እንዲህ ያለ ቁጥር ለኢትዮጵያዊያን የሚታወቀው በዘረፋ ነበር። 12 ቢሊኦን ዶላር ከኢትዮጵያ ሸሸ። 7 ቢልዮን ዶላር በገንዘብ አጠባ ወደ ውጭ ባንኮች ተሻገረ። በቢልዮን ብር ወጪ የሆነባቸው ፕሮጀክቶች ዳዋ መታቸው፤ ወደሙ፤ ተገትረው ቀሩ … ዛሬ ደግሞ 5 ቢሊዮን ችግኝ የማልማት ዜና ብስራት።

ቀደም ባሉት ሁለትና ሶስት አስርት ዓመታት ደካማ የሚያጎርስ፣ የደካማ ቤት የሚጠግን፣ ከድህነት ወለል በታች በሚኖሩ አዛውንት ቤት ገብቶ በዛገ ትሪና በነተበ ሰፌድ ማዕድ የቆረሰ መሪ አልታየም። በየሆስፒታሉ ህሙማንን የሚጠይቅ መሪና ካቢኔዎች አልነበሩም። ህጻናት ጠኔ እየጣላቸው በትምህርት ቤት ሲፈነገሉ ዳቦ ላጉርስ ያለ አልሰማንም። የነብረውን ደን በጨበጣ ልማት ስም እያወደሙ ከሰል የሚያከስሉና ጣውላ የሚነግዱ እንጂ ችግኝ የሚያስተክሉ ቆራጦች ስለመኖራቸው አናውቅም። ቢኖርም ለመርሃ ግብር ማሟያ እንጂ በፍላጎት የሚሆን አልነበረም።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚህ ሌባና ሌብነትን በሚጠየፈው አቋማቸው ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ አብይ አሕመድ ባሳለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የተጎነጎነባቸውን የሴራና የህይወት አደጋ እየተቋቋሙ ለዚህ ቀን መብቃታቸው ለሚያስቡ ሁሉ አስገራሚ ነው። ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጀምሮ በእሳት ውስጥ እያለፉ ያሉት ወጣቱ መሪ አገሪቱን የማተራመሱን ዘርፈ ብዙ እቅድ ከሚያግዟቸው ጋር በመሆን ሲያልፉት ኮሮና ተጋረጠባቸው። ይሁን እንጂ እየደከሙ ነው።

የአዲስ አበባን ቆሻሻ ከመጥረግ ጀመሮ አዲስ አበባን ውብ ለማድረግ ዛፍ ተክለው ወሃ ሲያጠጡ ” ለምን ” ቢሉ ወገኖች የሚብጠለጠሉ ሁሉን ወደጎን ትተው አዲስ አበባን አስውበዋል። እያስዋቡ ነው። እንጦጦን ነፍስ ዘርተውበታል። ገና ይቀጥላል። በዚህ ሁሉ ስራቸው የጎጥና የጎሳ ተባይ የበላቸው ዘማቻቸውን እያፋፋሙ መሆኑ እንደ አገር የውድቀት ምልክት ቢሆንም ” አሻግሬ” ዛሬ አምስት ቢሊዮን አምና አራት ቢሊዮን በድምሩ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኝ ለአገራቸው አበርክተዋል። እውነትም አሻራ!!

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ፋና ይን ብሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በሀዋሳ አስጀመሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከክልል እና ፌደራል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎችጋር በመሆን ነው በጋራ በታቦር ተራራ ላይ ዘመቻውን ያስጀመሩት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም በኮቪድ-19 ምክንያት ዕድገታችን አይገደብም ብለዋል።

 ዛሬ እየተከበረ ያለውን የዓለም የአካባቢ ቀን ምክንያት በማድረግ ነው ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሯን በዛሬው እለት ያስጀመረችው። ዘመቻው ኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወትን ለማስጠበቅ እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ዕድገትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ መርሃ ግብሩ በፌዴራል ደረጃ በሀዋሳ ቢጀመርም በሌሎች የአገሪቷ አካባቢዎች ችግኝ ተከላ እንደሚካሄድ መንግስት አስታውቋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የወቅቱ ስጋት እንደመሆኑም የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃግብር ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ከሚደረገው ጥንቃቄ ጋር ተጣጥሞ ይካሄዳል ብሏል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

ሃዋሳ

 በስነ ስርዓቱ ላይ በዚህ ዝናባማ ወቅት በአንድ በኩል የኮቪድ-19ን በመከላከል በሌላ በኩል ደግሞ 5 ቢልዮን ችግኞችን ለመትከል በቤተሰብ እና በማኅበረሰብ ደረጃ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን የኮሮናቫይረስን በጥብቅ በመከላከል ሁሉም ኢትዮጵያዊ የ2012 ችግኝ ተከላን በንቃት እንዲሳተፍ ብሔራዊ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *