ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የጦር ሰራዊቱ ኩዴታ እንዲያካሂድ ተጥይቆ እንደነበር ጀነራል ሳሞራ የኑስ አመኑ!!

የቀድሞው ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ የሕዝብ ዓመጽ መተቀጣጠለበት ወቅት ሰራዊቱ ኩዴታ እንዲያካሂድ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበር ይፋ አደረጉ። አገሬን እስከጠቀመ ድርስ በሙያዬ የምጠቀመውን አደርጋለሁ ሲሉም ተናግረዋል።

ጀነራሉ ይህንን ያሉት ሰሞኑንን ወደ ስራቸው ተመለሱ የሚል ወሬ መናፈሱን ተከትሎ በትግራይ ከሚገኝ አዋሎ ከተሰኘው የዩቲዩብ አምድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ጠያቂው እነማን እንደሆኑ እንዲብራራለት ሲጠይቅ ዝርዝር ውስጥ ያልገቡት ጀነራሉ ” በተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግስት አድርጉ” ሲባሉና ሲጠየቁ እንደነበር ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። የብልጽግና ፓርቲን ስለመቀላቀላቸው ሲጠየቁ ” መስፈርቱን አላውቀውም። ባውቀውም አላሟላም። የጠየቀኝም አካል የለም” ብለዋል።

” ደርግን ወያኔ ብቻ አልጣለውም ይህ ስህተት ነው” በማለት ማብራሪያቸውን ያሰሙት የቀድሞ መኮንን፣ ደርግ ከሕዝብ መነጠሉና በጦርነት መመታቱ እንደጣለው ሲገልጹ ወያኔ እጁ ሰፊ ቢሆንም እህት ድርጅቶችና ህዝብ በህብረት ጥለውታል ነው ያሉት። ዋናው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑንን አስመረውበት አልፈዋል።

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

” መሪና ፖለቲከኛ በተቀያየረ ቁጥር መታኮስ አያስፈልግም” በማለት የምክር ሃሳብ መጠየቃቸውን፣ የቀረበላቸው ጥያቄ ለኢትዮጵያም ሕዝብ ሆነ ለትግራይ ሕዝብ ስለሚጠቅም ልምዳቸውን ማካፈላቸውን ተለሳልሰው ያቀረቡት ጀነራሉ፣ የጠያቂውን ሃሳብ ሲከተሉ አልታዩም። ጠያቂው ደጋግሞ እሳቸው ምክር ሲሉ ያለሳለሱት ሃሳብ የተመቸው አይመስልም። ለዚሁም ይመስላል ጀነራሉ ” ችግሩ ምንድን ነው” ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል።

የሳሞራ ወደ ሃላፊነት መጠራት ወሬ ” የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት አልቻለም። የቀድሞው የህወሃት ሰዎች እየተጠሩ ነው” የሚለውን ዜና ያካተተ ቢሆንም ጀነራሉ ያሉት ግን ” ስወጣ ለመመለስ አይደለም። ይህንን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ማንም ያውቃል። ምክር ተጠይቄ ሰጥቻለሁ። ወደፊትም ከተጠየኩ አደርገዋለሁ። 42 ዓመታት በሙያው አሳልፌያለሁ” በማለት አልፈውታል።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

ኩዴታን አስመክቶ በኦገስት 2016 ጎልጉል የተሰኘው የድረገጽ ጋዜጣ

በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ እንዲካሄድ የማይፈልጉት የአሜሪካ ባለስልጣናት ህወሃት አገር መምራት የማይችልበት ደረጃ ደርሷል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። የሚያደርጉትን ቢያውቁም ለመፍትሄ በተናጠል ተቀናቃኝ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማህበራትን “ምክር” እየጠየቁ ነው። አሁን ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በዚህ ከቀጠለ ኢትዮጵያን ላለማጣት ድንገተኛ የሚመስል ግን የታቀደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሊደረግ እንደሚችልም ፍንጭ እየተሰጠ ነው።

የጎልጉል ታማኝ መረጃ ሰዎች እንዳሉት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) እንዳበቃለት የገመገሙት የአሜሪካ ባለስልጣናት “ከወዲሁ አንድ ነገር ማድረግ አለብን” የሚል አቋም ከያዙ ሰነባብተዋል። ለዚሁም መነሻቸው ህወሃት መልሶ እንዲያገግም ሊረዱት አለመቻላቸውና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የኢትዮጵያን መክሰር አለመፈለጋቸው ነው።

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

“ህወሃት አገር መምራት ካቃተው፣ ኢትዮጵያን ላለማጣት ምን ማድረግ አለብን” ከሚለው መሰረታዊ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዝንባሌያቸው በመነሳት አሜሪካኖቹ በየእርከኑ አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎችን፣ ነፍጥ አንስተው ከሚታገሉ፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ከሲቪክ ተቋማት ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው። ጎን ለጎን ድንገተኛ የሚመስል፣ ነገር ግን የታቀደ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግ ፍላጎት አሳይተው እንደነበር ነው ጎልጉል የገለጸው። ጎልጉል በተመሳሳይ ጀነራል ሳሞራን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የህወሃት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ተጠርተውና በራሳቸው ፍላጎት አሜሪካ መመላለሳቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

ዛሬ ከለውጡ በሁዋላ ሳሞራ የኑስ ያነሱትና ያረጋገጡት መፈንቅለ መንግስት በእነማን አስገዳጅነት ታስቦ እንደነበር ይፋ ባያደርጉም ጉዳዩ ከዚህ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ይታመናል። የጎልጉልን ዘገባ እዚህ ላይ ያንብቡ።