ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

” ከዱ” ከሁነኛ ምንጭ ስለ አምባሳደር ትርፉ ! የኢንቨስትመንቱ አንድ ሚልዮን ዶላር ከየት መጣ?

አምባሳደሯ አውስትራሊያ ውስጥ መኖሪያ ቤት የገዙ ሲሆን ለኢንቨስትመንት ፈቃድ የጠየቁትም የለውጡ ሀይል ስልጣን ከመያዙ በፊት ነው። ለውጡን ከመቀላቀላቸው በግምት ከአንድ አመት በኋላ ወደ ኢትዮጲያ ለስራ ጉዳይ ተጠርተው ነበር። ባለቤታቸው አቶ አባይ ወልዱ ትግራይ ውስጥ በጣም ታመው ነበር። የደህንነት ስጋት ስላደረባቸው የፌደራል መንግስት ደህነታቸው እዲጠበቅ ለክልሉ መንግስት በተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ ወደ ትግራይ ሄደው ለጥቂት ሳምንታት ቆይተዋል።
By – Wondemagegnehu Addisበወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ጉዳይ ወንድማችን ስዩም ተሾመ የለቀቀው እና በአንዳንድ አክቲቪስቶቾ እየተራገበ ያለው መረጃ የተዛባ ነው።
አምባሳደር ትርፉ እና ባለቤታቸው ከህወሀት ዝሆኖች ጋ ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደነበረ እና ከዚያም ከማእከሉ በአምባሳደርነት እንዲርቁ መደረጋቸው የሚዘነጋ አይደለም። በለውጡ ማግስትም አምባሳደሯ ተደምሬአለሁ ለውጡን ለውጡን ተቀላቅያለሁ በማለት ባደባባይ መግለጫ የሰጡ ምናልባትም የመጀመሪያዋ የህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣን እንደሆኑ ያደባባይ ሀቅ ነው። መደመራቸው ከአንገት ይሁን ካንጀት ግን ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው። በወቅቱ የሴትዮዋን አቋም ተከትሎ ሜልበርን በተካሄደው በአውስትራሊያ የኢትዮጲያውያን የስፖርትና የባህል ቶርናመንት ላይ መጋበዛቸው ይታወሳል። ቀላል የማይባል ቅሬታ ቢኖርም በበጎ ያዩትም በርካቶች ነበሩ።
አምባሳደሯ አውስትራሊያ ውስጥ መኖሪያ ቤት የገዙ ሲሆን ለኢንቨስትመንት ፈቃድ የጠየቁትም የለውጡ ሀይል ስልጣን ከመያዙ በፊት ነው።
ለውጡን ከመቀላቀላቸው በግምት ከአንድ አመት በኋላ ወደ ኢትዮጲያ ለስራ ጉዳይ ተጠርተው ነበር። ባለቤታቸው አቶ አባይ ወልዱ ትግራይ ውስጥ በጣም ታመው ነበር። የደህንነት ስጋት ስላደረባቸው የፌደራል መንግስት ደህነታቸው እዲጠበቅ ለክልሉ መንግስት በተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ ወደ ትግራይ ሄደው ለጥቂት ሳምንታት ቆይተዋል። በቆዩባቸው ጊዜያት ውስጥ ከስድብ እና ከማዋረድ እስከ ከፍተኛ ማስፈራራት ሲሰነዘርባቸው ነበር። ውሎ እያደር ዛቻው እየበረታ ስለመጣና ስጋታቸው በመጨመሩ ለመቆየት ካቀዱት ጊዜ ቀድመው ተመልሰዋል።
በቅርቡ በቦታቸው አዲስ አምባሳደር በመመደቡ ወይዘሮዋ በአምባሳደርነታቸው ይኖሩበት የነበረውን ቤት እንዲሁም ከኤምባሲው የተረከቧቸውን ንብረች ሁሉ አስረክበው ጨርሰዋል። እንደ አንድ የስራ ዘመኑን እንደጨረሰ አምባሳደር ወደ ሀገር ተመልሰው ሪፖርት ማድረግ ቢጠበቅባቸውም ባቀረቡት የግል ምክንያትና በኮሮና ወረርሽኝ ሰበብ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እስከ መስከረም እዛው እንዲቆዩ ፈቅዶላቸዋል። በዲፕሎማቲክ ቪዛ ወይም በምን አግባብ እንደሚቆዩ አልታወቀም።
የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቅ የሚለው የተሳሳተ የሚሆነው ሴትየዋ ከለውጡ በኋላ ካለው መንግስት ጋ የአምሳደርነታቸውን ጊዜ እስከጨረሱ ድረስ ግጭት ውስጥ አልገቡም። ተባረው ሳይሆን ተቀይረው ነው ከአምባሰደርነታቸው የተነሱት። ህወሀት ስልጣን ላይ ባለመሆኑ ከዛ አቅጣጫ የሚመጡ ስጋቶች ለፖለቲካ ጥገኝነት በቂ አያደርጉም። ባጠቃላይ ከለውጡ በኋላ እንኳን ካለው መንግስት ጋ ያልተፋቱ ሰዎችን ቀርቶ ተቃዋሚ ለሆኑትም የፖለቲካ ጥገኝነት ያለቀለት ጉዳይ ነው።
Ambassador's Message | The Embassy of the Federal Democratic ...
ሴትዮዋም የዚህን ያክል የዋህ አይመስሉኝም። ባለኝ መረጃ መሰረት ፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቁ የሚለው ወሬ ለሁለተኛ ጊዜ እዚህ በሚገኙ አፍቃሪ ህወሀት የትግራይ አክቲቪስቶች በተዘዋዋሪ የሚለቀቅ እና አንዳንድ የዋሆችም በቅንነት እንደ ወረደ የሚቀበሉት ነው። ሌሎች ነገሮችንም እየፈበረኩ በእጅ አዙር ሊያሳስቱን ስለሚሞክሩ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
በእግረ መንገድ የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ።
1_ አምባሳደሯ ለውጡን ተቀበልኩ ያሉት አምነውበት ነው ወይስ ከህወሀት ዝሆኖች በተሰነዘረባቸው ጥቃት ቂም ቋጥረው ነው?
2_ ባለቤታቸው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እሳቸውም የህወሀት ማ/ኮ/አባል ከመሆናቸው በፊት እንደ ህወሀት አመራር የሀገሪቱ አንድነት ጨምሮ ለፈፀሟቸው በደሎች ይቅርታ ጠይቀዋል ወይ?
3_ አቶ አባይ ወልዱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው በወልቃይት እና በራያ በሳቸው ትእዛዝ ለተፈፀሙት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶቾ ይቅርታ ጠይቀዋል ወይ?
4_ በተለያዩ የሜዲያ ዘገባዎች አምባሳደሯና ባለቤታቸው ከህወሀት ከፍተኛ አመራሮች ከሙስና የፀዱ እንደነበሩ ሲነገርና ህወሀትም እነሱን ለማሰናበት የተቸገረው በዚሁ ምክንያት እንደነበረ ጆሯችን እስኪነደል ደጋግመን ሰምተናል። ታዲያ አውስትራሊያ ውስጥ ቤት ለመግዛት እና ኢንቨስት ለማድረግ በትንሹ 1,000,000 የአውስትራሊያ ዶላር ይጠይቃል። የዚህ ገንዘብ ምንጩ የት ነው?
የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።