ሕገወጥ በሆነ መልኩ ወደ ኩዌት ገብተው ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው 259 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ኢትዮጵያዊያኑ ዛሬ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት ሽባባው፣ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ እና ሌሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ በእዚህ ወቅት እንዳሉት ዜጎች ወደ አገራቸው እየተመለሱ ያሉት የኩዌት መንግሥት በሕገወጥ መንገድ የገቡና ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን የተለያዩ አገራት ዜጎች ወደ የአገራቸው እንዲመለሱ መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ ነው።

በእዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍቃደኛ የሆኑትን ዜጎች ምዝገባ በማካሄድ ወደ አገራቸው እየመለሰ መሆኑን አስረድተዋል።

የዛሬውን ጨምሮ በኩዌት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉና ወደ አገራቸው ለመመለስ የተመዘገቡ አንድ ሺህ 150 ወገኖች መኖራቸውንና በተያዘው ሣምንት ወደ አገራቸው ተጠቃለው እንደሚመለሱ አመልክተዋል።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬሕይወት ሽባባው በበኩላቸው እንደተናገሩት ወደ አገራቸው እየተመለሱ ያሉ ዜጎች ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ከቆዩ በኋላ ከኮሮናቫይረስ ነፃ መሆናቸው ሲረጋገጥ ወደ ቤታሰባቸው እንደሚቀላቀሉ አመልክተዋል።

መንግሥት ዜጎቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከማድረግ በተጨማሪ ባለቡት አገር እዚያው ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ በመፍጠር በኩል ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ENA

Related stories   የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ወላጆች በሌላ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሄደው ለመማር ስጋት እንዳለባቸው ገለፁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *