ትህነግ በውስጣዊ የመስመር ልዩነት አደጋ ውስጥ በገባባት ወቅት የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ታስቦ በአንድ ምሽት እንደተቋቋመ የተነገረለት የፌደራል የጸረ ሙስናና የስነምግባር ኮሚሽን ከሁለት አስርት ዓመታት በሁዋላ የሹመኞችን ሃብት በኦንላይን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ የሚያስችለውን አሰራር እያመቻቸ መሆኑንን ዛሬ አስታወቀ።

በመግለጫው ላይ የተሳተፉ እንዳሉት ኮሚሽኑ ከሱማሌ እና አፋር ክልል በስተቀር 500 ሺህ የሚደርሱ ተሿሚ፣ ተመራጭና የሚመለከታቸው አካላት ሃብታቸውን አስመዝግበዋል። መረጃው ቀደም ሲል የነበረው የማንዋል ሁዋላ ቀር አሰራር በማስቀረት በዲጂታል አስተገባበር  ውስጥ ማስገባቱን ይፋ አድርጓል።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

በዚሁ መሰረት የመንግስት ተሿሚዎችና የህዝበ ተመራጮችን ሃብት መዝግቦ ያለ ገደብ ለህዝብ ክፍት የሚሆንበትን አሰራር መዘረጋቱን ነው የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይፋ ያደረገው። አሰራሩን ላማሳለጥና ለማቅለለ ይቻል ዘነድ የዘመናዊ ሃብት ምዝገባ መረጃ ስርዓትን በኦንላይን  ተግባራዊ ማድረጉን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ሁለት ወር ይፈጅ የነበረን የምዝገባ ሂደት ተመዝጋቢው ባለበት ሆኖ  በሁለት ደቂቃ ማከናወን እንደሚቻል አመልክቷል።

የኮሚሽኑ የሃበት ማሳወቅ እና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይ እንደተናገሩት፥ የተዘረጋው ስርአት ኮሚሽኑ የተመዘገበውን መረጃ ለሀብረተሰብ ለማሳወቅና ተደራሽ ለማድረግ ከጊዜና ከወጪ እንዲሁም ከርቀት አንጻር የነበረበትን በርካታ ችግር እንደሚፈታ ፋና ሃላፊውን ገልጾ ዘግቧል።

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

አዲሱ አሰራር የምዝገባ ሂደትን ከማቅለል በተጨማሪ የመንግስት ተሿሚዎችና የህዝበ ተመራጮችን ሃብት ለህዝብ ክፍት የሚያደርግ ነው። ኮሚሽኑ ቀደም ባሉት ዓመታት ይህንኑ አደርጋለሁ እያለ በማርላማና በተለያዩ አውደ ጥናቶች ላይ ሲለፍፍ እንደነበር ይታወሳል። ለምን ተግባራዊ እንዳላደረገ ሲጠየቅ ” አንዳንድ ባለስልጣና ፈቃደኛ አይደሉም” የሚልና የሚያስፈራሩም አካላት እንደነበሩ ተናግሮም ነበር። በተለይ የአገር ደህንነትና መረጃ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ሃብት የሚመዘበርበት በመሆኑ ለመመርመር ሲጠየቅ ያባርሯቸው እንደነበር በአንድ ወቅት አንድ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ሃላፊ ለሪፖረተር መናግራቸው አይዘነጋም።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ዛሬ በኦንላይን የሹመኞችን ሃብት ይፋ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ያስታወቀው ኮሚሽኑ ምን ያህል ከቀድሞው በተለየ መልኩ ቁርጠኛ እንደሆነ ለማወቅ ጥያቄ እንደቀረበለትና ምን መልስ እንደሰጠ በስፋራው የነበሩ ሚዲያዎች አልገለጹም።

ፎቶ – ሪፖርተር ካርቱን ፋይል

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *