“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ውይይትን በተመለከተ ያላትን አቋም ግልፅ አደረገች

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሶስትዮሽ ውይይት ትናንትናም ቀጥሎ ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ውይይትን በተመለከተ አቋሟን ግልፅ አድርጋለች።

የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ላይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ በሁለተኛ ቀን ውይይት ኢትዮጵያ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያላትን አቋም ግልፅ ማድረጓን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል እና ዓመታዊ የስራ ክንውን መመሪያዎች ዙሪያ እውነተኛ የሆነ ውይይት እና ድርድር ለማድረግ ያላትን ቁርጠኛ አቋም በመግለፅ፥ በሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ደረጃ ዳግም የተጀመረውን ውይይት በበጎ እንደምትመለከተው አስታውቃለች።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

ኢትዮጵያ ሶስቱ ሀገራት የተፈራረሙት የህዳሴ ግድብ የስምምነት መርሆዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ እንደምትፈልግም በአቋሟ አስታውቃለች።

የታዛቢዎች ሚና ከታዛቢነት ሊያልፍ እንደማይገባ በመግለፅ፥ አደራዳሪ አካል እና ተሞክሮዎችን የሚያካፍሉ ከተፈለገም ሶስቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ ደርሰው ጥያቄ ሲያቀርቡ ብቻ መሆን እንደሚገባውም አስታውቃለች።

የሶስቱ ሀገራት የህግ እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ከየካቲት 4 እስከ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ ያቀረቡት ሰነድ የድርድሩ መሰረት ሊሆን እንደሚገባ ያስታወቀች ሲሆን፥ ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል እና ዓመታዊ የስራ ክንውን መመሪያን በተመለከተ የራሷን አማራጭ ማቅረቧ እና በሱዳንም አቋማን የሚያንፀባርቅ ሰነድ አስገብታለች ብሏል መግለጫው።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ባሳለፍነው ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም በተጀመረው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ ከመግባባት እንደተረሰው የህዳሴው ግድብ ድርድር እሰከሚጠናቀቅ ድረስ በኢንተርኔት የሚደረገው የቪዲዮ ውይይት ከማክሰኞ፣ አርብ እና እሁድ ውጪ ባሉት ሁሉም ቀናት ቀጥሎ የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

ኢትዮጵያ በሶስትዮሽ ውይይቱ በሁሉም አካላት ዘንድ መተማመን ሊኖር እንደሚገባ ታምናለች ያለው መግለጫው፥ ይህም የሶስትዮሽ ድርድሩ የተሳካ እንዲሆን ለማስቻል እንደሆነም አስታውቃለች።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ሆኖም ግን ግብፅ አሁን እየተካሄደ ባለው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ እያንፀባረቀች ያለው አቋም እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት ለሁለተኛ ጊዜ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የውጭ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲፈጠር እያደረገች ያለው ጥረት በድርድሩ ላይ ግልፅነት እና መተማመን እንዳይኖር የሚያደርግ መሆኑም ኢትዮጵያ አስታውቃለች።

ስለዚህም በድርድሩ ላይ የሚሳተፉ ሁሉም አካላት እውነተኛ የሆነ ውይይት እና ድርድር በማድረግ ከስምምት እንዲደረስ እንደትምፈልግ የገለፀችው ኢትዮጵያ፥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሌሎች ተደራዳሪዎች ለዚህ እንደሚያበረታቷቸው እምነቷ መሆኑን ገልፃለች።

(ኤፍ ቢ ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0