በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ሩጫ እየከረረ ነው። በተከታታይ ሳምንታት የሚያሳየው የአሃዝ ለውጥ ጉዳዩ ወደ ከፍተኛውና ወደተፈራው ጫፍ እየገፋን ነው። ዛሬ ይፋ የተደረገው የጤና ሚኒስትር ሊያ እለታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው ተጨማሪ 176 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል።  የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል። እንደተለመደው ከአስከሬን ምርመራ የተጠኡ መሆኑም ተረጋግጧል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በ5,636 ሰዎች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰባ ስድስት (176) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆናቸው ታውቋል። በዚሁ ስሌት የአጠቃላይ ተጠቂዎች ቁጥር 3521 ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አምስት (75) ሰዎች (31 ከአዲስ አበባ፣ 28 ከሶማሊ ክልል፣ 10 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 1 ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስድስት መቶ ሃያ (620) አድርሶታል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር ስልሳ (60) አድርሶታል፡፡ እንደተለመደው ሚንስትሯ ህብረተሰቡ ራሱን ባገኘው አጋታሚ ሁሉ እንዲጠብቅ አደራቸውን አስተላልፈዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *