“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሱዳን የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት እንደምታከብርና የግዳሴውን ግድብ እንደማትጋፋ አስታወቀች፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ግድ ነው

ኢትዮጵያ የሕዝቦቿን ዕድገት የማረጋገጥ ሉዓላዊ መብት እንዳላት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ መሐመድ ገለጹ። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን መብት ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት አክብራ መቆየቷንም አስታውሰዋል።

ሚኒስትሯ ከሱዳን ቴሌዥዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳረጋገጡት አገራቸው ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ባስከበረ መልኩ የተፈጥሮ ሀብቷን የማልማት መብቷን ተጋፍታ አታውቅም። በተለይ እንደ አውሮፓያን አቆጣጠር ከ2011 አንስቶ የሕዳሴውን ግድብ በተመለከተ ያላትን መብት ስታከብር መቆየቷን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ ግድብ ገንብታ ኤሌክትሪክ በማመንጨት ሕዝቦቿን ተጠቃሚ የማድረግ ሕጋዊ መብት እንዳላት ብናምንም፤ ሂደቱ ዓለም አቀፍ መስፈርትን ያከበረ እንዲሆን እንፈልጋለን ብለዋል። ሱዳን በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት በመመራት የታችኛውን የተፋሰስ አገሮች ሳይጎዱ በውኃ ሀብታቸው መጠቀም እንዳለባቸው ታምናለች ብለዋል።

አገራቸው የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ አቋሟን ስታንጸባርቅ መቆየቷን ያወሱት ሚኒስትሯ፤ ሱዳን ግድቡ የማይዋዥቅ የውኃ ፍሰት እንዲኖረው፣ ጎርፍ እንዳይኖርና የናይል የውኃ ድርሻዋ እንዲጠበቅ ለማድረግ ስትጥር መቆየቷን አስታውሰዋል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ኢትዮጵያ የግድቡን ደህንነት ለማረጋገጥ ያደረገችው ማሻሻያ ሥጋቱን መቀነሱንና አስተማማኝነቱም ከግብፅ የአስዋን ግድብም ሆነ ከሱዳን የሮዘሪ ግድብ የተሻለ መሆኑን አስረድተዋል። ግድቡ የተገነባበት ዐለታማ መሠረት ከሌሎች ግድቦች ከፍ ያለ ደህንነት እንዲኖረውና የግንባታው የቴክኖሎጂ ደረጃም ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እንደሚጣጣም አረጋግጠዋል።

ሱዳን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሁለት ምክንያቶች ደብዳቤ ማስገቧቷንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ቀዳሚው ምክንያት በግድቡ ጉዳይ ዋነኛ አጋር በመሆኗ ቀጣዩ ደግሞ በድርድር ሂደቱ ሱዳን የሁለቱ አገሮች አደራዳሪ ናት የሚለውን ውዥንበር ለማጥራት ነው ብለዋል።

ሱዳን በግድቡ የግንባታ ሂደት ዋነኛ አጋርና ፍላጎቷ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነ አመልክተዋል። የግድቡን አሞላል በተመለከተ የሚደረገው ድርድር ለሱዳን ጠቃሚ መሆኑንም ጠቁመዋል። ግድቡን በተመለከተ ሱዳን ጥቅምም ሥጋትም እንዳላትና በሦስቱ አገሮች መካከል የሚደረገው ድርድር መቋጨት ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመዋል።

Related stories   ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የውኃ አጠቃቀም ቻርተርና የናይል አጠቃቀም የመርሆ ሥምምነት መሠረት በመጀመሪያ ፍትሐዊና እኩል የውኃ ተጠቃሚነት ሊኖር ይገባል ብለዋል። ሱዳን ድርድሩ እንዲቀጠል በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ አማካይነት ከሁለቱ አገራት መሪዎች ጋር ያደረገችው ውይይት አዎንታዊ ምላሽ ማግኘቱን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

የሱዳን የውኃና መስኖ ሚኒስትር ዶክተር ያሲር አባስ የግድቡ ዲዛይን አስተማማኝ ደህንነት ባለው መንገድ እንዲከናወን ስትጥር መቆየቷን ተናግረዋል።

አገራቸው ግድቡ ከሁለቱ አገሮች በተለየ ተጠቂ በመሆኗ በግንባታው ዋነኛ አጋር መሆኗን የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ የግድብ ግንባታ ያደርሳል ተብሎ ከሚታሰበው ጉዳት ይልቅ፤ ጥቅሙ የላቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በድርድሮች ሂደት የግብፅንና የኢትዮጵያን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ ግድቡ እውን እንዲሆን ሥንሰራ ነበር ብለዋል።የሮዘሪ ግድብ ህልውና በአጠቃላይ የተመሠረተው በሕዳሴው ግድብ አስተማማኝነት ላይ በመሆኑ በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ዶክተር አባስ አመልክተዋል።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

ድርድሩ ሁሉንም በሚጠቅም መልኩ እውን መሆን እንዳለበትና፤ ኢትዮጵያ ከግድቡ ኤሌክትሪክ በማመንጨት ስትጠቀም ሱዳን ደግሞ ያለችግር ግድቧን በማስተዳደር ከተስተካከለው የውኃ ፍሰት ተጠቃሚ ትሆናለች በማለት አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ከምታመነጨው ኃይል በዓመት 900 ሚሊዮን ዶላር ስታገኝ ግብፅና ሱዳን ደግሞ በዝቅተኛ ክፍያ የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት እንደሚችሉ ጠቅሰዋል። በግድቡ አማካኝነት የሚለቀቀው አስተማማኝ የውኃ ፍሰት ሱዳን ከዚህ በፊት ያልተጠቀመችበትን የናይል ሀብት እንድትጠቀም ያስችላታል ብለዋል።

በዚህም ሱዳን የምታመርተውን ሰብል ለኢትዮጵያና ግብፅ በጥሩ ዋጋ መሸጥ ትችላለች በማለት ጥቅሙን አብራርተዋል። የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሂደትና የውኃ አሞላል ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንደሚያስችላት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሚኒስትሮቹ የግድቡን ግንባታ ቴክኒካዊ ሂደት በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ዜና መሠረተ ቢስ መሆኑን ገልጸዋል። የግድቡ ግንባታ አስተማማኝና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እየተከናወነ በመሆኑም አገራቸው ሥጋት እንዳላደረባት አስታውቀዋል።

ENA

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0