ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ለነዋሪዎች ምርቱን ማቅረብ ለመጀመር የመጨረሻው ምእራፍ ላይ እንደሚገኝ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ። የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ማምሻውን የፋብሪካውን የሙከራ ስራ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ስርጭቱን ለመጀመር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንደተመለከቱ የገለፁት ኢንጂነር ታከለ፥ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢገጥሙም ስራውን በብቃት ማጠናቅ መቻሉን አመልክተዋል።

ይህም እውን እንዲሆን አስተዋፅኦ ለነበራቸው “ቀንና ለሊት ሳይሉ በብርቱ የስራ መንፈስ ስራቸውን ላከናወኑና ለእቅዱ ስኬት በስራው ላይ እየተሳተፉ ላሉ ሰራተኞች ከልብ የመነጨ አድናቆትና አክብሮት አለኝ” ብለዋል።

“የነዋሪዎቻችን ችግርን እየቀረፍን፤ አዳዲስ ሀሳቦችን እየተገበርን አዲስን በአዲስ መንገድ እንገነባለን” ብለዋል። “የእቅዶቻችን ስኬት፤ በማከናወን ላይ ላለናቸውና ለማከናወን ላሰብናቸው ፕሮጀክቶች ጉልበትን የሚሰጡ ናቸውም” ነው ያሉት።

የዳቦ ፋብሪካው በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ፥ለበርካታ የከተማችን ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡

ኤፍ ቢ ሲ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *