በዛሬው እለት ይፋ በሆነው እለታዊ የማስታወቂያ ሪፖርት ቫይረሱ ቢያጠቃትም በሰላም ተገላግላ የነበረች አንዲት እመጫት ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል። ተጨማሪ 86 ሰዎች በቫይረሱ መተቃታቸው ይፋ ሆኗል። አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 2020 ደርሷል። አሁን ጊዜው ወደ ከፋው ቀውስ እየተሸጋገረ ነው።
የዛሬውን ጨመሮ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር ወደ 27 ከፍ ብሏል።  ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,092 የላብራቶሪ ምርመራ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,020 ደርሷል። ቁጥሩ በሁሉም መስክ እያሻቀበ ነው።
በኤካ ሆስፒታል ህክምና ላይ እያለች ልጇን በሰላም የተገላገለችውን እናት ህይወቷ ማለፉ ልክ ዓለም ላይ ሲሰሙ የከረሙና እኛ ልንማርባቸው ያላቻልናቸው አይነት ልብ የሚሰበሩ ዜናዎች በአገራችንም መደመጥ መጀመሩን አብሳሪ ሆኗል።
በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት ስላሳ ሶስት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ዶር ሊያ በሪፖርታቸው ይፋ አድርገዋል። በዚሁ ስሌት  ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 344 ከፍ ሊል ችሏል። 32 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ ይገኛል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *