ምስል ኢትዮጵያ ከረዥም ርቀት ሚሳይል በተጨማሪ እጇ ካስገባቻቸው ጀቶች መካልከል ይህ Rafale የሚጠቅስ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ለሚቃጣ ማናቸውም ዓይነት ትንኮሳም ሆነ ጥቃት አስፈላጊውን ምላሽ የመስጠት አቅምና የማይታጠፍ ቁርጠኛነት እንዳለው ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ አስታወቁ። ሰራዊቱ የአገሪቱ የሉአላዊነት መገለጫ ለሆነው የህዳሴ ግድብ ያደረገውና በየእለቱ የሚያደርገው ዝግጅት አይቋረጥም ብለዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጀር ጄነራል መሐመድ ከፋና ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የኢትዮጵያ አለኝታ የሆነው የአገር መከላከያ ሰራዊት አደራውን በብቃት ይወጣል። ከመቼውም ጊዜ በላይ አቅሙን አጎልብቶ ማንኛውንም ጥቃት የማክሸፍ፣ የመመከት፣ አስፈላጊ የሚባለውን ምላሽ በተመጠነ ጊዜ ውስጥ መስጠት የሚችል አቋም ላይ ይገኛል።

Related stories   ለጥቁር ገበያ- ምንዛሬ ክፍያ ብር የሚያስተላልፉ ጎረቤት አገር ያሉ ቅ/ባንኮች ታወቁ

” ሰራዊታችን ለህዳሴው ግድብ ቀደም ሲል አንድ ከቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል። ወደፊትም ይቀጣላል” ያሉት ጀነራሉ ግድቡ በታቀደለት ጊዜ ወደ ማምረት ስራ እንዲገባ የአገር መከላከያ ሰራዊት በተጠንቀቅ ሆኖ ስራውን እንደሚያከናውን ሲገልጹ ሕዝብ ቅንጣት ስጋት እንዳይገባው ቃል በመግባት ነው። ” እኛ የህዝብ ልጆች ነን” ካሉ በሁዋላም ” ሕዝብ አንድ ሆኖ ይቁም” ሲሉም አሳስበዋል።

ቀደም ባሉት ወራት የአየር ሃይል አዛዥ በተመሳሳይ በህዳሴው ግድብ ላይ የሚቃጣ ማናቸውንም ጥቃት የመመከት አቅም መገንባቱን መናገራቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በሁዋላ አየር ሃይል ዘመናዊ በሚባል የጦር አውሮፕላኖች እንዲሁም ተሻጋሪ መሳሪያዎችና ሄሊኮፕተሮች መግዛታቸውን ታማኝ የውጪ አገር ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ከእቅዱ እስከ ግዢው ድረስ መዘገባቸውም አይዘነጋም።

Related stories   ኤታማዦርሹሙ ሱዳን ከተደገሰላት የጦርነት ወጥመድ ይልቅ ለዕርቅ ቁርጠኛ እንድትሆን መከሩ

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአብራሪዎችን አቅም ለማዘመን ከፍተኛ ስልጠና እንዲሰጥ ከፈረንሳይ ጋር ውለታ ገብተው ይህንኑ ተግባራዊ ማድረጋቸው በወቅቱ ተዘገቦ ነበር። ኢህአዴግ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ እንዲፈርስ የተደረገው የኢትዮጵያ አየር ወለድ በአዲስ መቋቋሙ ተመልክቷል።

በሌላ ዜና ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን የታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀጣይ ውሃ ሙሌትን ለማስጀምር የሚያስችል ወሳኝ የግንባታ ምዕራፍ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ማስታወቃቸውን ፋና ዘግቧል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ሃላፊዎች ቡድን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተያዘት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ውሃ ለመሙላት

የሚያስችለው የግንባታ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

Related stories   ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ከአፍሪካ 6ኛ ከዓለም 60ኛ ሆነች

በህዝቡ ሙሉ አቅም እና በመንግስት ጠንካራ ክትትልና ጥብቅ አመራር የታላቁ

ህዳሴ ግድብ ወሳኝ የግንባታ ምዕራፍ ላይ መዳረሱን ጠቁመዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተቀናጀ ርብርብ በሚካሄደው መልካም የግንባታ አፈፃፀም የመጀመሪያውን ምስራች ለማየት መቃረቡን ገልፀዋል።

የግድቡ ግንባታ በርካታ ውጣ ውረዶችን እያለፈ ወሳኝ የግንባታ ዕድገት ምዕራፍ እንዲደርስ፤ በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ በፅናት እየተረባረቡ ለሚገኙት የፕሮጀክቱ አመራሮች እና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይ የግንባታ ዘመን ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ እንዳያውካቸው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ህዝብ እና መንግሥት የጣለባቸውን ታሪካዊ ሃላፊነት በድል እንዲወጡ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *