“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኮሮናቫይረስ፡ ደጁን ለረገጡ ሁሉ ቫይረስ ያደለው የሩሲያው ሆስፒታል

ሆስፒታሉ ጥንታዊ ነው። በግሪጎሪ አቆጣጠር 1906 ነው የተገነባው። ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ‘ሪፈር’ የተፃፈላቸው በሽተኞች ናቸው የሚመጡት። ወረፋ ማግኘት ቀላል አይደለም። የወራት ቀጠሮ ማግኘት መታደል ነው። ሐኪሞች አጥንት ሰብረው፤ አጥንት ጠግነው፤ ቤት ሂዱና በአጥሚት ደግፉት የሚሉበት የታወቀ ሆስፒታል።ሆስፒታሉ አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ ተይዞብኛል ብሎ መግለጫ ሲያወጣ ሩሲያውያን ከቫይረሱ ሽሽት ቤታቸው መሽገው ነበር።

BBC Amharic – ወርሃ ሚያዚያ መግቢያ በሩሲያዋ ሴይንት ፒተርስበርግ በሚገኝ የአጥንት ሆስፒታል አንድ ታካሚ የሳንባ ምች ተገኘበት። የበሽተኛው የኮሮናቫይረስ ውጤት ሲመጣ ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋገጠ። ይሄኔ ነው ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ሁሉ ተለይተው እንዲቆዩ የተደረገው።

ከ700 በላይ የሕክምና ባለሙያዎች ለሚቀጥሉት 35 ቀናት ከማንም ጋር ሳይገናኙ መቆየት ነበረባቸው።

ሁኔታው ዳይመንድ ፕሪንሰስ ከተሰኘችው መርከብ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ኮቪድ-19 ገና በመስፋፋት ላይ ሳለ ይህች መርከብ ወደ ጃፓን ወደብ ትጠጋለች። ታድያ መርከቧ በኮቪድ-19 ተበክላ ኖሯል። መርከቧ ላይ የነበሩ ሰዎች ምርመራ ሲደርግላቸው አብዛኛዎቹ ቫይረሱ ተገኘባቸው። ከእነዚህ መካከል 9 ሰዎች መሞታቸው አይዘነጋም።

የሩስያው ሆስፒታል ዕጣ ፈንታም ተመሳሳይ ሆኗል። ምርመራ የተደረገላቸው ሁሉ ውጤታቸው ‘ፖዘቲቭ’ ነው። እስካሁን ቢያንስ ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችና ሁለት በሽተኞች ሞተዋል። የከተማይቱ አስተዳደር ሙሉ መረጃ ስላላወጣ ቁጥሮች ከውስጥ አዋቂ የተገኙ ናቸው።

Related stories   የትግራይ ክልል ባቀረበው ፍላጎት መሠረት የአፈር ማዳበሪያ መቶ በመቶ እንዲቀርብ መደረጉ ተገለጸ

አብዛኛዎቹ ታሪካቸውን ያካፈሉት በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ነው። ከእነዚህ መካከል ሁለቱ ለቢቢሲ ሩሲያ ክፍል ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ሆስፒታሉ ጥንታዊ ነው። በግሪጎሪ አቆጣጠር 1906 ነው የተገነባው። ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ‘ሪፈር’ የተፃፈላቸው በሽተኞች ናቸው የሚመጡት። ወረፋ ማግኘት ቀላል አይደለም። የወራት ቀጠሮ ማግኘት መታደል ነው። ሐኪሞች አጥንት ሰብረው፤ አጥንት ጠግነው፤ ቤት ሂዱና በአጥሚት ደግፉት የሚሉበት የታወቀ ሆስፒታል።ሆስፒታሉ አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ ተይዞብኛል ብሎ መግለጫ ሲያወጣ ሩሲያውያን ከቫይረሱ ሽሽት ቤታቸው መሽገው ነበር።

«መጀመሪያ አንድ ሰው ሳል እንዳለበት ተነገረን። ነገር ግን ኮቪድ-19 ይሁን አይሁን አልታወቀም ነበር። ለማንኛውም ጭምብል አጥልቁ ተባልን። መድኃኒት ቤት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማጣታችን ፋሻ [ባንዴጅ] ሁላ ተጠቅመናል» ትላለች በሆስፒታሉ ሕክምና እያገኘች ያለችው አይሪና።

ኢሪና ከፋሻ ያዘጋጀችውን አፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋImage copyrightIRINA YEFREMOVA

ሌላኛዋ ታካሚ ኔድዛዳ ከሁለት ዓመት ጥበቃ በኋላ የረገጠችው ሆስፒታል መድኃኒት ሳይሆን ቫይረስ አድሏታል። ለመጣችበት በሽታ ሕክምና ከማግኘቷ በፊት ወደ ኮቪድ-19 ታካሚዎች ረድፍ ገብታለች።

«ስመጣ ጤናማ ነበርኩ። ነገር ግን አሁን ቫይረሱ አለብኝ። የጠናባቸው ሰዎች ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች እየተወሰዱ ነው» ስትል ፅፋለች።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

ሆስፒታሉ በሩን ሲዘጋ 474 ታካሚዎችና 239 የህክምና ባለሙያዎች ግቢው ውስጥ ነበሩ። በሚቀጥለው ቀን ዶክተሮችና ነርሶች ወደ ለይቶ ማቆያ ስለሚገቡ ቤታቸው ሄደው የሚያስፈልጋቸውን ጭነው እንዲመጡ ተነገራቸው። ታካሚዎች ግን ከግቢው ንቅንቅ እንዲሉ አልተፈቀደላቸውም።

አንድ ዶክተር ሁኔታውን ሲገልፀው ‘ሰዉ ለአገርህ እወቅ የመጣ ነበር የሚመስለው’ ይላል። ሁሉም ሻንጣውን ሸክፎ ሆስፒታሉ ግቢ ተገኘ።

አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ከቀዶ-ጥገና ሕክምና በማገገም ላይ የነበሩ ናቸው። የተቀሩት ደግሞ በቀጠሯቸው መሠረት ሕክምና ሊደርግላቸው የታሰቡ ናቸው።

ቫይረሱ በፍጥነት እንዳይሰራጭ በማሰብ የሆስፒታሉ ማጤዣ እንዲዘጋ ተደረገ። ለበሽተኞች ምግብ የሚቀርብላቸው ያረፉበት ክፍል ደጃፍ ነው።

ነገር ግን ሆስፒታሉ ለኮሮናቫይረስ የተዘጋጀ አይመስልም። በተለይ ደግሞ የመከላከያ ቁሶች እጥረት ትልቁ ፈተና ነበር። ነገሮች መስተካከል ሲጀምሩ ቁሶችም ሲሟሉ ግን ቫይረሱ ሁሉንም አዳርሶ ነበር። ሆስፒታሉ የሕክምናም ሆነ የመከላከያ ቁሶች ያገኘው ከተዘጋ ከ10 ቀናት በኋላ ነበር።

ከሆስፒታሉ ውጪ ቆመ አምቡላንስ ንድፍImage copyrightDENIS KOROLEVአጭር የምስል መግለጫ20 በመቶ የሚሆኑ በሆስፒታሉ የነበሩ ታካሚዎች ሕመሙ ሲፀናባቸው ወደ ሌላ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርገዋል

አጥንት ሰብሮ የሚጠግነው፤ አከርካሪ የሚያቃናው ሆስፒታል ኮሮናቫይረስ ፈተነው። ከዚህም ከዚያም ሰው ያስላል፣ የትኩሳቱ እንፋሎት ከሩቅ ይታያል።

Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ

አብዛኛዎቹ የበሽታውን ምልክት ያሳዩት በመጀመሪያው የለይቶ መቆየት ሳምንት ነበር። የናዴዝዳ ጓደኛም ይህ ነው ያጋጠመው። ከዚያም በሽታው ሲፀናበት ወደ ሌላ ሆስፒታል ተወሰደ። ከቀናት በኋላ ጓደኛዋ መሞቱን ሰማች።

ነገር ግን የሆስፒታሉ ሐኪሞች የሚችሉት አድርገዋል። ለዚህም ከብዙዎች ምስጋና ተችሯቸዋል። ባለሙያዎቹ ከኪሳቸው አውጥተው የማጠቢያ ማሽን በመግዛት የታካሚዎችን ልብስ ያጥቡ ነበር።

የሆስፒታሉ ነርስ የሆነች ግለሰብ ዩቲዩብ ላይ ያሉበትን ሀኔታ የሚያሳይ ቪድዮ ለጠፈች። አምስት ጊዜ ተመርምራ ውጤቷ እንዳልመጣና የረሃብ አድማ እንደመታች አሳወቀች።

ቪድዮው አሁን ከዩቲዩብ እንዲወርድ ቢደረግም ሁኔታው በጊዜው ሩስያውያንን አስደንግጦ ነበር። ከዚህ ቪድዮ መለቀቅ በኋላ ነው ሆስፒታሉ የኮሮናቫይረስ ማከሚያ ሥፍራና ከቫይረሰ ነፃ የሆነ ክፍል የተዘጋጀለት።

ሆስፒታሉ እንዲዘጋ መታዘዙ ከመጀመሪያው ስህተት ነበር የሚሉ በርካቶች ናቸው። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሕክምና ባለሙያዎች ለቢቢሲ የሚናገሩትም ይህንኑ ነው። አልፎም የምርመራ ጊዜው መዘግየት ለችግሩ መባባስ ትልቅ አስተዋፅዖ ነበረው።

ቢቢሲ በሆስፒታሉ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች ምን ያክሉ እንደሞቱ ትክክለኛ ቁጥር እንዲሰጠው የሆስፒታሉን ኃላፊዎች ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0