“በውል እንደሚታወቀው “ይላል የኖቬል ሰላም ሽልማት ጸሃፊ ኦልቫ ኒዮስታድ ደብዳቤ ” በውል እንደሚታወቀው የኖቤል የሰላም ሽልማት አንዴ ከተሰጠ መልሶ ሽልማቱን መውሰድ ፈጽሞ አይፈቀድም ” ሲሉ የስዩም መስፍንና በሳቸው ዙሪያ ያሉትን ሃሳብና ምኞት በአርማታ ደምደመው ይዘጉታል። አክለውም ሽልማቱን የሰጠው አምኖበት በመሆኑ አሁንም ወደፊትም የጠነከረ እምነቱ ጸንቶ እንደሚቆይ ደምደመዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብን ደጋግሞ በመዋሸት የሚታወቁት አቶ ስዩም መስፍን መቀሌ ካረፉበት ሆቴል ሆነው በሚያስተዳድሩት ሚዲያ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል ሽልማታቸውን እንዲነጠቁ እየተሰራ መሆኑንን ሲገልጹ ጠያቂና የቃለምልልሱ ተደራቢ ተዋንያን ጌታቸው ረዳ ፊታቸው ላይ ኩራት ይነበብ ነበር።

በዚሁ የኩራትና የጅግንነት ስሜት ነበር ክልሉ የሚያስተዳድረው ቲቪ የአንድ ይርቢቢሲ ሪፖርተር አስተያየትን አስራ አንድ ወር ወደሁዋላ በመሄድ አጣሞ የስዩም መስፍንን ቅዠት የሚያጠናክር ዜና ያሰራጨው። ቢቢሲ እንዲህ ያለ “ዜና አላሰራጨሁም” ሲል ቀዳዳዎች መሆናቸውን በቅጽበት ምላሽ ሰጠ። ሚዲያው ይህ ሁሉ ቢሆንም ማስተባበያ አላቀረበም።

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለመሸለም ያሳለፈው ውሳኔ ትክክለኛነት ላይ ዛሬም ፅኑ እምነት እንዳለው የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2019 በይፋ ዛሬ አስታውቋል። ኮሚቴው እንዳለው እንዲህ ያለውን ጉዳይ አስቦትም አያውቅም። ሊታሰብም የሚችል አይደለም።

ስድብን ባልተገባ መንገድ የሚያመርቱት የከፋቸው ወገኖች ዛሬም ይህ ደብዳቤ ይፋ ሆኖ ማስተባበያ አልሰጡም። የኦሮሞ ህዝብን እንወክላለን በሚል በህወሃት ሚዲያዎች ላይ ከሚጣዱት ባንዳዎች መካከል ህዝቄል ገቢሳም የዚህ ዜና አካል ቢሆንም አሁን ድረስ በይፋ ያለው ነገር የለም። ይቅርታም አልጠየቀም። የትግራይ ክልል አስተዳደርም ይህ እንዲስተካከል የወሰደው እርምጃ ስለመኖሩ አልገለጸም።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

ኮሚቴው አንዳንድ አካላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሰጠውን የኖቤል የሰላም ሽልማት “ለመሻር ዳግም እያጤነ ነው”  ሲሉ ላናፈሱት  ወሬ “ማረጋገጫዬን እሰጣለሁ በፊትም ሆነ አሁን ሽልማቱ መሰጠቱን ዳግም ለማጤን አላሰብኩም ወደፊትም ለማጤን ፍላጎት የለኝም” ብሏል። አያይዞም ዛሬ በይፋ ባሰራጨው ደብዳቤ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ሽልማት ከተበረከተ በኋላ መሻርን ፈፅሞ እንደማይፈቅድ ህጉን ጥቅሶ አመልክቷል።

የኖቤል ሽልማት መሰጠት ከተጀመረ ከአሮፓውያኑ 1901 ጀምሮም የአንድም ተሸላሚ ሽልማት አለመሻሩንም ነው ያመለከተው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ትብብር ላደረጉት ጥረት በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለዓመታት የዘለቀው የድንበር የይገባኛል ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ተነሳሽነትን በመውሰዳቸው የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ እንዳደረጋቸው ኮሚቴው መግለፁ የሚታወስ ነው።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ኮሚቴው በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማምጣት ቃል መግባታቸውን በማስታወስ፥ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመቀበል ሀገራቱ አስመራ ላይ የሰላም ስምምነት እንዲፈራረሙ ማስቻላቸውን ነው ያነሳው።

በተጨማሪም ሁሉም ባለድርሻ አካለት በኢትዮጵያ፣ በምስራቅና በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ ላደረጉት አስተዋፀኦ እውቅና ለመስጠትም እንደ ተሸለሙ ኮሚቴው  መግለፁ አይዘነጋም።

አብይ አህመድ በትናንትናው እለት ፓርላማ ቀርበው ” አቡዋራ ይቦናል” ሲሉ ለትውልድ የሚሆን አሻራ እናኑር ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *