የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት በአገራችን ውስጥ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት መሰረት በማድረግ በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መደረክ አካሂደዋል፡፡

ተቋማቱ ለውይይቱ መነሻ ይሆናል ያሉት ሀሳብ በፅሑፍ ያቀረቡ ሲሆን “የትግራይ ክልል አመራር ከፌደራል መንግስት አመራር ጋር በክብ ጠረጴዛ በሰከነ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ስለአጠቃላይ አገራዊ መግባባት ፣ አለምአቀፍና አገር ወለድ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት በአስቸኳይ ግንኙነት እንዲያደርጉ ያሳስባል” ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት አገራችን ሰላም ያስፈልጋታል፣ የአገራችን ህዝቦች ጦርነት አያስፈልጋቸውም፤ ሁሉም አቅማችን ወደ ልማት መሆን አለበት፤ ለዚሁም ሲባል የትኛውም አይነት ልዩነት ይኑረን፣ ልዩነታችንን በውይይት መፍታት አለብን ብለዋል ተቋማቱ፡፡
በውውይት መድረኩ ተገኝቶ በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ለቀረበው ሀሳብ ማብራርያ ያቀረበ የድርጅታችን ሊቀ መንበርና የትግራይ ብሄራዊ ክልልላዊ መንግስት ምክትል ርእስ መስተዳድር ጓደ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል “የውውይት መድረክ መፈጠር ካለበት፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የሚወክሉ ፌደራሊስት ሀይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ትግራይ መንግስት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም ብለዋል፡፡

Related stories   ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር ፌዴራል ፖሊስ ተግባሩን ያጠናክራል

ውይይቱ በመጨረሻ ሰአት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው ያለው ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማነኛውም የአገሪቱ ችግር ለመፍታት የሚቀሳቀስ አካል ካለ ችግሩ ወይም ውጥረቱ የተፈጠረው ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማፍረስ በአገሪቱ አምበገናናዊ ስርአት ለመገንባት እየተሯሯጠ በሚገኘው ብልፅግና የተሰኘው በድንና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እንጂ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ብቻ የተፈጠረ አለመግባባት አድርጎ መመልከት የለበትም ብለዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ስለ ጦርነት አላስፈላጊነት መስበካቸው፣ ስለ ሰላምና ውይይት መናገራቸው ልክ ነው፤ ያሉት ጓድ ደብረፅየን፣ ግን ይህንን መባል ያለበት ህግ መንግስታዊ ስርአቱን በማክበር ምርጫ አድርጋለሁ ባለው ክልላዊ መንግስት የጦር አዋጅ ለሚያውጅ የፌደራል መንግስት፣ ህግ መንግስታዊ ስርአቱን በግላጭ በመጣስ ያለ ምርጫ ስልጣን ላይ ለመኖር ለሚቋምጠው ቡድን፣ የመንግስት ሚድያዎች ተጠቅሞ በራሱ ህዝብ /የትግራይ ህዝብ/ የስም ማጥፋትና የጅምላ ጭፍጨፋ ነጋሪት ለሚመታ ቡድን፣ ከዚህም አለፍ ሲል የትግራይ መንግስትና ህዝብ በማግለል ከኢሰያስ አፈወርቂና ሌሎች የውጭ ጠላትች ቀማበር በራሱ ህዝብ ተንኮል ከሚሰራ የብልፅግና አመራር መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ይህን መሰል መድረክ ሲዘጋጅ መፍትሔ ለማምጣት ተፈልጎ ከሆነ ቢያን ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ፖለቲካዊ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሌሎች የሚመለከታቸው የህብረተ ሰብ ክፍሎች መሳተፍ ነበረባቸው። ከዚሁ በተጨማሪ ሚድያ እንዳይገባ የተፈለገበት ምክንያትም ልክ አይደለም ያለው ጎድ ደብረፅዮን ወደ ፊትም ቢሆን መደባበቁ ችግሩ ሊያባብሰው ካልሆነ በስተቀረ መፍትሄ አይሆንም ብለዋል።

Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

ለአገራችን ሰላም፣ አንድነትና መቻቻል ተጨንቀው አገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት መፍትሄ ለማጣት በማሰብ የውይይት መድረኩን ለጀመሩ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ትልቅ ክብር አለኝ፣ ያለው ጓድ ደብረፅዮን ከወደ ትግራይ የሚጀመር አንዳች ጦርነት አይኖርም ብለዋል፡፡ ትግራይ የጦርነት አስከፊነት፣ የሰላምና መቻቻል አስፈላጊነት ጠንቅቃ ታውቃለች ካለ በኅላ ቢሆንም ግን ትግራይ የጦርነት አስከፊነት ስለምታውቅ መብትዋን አሳልፋ ትሰጠላች ማለት ግን አይደለም ሲል ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ በመገኘት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ያነስዋቸው ሀሳቦችን በተመለከተ አስተያየታቸው ያቀረቡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት የትግራይ ህዝብ ወደ መሃል አገር የሚመላለስበት የደሴ መንገድ ሲዘጋ ለምን አላወገዘም፣ የትግራይ ህዝብ መብቱ ስለጠየቀ /ምርጫ አካሄዳለሁ ስላለ /ጦርነት ሲታወጅበት ለምን ዝም አለ? የትግራይ ህዝብ ይህንን ይገበዋል ወይ? በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች፣ ፌደራሊስት ሀያሎች እየደረሰ ያለው ሲቃይስ ይገባቸዋል ወይ? ይህንን ሲሆን ለምን ዝም ተባለ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ሲሆን የአገር ሽማግሌዎችስ የት ነበሩም ብለዋል፡፡

Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ

የትግራይ ህዝብ ላለፉት ሁለት አመታት በአገሩ እንደ ባእድ ተቆጥሮ በፌደራሉ መንግስት ስፍር ቁጥር የሌለው በደል ደርሶበታል ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች፣ ያም ሆኖ የትኛውም የትግራይ ህፃን ቢጠየቅ ዛሬ ድረስ ኢትዮጵያዊነቱን አጥበቆ ይወዳል፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ይላል ብሏል፡፡

በአሁኑ ሰአት ብልፅግና የተባለውን ቡድን የተከተለው ኢ ህገ መንግስታዊ አካሄድ ኢትዮጵያን ለብተና ሊዳርጋት ተቃርበዋል ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት ችግሩ በትግራይና ፌደራል መንግስት ያለ ችግር አድርገው ከመመልከት ወጥተው ያለ ምርጫ፣ ገደብ የለሽ ንግስና የተመኘው ብልፅግናና መብታቸው ለማስከበር ብትግል ላይ በሚገኙ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አድርጎ መመልከት ይበጃል ብሏል፡፡

ከድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮችና የመድረኩ ተሳታፊዎች የተሰጡት ማብራርያዎች ያደመጡ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት የተሰጡት ሃሳቦችና ማብራርያዎች ይዘው ወደ ፌደራሉ መንግስት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ
መቐለ፡ ሰኔ 09/2012 ዓ/ም

TPLF

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *