የትግራይ ቲቪ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ላይ የከፈተውን ሁለት ዓመት የዘለቀ የማጠልሸት ዘመቻ አካል የሆነው የፈጠራ ዜና መሰረት የሌለው ቅጥፈት መሆኑንን ቢቢሲ አስታወቀ። ቢቢሲ ተጠቅሶ የተሰራጨው ዜና ቅጥፈት መሆኑ ቢገለጽም እስካሁን ማስተባበያ አልቀረበበትም። ሚዲያውን የሚያስተዳድሩት አካላትም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ደብዳቤ መጻፉ ታውቋል።

በተመረጡ ባጭር ጊዜ ውስጥ ባከናወኑት ተግባር የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ለመሆን የበቁት ዶክተር አብይ “ የምያንማሯ መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ የገጠማቸው አይነት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል ” ሲል ቢቢሲን ጠቅሶ የማጠልሸት ዜና የዘገበው የትግራይ ቲቪ ዘገባውን ባሰራጨ ቅጽበት ውስጥ ” የቀረበው ዜና ፍጹም ሐሰት እና እኛን የማይገልጽ ነው ” ሲል ቢቢሲ እርቃኑንን አስቀርቶታል።

በፕሬስ ህጉ መሰረት በተመሳሳይ ሰዓትና በተመሳሳይ መጠን ማስተባበያ ከይቅርታ ጋር እንዲጠየቅ የሚያዝ ቢሆንም ” ለህግ መከበር ሲባል በሞት ጥላ ውስጥም ቢሆን  ምርጫ አደርጋለሁ” የሚለው የትግራይ ገዢ ይህ እስከተጻፈ ድረስ ለፈጠራ የማጠልሸት ዜናው በአደባባይ ይቅርታ አልጠየቀም።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

“በዘጋቢያችን ቃልኪዳን ይበልጣል የቀረበን የድምጽ ቅጂ ቆርጦ በማውጣት ለዚህ ዘገባው ተጠቅሞበታል፤ ነገር ግን ቢቢሲ ይህን የመሰለ ዘገባ ፈጽሞ አልሰራም” ሲል ቃል በቃል መቃወሚያ ያቀረበበት የትግራይ ቲቪ ዜና አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ምን ርምጃ እንደሚወስድበት ለጊዜው አልተገለጠም።

ቢቢሲ የሚከተለውን ነው ያለው

የትግራይ ቴሌቪዥን “የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር የምያንማሯ መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ የገጠማቸው አይነት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ይኖራቸዋል” ሲል ቢቢሲ ዘገበ በማለት ያቀረበው ዜና ፍጹም ሐሰት ነው።
ትግራይ ቲቪ በቅርቡ፤ ከወራት በፊት በዘጋቢያችን ቃልኪዳን ይበልጣል የቀረበን የድምጽ ቅጂ ቆርጦ በማውጣት ለዚህ ዘገባው ተጠቅሞበታል። ነገር ግን ቢቢሲ ይህን የመሰለ ዘገባ ፈጽሞ አልሰራም።
ምንጊዜም በቢቢሲ የቀረቡ ዘገባዎችን ለማረጋገጥ ትክክለኛውን ድረ ገጻችንንና የፊስ ቡክ ገሻችንን ይመልከቱ …

 

እውነታው ይህ ከሆነ የትግራይ ቲቪ እንዲህ ያለውም የፈጠራ ዜና ለማሰራጨት ለምን አስፈለገው? የሚለው ወቅታዊ ጉዳይ ነገሮችን በጥሞና ለሚከታተሉ ትርጉም እንዳለው በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች እየተሰራጨ ነው።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ከአስራ ዓምስት ዓመት በላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬና የህወሃት ቃለ አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ እዛው ትግራይ ሆነው ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲዘነጥሉና እየተጋገዙ ሲያጣጥሉ ነበር። በዚሁ የቡድን ማጠልሸት ውስጥ አቶ ስዩም መስፍን ”  “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጣቸው የኖቬል የሰላም ሽልማት አይገባቸውም” ሲሉ ተድምጠዋል። ሽላማቱን እንደገና እንዲነጠቅ ኖርዌይ ስራ መጀመሩንም ጠቆም አድርገው ነበር።

ህወሃት የገነባውን የዲፕሎማሲ ሃይል አዲሱ መንግስት ገደል እንደከተተው በደሰኮሩበት ፕሮግራም ላይ ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ የህወሃት የዲፕሎማሲ ድል አንድ ሁለት ብለው እንዲጠቅሱ አልተጠየቁም። ስዩም መስፍን አልጀርስ ላይ ኢትዮጵያ በህግ ክርክር እንድትሸነፍ ያደርጉ፣ ከዛም በሁዋላ ኢትዮጵያ በጦርነት 100 ሺህ ሰዎች ገብራ ያሸነፈችውን ጦርነት በዲፕሎማሲና በክርክር በሽንፈት ማተናቀቃቸ የሚታወስ ነው። የአልጀርሱ የሽንፈት ሰነድ አደባባይ ላይ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያን ሕዝብ በናቀ መልኩ ” ኢትዮጵያ በአልጀርሱ ስምምነት አሸነፈች” በሚል ሕዝብ ሰላዊ ሰልፍ እንዲወጣ ያደረጉ፣ ይህንንም በአደባባይ ጥቁር ክራባት ለብሰው በቀጥታ ስርጭት ያበሰሩና ከበሮ ያስደለቁ ” ውሸታም” መሆናቸውን ቃለ ምልልሳቸው አየር ላይ መዋሉን ተከትሎ በርካቶች  በማህበራዊ ገጾቻቸው አስተያየት ሰጥተዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ይህንኑ ተከትሎና የስዩም መስፋንን ፍንጭ ለማተናከር በሚል ከዛሬ አስራ አንድ ወር በፊት አንድ የቢቢሲ ሪፖርተር ተናገረ በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የማጠልሸቱ ዜና እንደተቀነባበረ አብዛኞች ይስማማሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ለትግራይ ቲቪ ማስጠንቀቂያ መላኩን፣ ህጉን ተከትሎ ማስተባበያ ከይቅርታ ጋር እንዲያቀርብ ቀነ ገደብ አስቀምጦ መመሪያ መስጠቱን ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮቹ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠበቅም አክለው ገልጸዋል። በትግራይ ህዝብ በተቃውሞ መንገድ መዝጋቱ ለምን ዜና ሆነ በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰማው የትግራይ ክልል የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መልስ ተጠይቆ ” የማቀው ነገር የለም” ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *