“Our true nationality is mankind.”H.G.

በ24 ሠዓታት በተደረገ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሠዓታት በተደረገ 4 ሺህ 775 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 156 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 85ቱ ወንዶች ሲሆኑ፤ 51 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

ከእነዚህም 124ቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ 12ቱ ደግሞ የውጭ አገራት ዜጎች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ከ1 እስከ 97 ዓመት ክልል ውስጥ የሚገኝ ነው።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

ባለፉት 24 ሠዓታት በምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 115ቱ ከአዲስ አበባ፣ 7ቱ ከትግራይ ክልል፣ አንድ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ 9 ከኦሮሚያ፣ 2 ከሐረሪ፣ 2 ሰዎች ደግሞ ከሶማሌ ክልሎች መሆናቸውን ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ትናንትና 17 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 361 ደርሷል።

ሌሎች 32 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕሙማን ከፍል ውስጥ ይገኛሉ።

Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ

በአጠቃላይ እስካሁን በኢትዮጵያ 147 ሺህ 735 የላቦራቶሪ ምርመራ ተካሂዷል፤ በጽኑ ህሙማን ክፍል ያሉትን ጨምሮም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 766 ነው።(ኢዜአ)

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0