈው ይህ ሰው ለፖሊስ ስራ በሚል አስከሬኑ ከመመርመሩ በፊት ኮሮና እንዳለበት አይታወቅም።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

የዞኑ ፖሊስ የግለሰቡ ህይወት በሰው አጅ መጥፋቱን በማስረጃ ለማስደገፍ እንዲረዳው የሟች አስክሬንን አዲስ አበባ ወደሚገኘው ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል በመላክ ምርመራ ባስደረገበት ወቅት ነው የኮሮና ተህዋስ ተጠቂ መሆኑ መረጋገጡን ሃላፊው ይፋ አድረገዋል።

በተላከው የሟቹ አስክሬን ላይ የኮሮና ተህዋሲ መገኘቱን ትናንት ማታ ለዞኑ ጤና መምሪያ ሪፖርት መደረጉን የገለጹት ሃላፊው፤ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ከሟች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች የመለየት ስራ እየተካሄደ መሆኑንን ገልጸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፈው ሳምንት በዞኑ ዴቻ ወረዳ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሞቶ የተገኘ ግለሰብ አስክሬኑ ሲመረመር በኮረና ተህዋሲ የተያዘ ሆኖ መገኘቱን አቶ የጊዜወርቅ ተናግረዋል።በአሁኑወቅት አስክሬኑን በማንሳትና በማጓጓዝ የተሳተፉትን ጨምሮ ከሟቹ ጋር ንክኪ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ 61 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን አስረድተዋልል።

በተመሳሳይ ዜና በጉራጌ ዞን የኮሮና ተህዋሲ ተጠቂ ከሆነች ግለሰብ ጋር ንክኪ ነበራቸው ያላቸውን 47 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ማስገባቱን የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል።የመምሪያው ሃላፊ አቶ ፋሲካ ዓለሙ ለዶቼ ቨለ ( DW ) እንዳስታወቁት በዞኑ የቸሃ ወረዳ ነዋሪ የሆነችና የ28 አመት እድሜ ያላት እናት አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሳ ስትመለስ በተህዋሲው እንደተያዘች ለማረጋገጥ ተችሏል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ይህን ተከትሎም በተህዋሲው ከተያዘችው ግለሰብ ጋር አብረው የተጓዙትን ጨምሮ በተለያየ መንገድ ንክኪ ይኖራቸዋል ተብለው የተጠረጠሩ 47 ሰዎች በለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን ሃላፊው አስረድተዋል ሲል የዘገበው የሃዋሳው ዘጋቢያችን ሽዋን ግዛው ወጋየሁ ነው።ምንጭ፦ #DW_Amharic

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *