“ኦሮሞ ስማ !! የኢትዮጵያ ሕዝብ ስማ!! የህወሃት ሰራዊት ኦሮሞን ሊገል በምዕራብ ወለጋ መፈንጫ ተሰጠው”

 

አቶ በቀለ ገርባ “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ዝምቤንም እሽ አላለውም” በሚል የሰጡትን መግለጫ መልስ ማግኘቱን ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገው ድሪባ ይናገራል። ድሪባ አቶ በቀለ ይህንን ከማለታቸው በፊት እጅግ ከሚቀርቧቸው አንዳንድ ባልደረቦቻቸው ህወሃት ስትራቴጂካል አጋር መሆኑን ይሰማ ነበር። እናም አሁን ህወሃት በምዕራብ ኦሮሚያ ሰራዊት አሰማራ መባሉ እንግዳ አልሆነበትም። ግን ማዘኑንን አይደብቅም።

አቶ በቅለ ብቻ ሳይሆኑ “ የኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን” የሚሉ ወደ መቀሌ የመመላለሳቸው ጉዳይ፣ በአፍቃሪ የህወሃት መገናኛዎች ላይ አዘውትሮ መታየትና የህወሃት አንድበት ለሆኑ የዩቲዩብ ገጾች የእለት ጉርስ መሆናቸው ስህተት እንደሆነ ከእነዚሁ ባልደረቦቹ ጋር አዘውትሮ ሲወያይ መቆየቱን ያስታውሳል።

“የህወሃት ለኦሮሞ ድርጅቶች ስትራቴጂክ አጋር የመሆን ጉዳይና ከህወሃት ጋር አብሮ ለማደም መስማማት ራሱን የቻለ ክህደት ነው፤ ሩቅ የሚዘልቅ ሳይሆን በቅርቡ በኦሮሞ ልጆች የሚመክን ስሌት ነው። ነገር ግን በኦሮሞ ታሪክ ታላቅ ጠባሳ ሆኖ ይኖራል። ታሪክም ይቅር አይለውም ” ሲል አምርሮ የሚናገረው ድሪባ “ የሌሎችን ሳይጨምር አምስት ሺህ ልጆቿን የገበረችው ኦሮሚያ፣ ይህንን ጭፍጨፋ ለፈጸመባት ክፍል ኦሮሞን እንዲገሉ ልጆቿ ነጻ መሬት  ሰጡ የሚለውን ዜና በኦፊሳል ስሰማ ማመን ቸገረኝ፣ እስካሁንም በቅዠት ውስጥ ያለሁ ያህል ነው የሚሰማኝ” በማለት ስሜቱን ይገልጻል።

“ የኦሮሞ ልጆች ቁጭ ብለው ችግራቸውን መስማማት አቃታቸው ?” ካለ በሁዋላ ድሪባ ሳግ ያዘው። ለደቂቃዎች ጸጥ አለ። ስልኩ ተቋረጠ። ከቆይታ በሁዋላ “ ለጊዜው ከዚህ በላይ መናገር አልችልም። ሃዘን የጠበሳት እናት እምባ ይፍረድ። ኦሮሞ የሆንክ ሁሉ አስብ” በማለት ስልኩን ዘጋ።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

“ የመከላከያ ሰራዊት የማረካቸውና ወደው እጅ የሰጡ ሲናገሩ ሰማሁ” ሲል ለኢትዮ ጎልጉል መረጃ ያቀበለ እንዳለው በምዕራብ ኢትዮጵያ ጠብ መንጃ ያነሳው የኦነግ ሸኔ ህጻናት ስልጠና የተሰጣቸው በህወሃት ነው። ለምን መንግስት እስካሁን እንደደበቀው ግልጽ አልሆነልኝም። ይላል። ይህ ስሙን ያልጠቀሰ አስተያየት ሰጪ የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ይህንን እውነት ፈጥረው አላወሩትም። የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንደሚባለው ህወሃት ዛሬ ላይ ምንም አትመርጥምና እንተንቀቅ”

ቪኦኤ ድምጻቸውን ያሰማው የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር እንደሚሉት ቁጥራቸው በርካታ የሆነ የህወሃት ታጣቂዎች ከኦነግ ሸኔ ሽፍቶች ጋር ተቀላቅለው የኢትዮጵያን መከላከያና የኦሮሞ ልጆች ላይ መተኮስ ጀምረዋል። ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ህወሃት ከትሞ የኦሮሞ ልጆችን እንዲገል ፈቃድ አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ቀደም ተብሎ የሚታወቅ ቢሆንም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አሁን ለምን ይፋ እንዳደረገው ግን የታወቀ ነገር የለም።

“ ስትፋቅ ኦነግ ነህ ” በሚል ሲዘበትብህ የነብርከው በማን ነበር? ደራራ ከፍኔ አምቦ ሲገደል ምን ተደርጎ እንደነበር ኦሮሞ አይረሳም። የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ቋንቋ ኦሮምኛ የሆነው በማን ዘመን ነበር? የልጇ አስከሬን ላይ ሆና ወለጋ የተደበደበችው እናት ማን ደበደባት? ማን ልጇን አልሞ ገደለ? አምስት ሺህ የኦሮሞ ልጆችን ማን አልሞ ገደለ? ኦርሞ በመሆኑ ብቻ እየታደነ የተለቀመው ህዝብ ዛሬ ለወያኔ ነጻ መሬት ሲፈቅድ ማየት ምን ማለት ነው? ኦሮሞ ጠይቅ? ኦሮሞ ጠይቅ? ለመሆኑ የደምህና የመከራህ ደጋሽ ምድርህ ላይ ሆኖ ወንድሞችህን እንዲገድል ማበርን ማን ፈቀደ? ምን ለማግኘት? “ ሲል በሜሲንጀር መልዕክት የላከው ታፈሰ ኡርጌሳ በሚባል የፌስ ቡክ ገጽ የሚታወቅ የግንደበረት ልጅ ነው።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

“ሁሉንም አይነት የማተራመስ ሙከራ አድርጎ ያልተሳካለት ህወሃት ልክ እንደ አሳማ በገኘው ቆሻሻ ላይ ሁሉ እየተንከባለለ ነ” የሚለው ደግሞ ደስታ ሃይሌ ነው። ነዋሪነቱ በጀርመን የሆነው ደስታ ህወሃት ወደ ክልሉ ከተሸኘ በሁዋላ የማዕከላዊ መንግስቱን ለማፍረስ ላይ ታች ሲል ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ሁሉንም አይነት ድንጋይ ቢፈነቅልም አልተሳካለትም ባይ ነው። ክልል እንደሚመራ ድርጅት አንድም የልማት ስራ አላከናወነም። የሕዝብ ጥያቄ መመልስ ቀርቶ ሊሰማ አይወድም። እንዲያውም በተቃራኒው ህዝቡን “ ተከበሃል” በሚል ማስፈራሪያ “ ትገነጠላለህ” በሚል አጉል ተስፋ እያሞኘ፣ ኤርትራን ወረን አገር እንመሰርታለን በሚል የፌስ ቡክ ወሬ የላም አለኝ በሰማይ ተረቱን ሲረጭ ቢከርምም አሁን መጨረሻው ምዕራብ ወለጋ ሆኗል። ይህ ለትግራይ ሕዝብ የሚፈይደው ነገር የለም ሲል ያክላል።

ህወሃት የመጀመሪያ ዒላማ የነበረው የአማራ ክልልን ማተራመስ ቢሆንም ዛሬ ክልሉ ውስጡን እያጠራ፣ የፋኖ መሪዎችም በስማቸው እንደማይነገድባቸውና በክልላቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ ይፋ እያደረጉ ከመንግስታቸው ጋር ቆመዋል። የተወሰደባቸውን መሬትም ለማስመለስ ከክልሉ ጋር ተግባብተዋል። ክልሉም ይህን የተወሰደ መሬት በህጋዊ መንገድ ለማስመለስ እንደሚሰራ ቃል ገብቶ ነገሮች ረግበዋል።

ደስታ እንደሚለው በአሁኑ ወቅት፣ የቅማንት ሕዝብ ላይ የተረጨው ቅስቀሳ ሲመክን ራዳሩን ወደ ኦሮሚያ ያደረገው ህወሃት በእነ በቀለ ገርባና ሕዝቄል ጋቢሳ በኩል ሲያሰራጭ የከረመው ሽምግልና ዓላማው ግልጽ የማይሆንለት ኦሮሞም ሆነ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብሎ እንደማያስብ ይገልጻል።

በጅ መንሻና በሁከት ዘመቻ ሃብቱን ከስክሶ ተጨማሪ በጀት የጠየቀውና የተከለከለው ህወሃት ከበስለ የፖለቲካ ትግል እየወላለቀመውታኡን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውን የሚናገረው ደስታ “  ህወሃት ዛሬ በተራ ስድብ፣ በፈጠራ ዜና፣ ግለሰቦችን በማጠልሸት ላይ የተቸከለው የደረሰበት የእድገት ደረጃ ውጤት ላይ በመድረሱ ነው” ሲል የህወሃት የእድገት መጨረሻ ያሳያል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አንድ በርካታ ችግሮች ያሉበትን ክልል የሚመራ ድርጅት ዜና እያመረተ ሲያሰራጭ፣ የኮማሪት ፖለቲካ ሲያራምድ፣ በማይመከተው ጉዳይ ውስጥ እየዘለለ ሲቀረቀር፣ እንደ እሪያ ባገኘው ቆሻሻ ላይ ሲልከሰከስ፣ ያልሆነውን ለመሆን ሲሞክርና ያማያውቅበትን ለቅሶ ደራሽ ሲሆን በፖለቲካው ቋንቋ “ መበስበስ” ነው። ደስታ ሟቹን አቶ መለስ ዜናዊ “ ከንጥላችን በስብሰናል። ከግሮሯችን ገምተናል” ሲሉ በወቅቱ የተናገሩት በተቋም ደረጃ የደረሰባቸውን ክስረት ለማሳየት መሆኑንን ያመክታል።

ያክልና “ እንደ ድርጅቱ የጡት አባት ገለጻ በበሰበሰው ተቋም ውስጥ አልፎ እዚህ የደረሰው ህወሃት አሁን በመሪዎች ደረጃ የሚታይበት ያ ቀደም ሲል የተባለው የመበስበስ ድምር ውጤት ነው” ይላል። ይህ ፍንትው ብሎ የሚታይ ሃቅ መሆኑንን የሚናገረው ደስታ የትግራይ ሕዝብ ድህነቱ ሳያንሰው ተጨማሪ ጠላት ለምን እንደሚመረትለት ግልጽ ሊሆንለት እንዳልቻለም ይናገራል። የትግራይ ምሁራንም ይህንን እውነት ማየት አለመቻላቸው ምክንያቱን ሲያስብ እንደሚጨልምበት ሳይሸሽግ ይገልጻል።

የፖሊስ ኮሚሽኑ ግርማ ገላን እንደሚሉት ከስልጠና አምልጠው የጠፉና ስልጠናውን ከወሰዱ በሁዋላ ጫካ የተያዙ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በህወሃት አማካይነት ስልጠና እንደተሰጣቸው እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

አገር ካልዘረፍኩ በሚል ምስኪን ህዝብ አግቶ ወደ ጦርነት ያመራው ህወሃት ይህ እስከታተመበት ድረስ በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጠም። መንግስትም ክልሉን ተከትሎ የሚይዘው አቋም ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን ይፋ አልሆነም። ክልሎች ግን ለኦሮሚያ ክልል ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ኢትዮ ጎልጉል ሰምቷል። አብን ህወሃት አሸባሪ ድርጅት ተብሎ እንዲፈረጅ መጠየቁም አይዘነጋም። ኢትዮጵያና ኤርትራ የመከላከያና የድህንነት ህበረት ፈጥረው ለመስራት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *