ይህ ስለአገር አንድነት ማቀንቀኔ አሀዳዊነት ካሰኘኝ ልሁን ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ አገር አንድ እንድትሆን፣ አገር እንዳትበተን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰላምና በመቻቻል አብረው እንዲኖሩ፣ የመንቀሳቀስና የመስራት ነጻነት እንዲያገኙ እንደሚያቀነቅኑ ነው የገለፁት።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፤ አገር አንድ እንድትሆን፣ አገር እንዳትበተን፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሰላምና በመቻቻል አብረው እንዲኖሩ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ዜጎች የመንቀሳቀስና የመስራት ነጻነት እንዲያገኙ አቀነቅናለሁ ብለዋል። ስለአገር አንድነት ማቀንቀኔ አህዳዊነት አይደለም ብለዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በአሀዳዊና በአንድነት መካከል ልዩነት መኖሩን የገለጹት አቶ ሙስጤፌ እኔን የአሀዳዊነት የፖለቲካ አቀንቃኝ ነህ የሚሉ ካሉ ስህተት ነው።እኔ የአንድነት ፖለቲካ አቀንቃኝ ነኝ ብለዋል።

ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ላላት ኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር ይጠቅማታል ብለው በግላቸው እንደሚያምኑ የገለጹት አቶ ሙስጠፌ የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር ግን ከአንድነት ጋር እንደማይጋጭ ተናግረዋል።

በፌዴራል ሥርዓት አስተዳደር ስር በተዋቀሩት ክልሎች የአንዱ ብሄረሰብ የበላይነት የሚሰፍንበት፤ ሌላው የሚጨቆንበት፣ አንዱ ልጅ ፤ሌላው የእንጀራ ልጅ የሚሆንበት ሥርዓት መፈጠር የለበትም ብለዋል፡፡

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሶ በሰላም አብሮ የሚኖርበትና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ያለባት አንድ ኢትዮጵያን እንደሚመኙና ለአገራችንም የሚያዋጣው ይህው ነው ብለው በግላቸው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

የአገር አንድነት ማቀንቀንና አሀዳዊነት የመንግስት አስተዳደር የተለያዩ መሆናቸውን ገልጸው አሀዳዊና ፌዴራላዊ ሥርዓት የመንግስት የአስተዳደር ዘዬ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *