ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

አብይ ስንት መፈንቅለ መንግስት ተሞከረባቸው? ሳሞራ የኑስ ለምን አድበሰበሱት?

ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ መረጃ አቀባይ ዲፕሎማትን እየጠቀሰ ዘወትር ጥብቅ መረጃ በማተም የሚያወቀው ጎልጉል የድረገ ገጽ ጋዜጣ  የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ድረስ የሄዱበትን ጉዳይ በወቅቱ አስነብቦ ነበር። ይህ ያለ አንዳች ማስታወቂያ መረጃዎችን የሚያሰራጨው የድረገጽ ጋዜጣ በወቅቱ መፈንቅለ መንግስት ወይም ኩዴታ ሊደረግ መታሰቡን ነበር ያተመው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን ከሥልጣን ለማውረድ በሌላ አነጋገር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የአሜሪካንን ይሁንታን ፍለጋ ነው ቁልፍ የህወሃት ሰዎች ወደ ስፍራው አቅንተው ነበር። በወቅቱ የባለስልጣኑንን በአስራ አንደኛ ሰዓት እዛ መታየት ” ቤት ሊገዙና ኑሯቸውን ሊያደላድሉ” በሚል ነበር ሲዘገቡ የከረሙት። ጎልጉል ግን ” የለም ጉዳዩ ሌላ ነው” ሲል አሁን ላይ ይፋ የሆነውን ዘገባ ይዞ ወጣ።

ህወሃት ሆን ብሎ የተሳሳተ ዜና አለያም የተቀራረበ ዜና በምናሰራጨት ደርሼበታለሁ የሚለው ጎልጉል ጁን 28 ቀን 2018 ባተመው ዜና  አስረግጦ የተናገረው ነገር ቢኖር ” ‘የቀን ጅቦች’ በሚል ዘርና አካባቢ ሳይለይ በጥቅል ለሌቦች ሁሉ  የተሰጠውን ስም በተለይ ለአንድ የህብረተሰብ ክፍል ነዋሪዎች ባቻ እንደተሰጠ በማስመሰል ራሳቸውን ህዝብ ጉያ ሥር በመክተት ‘የትግራይን ህዝብ ከመሪ ድርጅታቸው ህወሓት ነጥለው ሊያጠቁ ተነስተዋል’ በሚል  ወደ አሜሪካ ያቀናው ህወሃት ከከበበው ፍርሃት በመንሳት መልሶ የፖለቲካ ስልጣኑንን ለመረከብ ነበር ወደ አሜሪካ ያቀና ” የሚለውን ነበር።

ጋዜጣው ይቀጥልና ” በዚሁ መሠረት አሜሪካ ያቀኑት የህወሃት ቁልፍ የተባሉ ሰዎች ‘ዶ/ር ዓቢይን በሰላማዊ መንገድ እንድናስወግድ ፍቀዱልን’ ሲሉ ነው ጥያቄ ያቀረቡት። የመረጃው ምንጭ እንዳሉት ‘አገሪቱና ቀጣናው አሁን በመበታተን አደጋ ውስጥ ናት’ በማለት የህወሓት ሰዎች ‘የማረጋጋትና ሰላም የማስፈን ልምድና ክህሎት ስላለን ይህንን ሥጋት ማስወግድ እንድንችል ይሁንታ ስጡን’ ሲሉ ነው የተማጸኑት” ሲል ሰላማዊ ኩዴታ ለማድረግ የሄዱበትን ርቀት ያትታል።

በዶ/ር ዓቢይ ሕይወት ላይ ምንም ሳይደርስ “በሰላማዊ መንገድ ጉዳዩ ይከናወናል” ያሉት የህወሓት ሰዎች፤ የመፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ በኋላ “የአሜሪካንን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ አዲስ አስተዳደር እናዋቅራለን፤ በቀጠናው የአሜሪካንን ፍላጎት ተግባራዊ እናደርጋለን” ሲሉም ከኩዴታው በኋላ የሚያከናውኑትን በዝርዝር ማስረዳታቸውን ጎልጉል ምንጬ ያላቸውን ዲፕሎማት ጠቅሶ አስታውቋል።

መረጃውን  ያቀበሉት ዲፕሎማት እንዳሉት ከሆነ የህወሓት ሰዎች ዶ/ር አብይ አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ እያመሯት እንደሆነና ህወሓት በዚህ አካሄድ አገሪቱ ልትበታተን ትችላለች የሚል ስጋት እንደገባው መስሎ ላቀረበው “መንግስት ልገልብጥ” ጥያቄ ከአሜሪካ በኩል የተሰጣቸው መልስ “አርፋችሁ ተቀመጡ” የሚል እንደነበር ከሪፖርቱ ለማወቅ ተችሏል።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

ይህ ዶ/ር ዓቢይን ከሥልጣን ለማስወገድ የቀረበ ሃሳብ ውድቅ መሆኑ ከተሰማ በሁዋላ የቅዳሜው ሰኔ 16 ዓቢይን የመግደል ሙከራ  ስለመደረጉ የተጠየቁት መረጃ አቀባያችን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ጋዜጣውም በዚህ ጉዳይ የጨመረው አስተያየት የለም። ከዛ በሁዋላ ግን በግልጽ እንደታየው በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መተራመስ ተፈጠረ። መፈናቀል በዛ። አፍንጋጭና ለህግ አንገዛም የሚሉ የአካባቢ ጎበዞች ተፈለፈሉ። ቀደም ሲል የነበረው መዋቅር አልታዘዝም ብሎ በሴራ አገሪቱንና ህዝቡን መከራ ውስጥ እንዲወድቁ ሆነ። ለዚህ ሁሉ ቀውስ ” ዋናው ተዋናይ ማን ነው” ለሚለው ሕዝብ በአደባባይ በየአውዱ፣ ባለስልታናትና የድረገጽ አምደኞች እንዲሁም የዩቲዩብ መገናኛዎች ህወሃትን ፊት አቁመው ወነጀሉ። መንግስትም ሲብስበት ፊት ለፊት መናገር ጀመረ።

ህወሃት ዲጂታል ወያኔን ማደራጀቱ በዋናነት ” ይህ በዕዝና ቁጥጥር የሚመራ ኃይል ዋና ትኩረት የሚያደርገው በለውጡ ዙሪያ ያሉትን አመራሮች ማጠልሸት፤ የሕዝብ ድጋፋቸውን ማምከን፤ ከተቻለም ሕዝብ እንዲነሳባቸው ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ረቂቅ ስልት በሚበትኑት መረጃ ሕዝብ ከሕዝብ ጋር እንዲጋጭ፤ ደም እንዲቃባ፤ ሰላም እንዲደፈርስ፤ ሕዝብ እንዲፈናቀል፤ ሕዝብ በመሪዎቹ ላይ እምነት እንዲያጣ በማድረግ “በአመራር ላይ ያለው ኃይል አገር ማስተዳደር አቅቶታል” በሚል በአገር ውስጥና በውጪ ተዓማኒነቱን ማሳጣት ነው” በሚል የኔት ወርኩን አብይ ተጋብር የሚጠቁሙ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ገለልተኛ የክልሉን ነዋሪ ዋቢ አድርጎ ” ምን በተግባር ያልታየ እንዳለ ይኸው ሚዲያ በወቅቱ በሌላ እትም ጠይቋል።

” ከኔ በላይ የተሰደበ አለ” ሲሉ ዶክተር አብይ በቅርቡ በፓርላማ ጠቆም አድርገው ያለፉት የ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል” ስልት፤ “አቧራ” ና ” ረብ የለሽ” ብለው ዛሬ ላይ ቢያጣጥሉትም በማጠልሸቱ ዘመቻ እሳቸውም ሆኑ መንግስታቸው ብዙ ዋጋ ስለመክፈላቸው ማስተባበል ግን አይቻልም። ዲጂታል ወያኔ ነጥሎ እሳቸውን በማጠልሸትና ከህዝብ ለመለየት ያካሄደው ዘመቻ ስኬታማ መሆኑንን ከገመገመ በሁዋላ ” አገሪቱን እንድናረጋጋ ህዝብ ዳግም መንግስት እንድንሆን ጠየቀን” የሚል ዜናም ማስነገር ጀምረው ነበር።

Related stories   "በፕሮፓጋንዳ እስካሁን የተወናበድኩት ይበቃኛል ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ይገባል ... ወጣቱን ያለ እድሜው ህይወቱን ይቀጩታል"ሌ.ጀ ዮሐንስ

ህወሃት ከብልጽግና ተባረረ ወይስ ራሱ ወጣ የሚለው ጉዳይ ለጊዜው በይደር ይቆይና፤ ከፍቺው በሁዋላ እየጦዘ የሄደው የህወሃትና የብልጽግና ፓርቲ ንትርክ በጋመበት ወቅት ዶክተር ደብረጽዮን ” ልዩነቱ የፖለቲካ ነው” ሲሉ ግልጽ አቋም ይዘው የይለያል እንቅስቃሴ ውስጥ መግባታቸውን በትግራይ ቲቪ አስታውቀዋል።

ይህ ከሆነ በሁዋላ በትግራይ የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ፣ አለመስማማትና በአንዳንድ ጥያቄዎች መነሻነት ግብግብ መሰማት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ ” ከኢትዮጵያ ትግራይ ብቻ ሰላማዊ ቀጣና” የሚለው ዜና ሰፊ ሽፋን እነዲያገኝ የሚፈለገው ለአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለውጪው ፖለቲካ ግብዓት ስለመሆኑ በርካቶች ገልጸዋል። በገሃድም ደጋግመው የህወሃት ጥንካሬ ማሳያ መሆኑንንም ደጋፊዎቹም ባለስልጣኖቹም አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እያለና ፖለቲካው ወዴት ያመራል የሚለው ጉዳይ አሳሳቢ በሆነበት ወቅት ላይ ነው እንግዲህ የቀድሞው ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ ” መፈንቅለ መንግስት እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦልን ነበር” ሲሉ አዋሎ በተባለ ሚዲያ ይፋ የተናገሩት። የጦር ሰራዊቱን ታማኝነትና ለህገ መንግስቱ ተገዢ መሆኑንን ለማስረዳት ” መፈንቅለ መንግስት እንድናካሂድ ተጠይቀን ነበር” ሲሉ የተናገሩት። ቀደም ሲል የተባለውን ያመኑት።

ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በሁዋላ የዶከተር አብይን መንግስት በቡቃያ እድሜው ለመብላት የታሰበውንና የከሸፈውን ይሁን አስቀድሞ የታቀደውን መፈንቅለ መንግስት በውል ሳይለቱ ጣይቄው መቅረቡን ጀነራሉ መናገራቸው ለሕዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው ደወል መሆኑንን ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ ቀደም ሲል ከሰማናቸው ዘረጃዎች ስነነሳ ሁለት ያልተሳኩ ሙከራዎች ተካሂደዋል።  እጅግ ውድ የሆን የአዴፓ መሪዎች ያለፉበትና  ጀነራል ሰዓረ የተገደሉበትን ሴራ ሳይጨምር ማለት ነው።

አንደኛው ጎልጉል ይፋ ያደረገውና አዲሱ መንግስት ገና ሳይጠና፣ የህወሃት መዋቅር ሳይበታተን አሜሪካን ፈቃዷን የተጠየቀችበት የመፈንቅለ መንግስት ሃሳብ ሲሆን፣ ሌላኛው ግን የሕዝብ አመጹ ነዶ፣ እህት ድርጅቶችም አመጹን በመምራት ተባባሪ ከሆኑ በሁዋላ ለአርባ ቀን ገደማ በዝግ ንትርክ ሲካሄድ የተወጠነው ነው።

ሳሞራ የኑስ ” እኔ ወታደር ነኝ” እያሉ በመደጋገም በመግለጽ ” ወታደር መሆን ማለት ፖለቲካውን አለማወቅ አይደለም” በማለት እያከሉ ” መፈንቅለ መንግስት እንድናካሄድ ጠይቀውን ነበር” ያሉት የኩዴታ ሃሳብ ጊዜው እየጨለመ ሲሄድ እነ ጄነራል ጻድቃን ካቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ ደጅ የሚስለፍ ይመስላል።

” መከላከያው፣ ደህንነቱ፣ ፖሊስና የጸጥታ መዋቅሩ ሃላፊነት ወስዶ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ሁሉን የሚያካትት መንግስት ይቋቋም። ይህ ሁሉንም ወገን መተማመኛ ይሰጣል ” የሚል ጥቅል ሃሳብ የያዘው ፕሮፖዛል ለአሜሪካ የቀረበ ነበር። ጄነራሉ ራሳቸው በሚዲያ ቀርበው ተንትነውታል። ጽሁፉም ተሰራጭቷል። ይህ እሳቸው ያቀረቡት ሃሳብ ተግባራዊ ካልተደረገ አገሪቱ ብሎም ምስራቅ አፍሪካ ወደ መተራመስ ያመራል የሚል ድምዳሜ ያነገበ ነበር።

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

እንግዲህ ጀነራል ሳሞራ በጡረታቸው ዝመን ላይ ሆነው ” አገሬን በሙያዬ አግዛለሁ። ለሕዝብ ከጠቀመ ነገም እቀጥላለሁ” በሚል የዜግነት ግዴታ እንጂ የብልጽግና ፓርቲ አባል አለመሆናቸውን ለማስታወቅ በሰጡት መግለጫ ከየአቅጣጫው ሲነገር የነበረውን ዱለታ አፈንድተውታል።

ዋልታ ረገጥ ፖለቲከኞች፣ ዘረኛ አክቲቪስቶች፣ እንደ አሸን የፈሉት ሚዲያዎች እየተቀባበሉ ፣ ለውጡ ያልተቀበሉ አመራሮች፣ ስጋት የገባቸው አባላት፣ ጥቅማቸው የቀረባቸው … የዶክተር አብይን አመራር ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ነው መለብለብ የጀመሩት። የተወረወረለትን ሁሉ የሚያፍሰው ማህበራዊ ሚዲያም በዓላማና ባለማወቅ ሁሉን እያግበሰበሰ የአዲሱን መንግስት አሳር አብዝቶ ነበር።

በዚህ ሁሉ ግን እየተውተረተረ ራሱን ያጠነከረው አዲሱ መንግስት ዛሬ ላይ ሃይሉ መጠንከሩን በርካቶች ዋና ተቀናቃኝ የሚባሉትን  ጨምሮ ቢያምኑም፣ ኮሮና፣ ኮሮናን ተከትሎ የሚመታው ማህበራዊ ቀውስ፣ የግብጽ የጦርነት አዋጅ፣ የሱዳኖቹ ተለዋዋጭ አቋምና የህወሃት ማምረር ተዳምረው ሌላ ፈተና ደቅነዋል። ሕዝብ አስተውሎ መራመድ ያለበት ጊዜ ላይ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ምክንያታዊ መሆን ይገባዋል። በተለይም ህወሃትና አንድና ሁለት አክራሪ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየፈጠሩት ያለው ህዝብረት ውጤት ባያመጣም አገሪቱ ከግብጽ ጋር ከገባችው ውዝግብ አንጻር ጦሱ የከፋ ስለሚሆን ህዝብ አሁንም ደግሞ የሚያስበበት ውቅት መሆኑንን የገባቸው ይመክራሉ።

ቤተመንግስት እንደታጠቁ የመጡትን አፈንጋጮች ሳይጨመር በገሃድ የሚታወቅ ሶስት መፈንቅለ መንግስት መክሸፉ ሃቅ ነው። ለውጡ ሲፋፋምና አብይ ወደ ስልጣን እንደሚመጡ ሲታመን፤ አብይ ስልጣን በያዙ ማግስትና ውድ የአማራ ክልል መሪዎችና ” ኢትዮጵያ ስላለ ሞተ” ሲል ልጅ በሲቃ የመሰከረላቸው ጀነራል ጸአረ እንዲሁም ይህ ኦፕሪሽን ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቀጣይ ሚናውን ለመጫወት በድሮው አውሮፕላን ማረፊያ መኮንኖች ሰፈር ለኦፐሬሽን በዝግጅት ላይ እንዳለ የሟሟው ሃይል የወጠኑት የውክልና መፈንቅለ መንግስት ይጠቀሳሉ። ከግድያ ሙከራም ተርፈው አብይ ዛሬ ዛፍ እየተከሉ አሉ። ሕዝብም እያደር እየገባው ያለ ይመስላል።