“Our true nationality is mankind.”H.G.

ይድረስ ለክቡር ጠሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ! ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ምን እየሠራ ይሆን?

  • Guangul Teshager J – Opinion

ግብፅ ለፀጥታው ም/ቤት UNSC አቤት ማለቷ ይነገራል። አሜሪካ እና እንግሊዝን አማክራ ይቅረብ እንደግፍሻለን አንቺ ሎቢውን አጧጡፊ አይዞሽ ተብላ እንዳቀረበችው ለመገመት ነቢይ መሆን የለብኝም። የአሜሩካ እጅ እንዳለበት አሜሪካ እስካሁን ከያዘችው አቋም ብቻ ተነስቶ መገመት ይቻላል። የፀጥታው ምክር ቤት ከመከረበት በኋላ እንግሊዝ እና አሜሪካ ግብፅን እንደሚደግፉ፣ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ረቂቅ ውሳኔ (Draft resolution) ምናልባትም ማዕቀብን ያካተት በሌላ አባል ሀገር በኩል እንዲቀርብ እንደሚያደርጉ ሳይታለም የተፈታ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሶስቱ ሌሎቹ ቋሚ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ማለትም ሩሲያ፣ ቻይና እና ፈረንሳይ በግብፅ ሎቢ ተደርገው የሀሰት የይስሙላ ገለልተኛ ነን ለማለት፣ እንዲሁም ግብፅን ላለማስቀየም ለኢትዮጵያም እኛ አልወገንም ለማለት ድምፀ ተዐቅቦ Abstention ያደርጉ ይሆናል ብሎ መጠርጠር ብልህነት ብቻ ሳይሆን ተገቢም ነው። የፀጥታው ምክር ቤት አምስቱ ቋሚ የሆኑ የማይለወጡ {Permanent} አባላት እና አስር Non-permanent የሚለዋወጡ ቋሚ ያልሆኑ አባላት በድምሩ አስራ አምስት አባላት አሉት። በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቻርተር አንቀፅ 27 መሰረት ድምፅ አሰጣጡ ላይ እያንዳንዱ አባል አንድ ድምፅ ቢኖረውም አምስቱ የፀጥታው ምክር ቤት (UNSC) ቋሚ አባላት (Permanent Members) ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን (Veto Power) ስላላቸው አንዳቸው ቬቶ ካደረጉት የቀረበው ረቂቅ ውሳኔ ( Draft resolution) ውድቅ ይሆናል። ከአምስቱ ቋሚ አባላት ድምፀ ተዐቅቦ Abstention ቢኖርም ከአስራ አምስቱ አባላት ዘጠኙ ከደገፉት ውሳኔው ተግባራዊ ይሆናል። ጉዳዩ የሚመለከተው አገር የፀጥታው ምክር ቤት አባል ከሆነ ድምፅ የመስጠት መብት የለውም (Chapter VI, Para 3 አንቀፅ 52)
ስለዚህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቤት መስራት ያለበት በግብፅ እና በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ ወይም በእጅ አዙር በሌላ ሀገር ተረቆ የሚመጣ ውሳኔ Resolution ቻይና እና ራሺያ ወይም ከሁለቱ አንዱ በቬቶ ውድቅ እንዲያደርጉት ከባድ ሎቢ ማድረግ ነው። ቻይና ወይም ራሺያ ድምፀ ተዐቅቦ Abstention ቢያደርጉም ከ15ቱ አባላት በዘጠኝ አባላት ከተደገፈ ውሳኔው ስራ ላይ ይዋል ብሎ መፍቀድ ማለት ነው። በውጤቱም ኢትዮጵያ ትጎዳለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ሰዎች በእውቀት ሳይሆን ወያኔ በታማኝነታቸው ብቻ የሰበሰባቸው ስለሆኑ አቶ ገዱን በዚህ አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ ላይ በተገቢው መንገድ በእውቀት ላይ ተመስርተው ያግዙታል የሚል እምነት የለኝም።
የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት {UNSC} በአሁን ወቅት ቋሚ ያልሆኑ ለሁለት ዓመታት በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ By the UN General Assembly ተመርጠው በአባልነት ያሉ አስሩ ቋሚ ያልሆኑ አባላት (Non Permanent Members)
የሚከተሉት አገሮች ናቸው

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

1. Belgium (2020)
2. Dominican Republic (2020)
3. Estonia (2021)
4. Germany (2020)
5. Indonesia (2020)
6. Niger (2021)
7. Saint Vincent and the Grenadines (2021)
8. South Africa (2020)
9. Tunisia (2021)
10. Viet Nam (2021)
እንግዲህ እንደ አንድ ተራ (ምክትል ተራ) ዜጋ ይቺን ሚጢጢ ጥናት (Modicum research) ሰርቻለሁ። እኔ በግሌ ከአንዳንድ የሚኒስቴረ
መ/ቤት ቁልፍ ሰራተኞች፣ አምባሳደሮች ጋር በነበረኝ ትውውቅ ብዙ ታዝቤያለሁ። በጣም አዝኛለሁም። አንዳንዴ አልቅስ አልቅስ ይለኝም ነበር። እናም ግብፅ በዴፕሎማሲው መስክ እጅግ በጣም በልጣናለች። ትልቁ የግብፅ ጥንካሬ በችሎታ ያምናሉ፣ እንደ ሸሚዥ ወያኔ እንደሚያደርገው ሰው እይቀያይሩም። ስራቸው ቀጣይነት Continuity አለው። ቴሌ ስሰራ በቴሌ ጉዳይ ስብሰባ ላይ ሳገኛቸው እኔ በዚያ ጉዳይ ስሰበሰብ አስረኛው ሰው ልሆን እችላለሁ። እነርሱ ግን እንደ ሰላይ ቢጤም ናቸው መሰል ቀደም ሲል በዚያ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙትን እያንዳንዱን እያነሱ እገሌ ደህና ነው እያሉ ይጠይቁኛል። በቡድን ነው የሚመጡት። በጣም የተደራጁ ናቸው። እኛ ሀገር የአስተሳሰብም ድህነት ስላለ እንደ ሀገር ጥቅም ሳይሆን ስብሰባው ላይ እንደሚሳተፈው ሰው የግል ጥቅም አበል ማግኛ ስለሚታይ ዘንድሮ እገሌ አገር አይቶ ይምጣ ተብሎ ነው ሰው ለውጭ ስራ የሚመደበው። ችግር ላይ ነን። ፈታኝ ወቅት ላይ ነን። ዕውቀት ያላቸው ሰዎች በሁሉም መስክ የሉንም። ይህንን ክሽፈት ያደረሰው በዘር፣ በድርጅት አባልነት እየሾመ አገር ያግማማው ወያኔ ነው። ኡትዮጵያ በሁሉም መስክ ሰው ያስፈልጋታል። የወያኔን ሹማምንት አራግፈን ውጭ ሀገር ላለው ዲያስፖራ ሁሉ አገሩን እንዲያገለግል ጥሪ እናድርግ
ቸር ይግጠመን

??
====

Related stories   የተላላኪው ጠበቃዎች

Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ

Guangul Teshager J Face book

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0