በ24 ሰዓታት ውስጥ 179 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

society

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 845 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ በ179 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 345 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አስታውቅዋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች መካከል 176 ሰዎች ኢትዮጵያውያን፤ 3ቱ የዉጭ ዜጎች ሲሆኑ፥ የእድሜ ክልላቸውም ከ2 ወር እስከ 80 ዓመት የሆነ 116 ወንዶች እና 63 ሴቶች ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 111 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 23 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 11 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 5 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከድሬ ዳዋ ከተማ እና 1 ሰው ከሀረሪ ክልል መሆናቸውንም አስታውቅዋል።

በትናንትናው እለት በቫይረሱ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉም የታወቀ ሲሆን፥ ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 የሚሆነው በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ በሁለቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውም ታውቋል።

ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 57 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 50 ሰዎች (41 ከአዲስ አበባ፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 3 ከአፋር ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 545 መድረሱንም ዶክተር ሊያ አስታውቅዋል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ181 ሺህ 349 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 345 ደርሷል።

አሁን ላይ 2 ሺህ 741 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 30 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 545 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ57 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

Related stories   ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው፤ ጤፍ፣ ሽንኩርት፤ዘይት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *