“Our true nationality is mankind.”H.G.

የሽምግልና ጉዳይ ” አክቲቪስት” የሚባሉትን ሃይሎች እያስቆጣ ነው፤ እስካሁን ስለሽምግልናው ብልጽግና የሚያውቀው ነገር የለም

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መንጋገርን፣ መደራደርን፣ ሽምግልናን የሚያወግዙ ” ኢትዮጵያዊያን” መኖራቸው ያስደነግጣል። የትኛዋን አገር ለመጥቀም እንደሚሰሩም ለመረዳት ያስቸግራል። በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም ቢወርድ ለምን እንደሚከፋቸው መገመትም ያዳግታል። ዛሬ ከየጥጉ የሚወረወረው ይህ አይነቱ አባዜ ወዴት እንደሚወስደን አለመረዳት የእውቀት ማነስ ሳይሆን ” የኪሴን ልሙላ” አባዜና በንዋይ እሳቤ የመቀንዘር ለባዊ ሴሰኛነት ነው።

ፎቶ – የተፈናቀሉ ወገኖች ናቸው። አሁን የሚፈለገውም ከሰላም ይልቅ ህዝብ እንዲያልቅና እንዲፈናቀል በመሆኑ የርቅ ሃሳብ የተወገዘ ነው
ስለ ሽምግልና የተሰማውን ዜና ተከትሎ ” አክቲቪስት” ነን ባዮች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። በህወሃትና በገዢው ፓርቲ መካከል እየተካረረ የመጣው አለመግባባት ሰላም እንደነሳቸው ያስታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት መሪዎች በጥምረት ወደ ትግራይ ማምራታቸውን ተከትሎ ነው ቁጣው የተሰማው።
በህይወትና በነብስ መካከል እንደነበር በገለጸ ማግስት ህዝብ ድጋፍ ያደረገለትና ወደ አሜሪካ እንዲያቀና ልዩ እገዛ የተደረገለት ሃብታሙ አያሌው በፊስ ቡክ ገጹ በይፋ ዶክተር አብይ እርቅ እንደጠየቀ በማስመሰል ቁጣውን ለመግለጽ ቅድሚያውን ወስዷል። ይሁን እንጂ አቶ ታዬ ዳንደአ በይፋ እንዳስታወቁት አሁን ተጀመረ ስለተባለው ሽምግልና ብልጽግና እስካሁን የሚያውቀው ነገርም ሆነ የደረሰው አንዳችም ጥያቄ የለም። ከሆነም ልዩ ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ ነው።
በአማራ ክልል ከፋኖ ዋና አመራሮች ጋር የተደረሰው ስምምነትና አብሮ ለመስራት በሚያስችል ደረጃ መግባባት መፈጠሩ እጅግ ያበሳቻቸው ወገኖች በተመሳሳይ የክልሉን አመራርና የፋኖን ታጋዮች ሲያጣጥሉ መቆየታቸው ይታወሳል። ቀደም ሲል እጅግ ያከር የነበረው አብንም እጅግ የረጋ የተባለ አካሄድ መጀመሩና በክልል ደረጃም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ መከተል የጀመረው የትብብር መንፈስ በተመሳሳይ ለስድብ እንደዳረገው የሚታወስ ነው።
የሐይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መሥተዳድርን ለማስታረቅ ጥረት መጀመራቸውን ይፋ ያደረጉት  የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሐጂ መስዑድ አደም ናቸው። እሳቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁሌታ የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎችን ጣልቃ ገብነት የሚያስፈልገው ሆኗል።
ይህ ከመሰማቱ በፊት ዶክተር አብይ ስለተፈጠረው ችግር ተጠይቀው ” ሲፈልጉ በሚስጢር፣ ሲያሻቸው ህዝብ በአደባባይ እየሰማ መነጋገር እንችላለን” ማለታቸውን የዘነጉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ” መነጋገር እያለ ጠብመንጃ በዚህ ዘመን ማንሳት ነውር ነው” እያሉ ለሰላም ጥሪ ሲያደርጉ ያደመጡ የአቶ ሃብታሙና ባልደረቦቻቸው ፍላጎት ሊገባቸው አልቻለም።
“መጥኔ ለኢዜማ” በሚል ርዕስ አዜማን ከሽምግልናው ሃሳብ ጋር እንዴት እንዳገናኘው ማብራሪያ ሳያቀርብ ሽሙጥ የለተፈው ሃብታሙ አያሌው “ቢጫዋ ሄሌኮፕተር ልትላክ ነው ብለው ዘመቻ ሲከፍቱ የነበሩት የብልፅግና እና የኢዜማ የአንደኛው ቡድን አባላት
ቢጫዋን ሄሊኮፕተር ሲጠብቁ መንግስት *ቢጫ የለበሰ* መነኩሴ ልኮ ህወሓትን እንታረቅ ሲል ‘ይሄማ የአቶ ልደቱ አያሌው ሸር ነው” በማለት ድሮ የአንድነትና የቅንጅትን ኮት በለበሰበት ዘመን ሲወነጅለው የነበረውን ልደቱ አያሌውን ” ሲልሰው” አሳይቷል።
ከዚህ ሽምግልና ጋር አዜማ ምን እንደሚያገናኘው ባይታወቅም ሃብታሙ አያሌውና ሌሎች አክቲቪስት ነን የሚሉ ” እንዴት እርቅ ይታሰባል” ሲሉ ሙግታቸውን የጀመሩት ገና ሽምግልናው ሳይጀመር፣ ብልጽግና ስለ ሽምግልና የቀረበለት አንዳችም ሃሳብ እንደሌለ በገለጸበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን አስገራሚ አድርጎታል።
አቶ ታዬ በማህበራዊ ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተደጋጋሚ እንዳስታወቁት፣ አሁን በቅርቡ ባሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት ከማናቸውን የተፎካካሪ ሃይሎች ጋር አብሮ ለመስራትና ለመነጋገር መንግስት በሩ ክፍት መሆኑ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ መሆኑንን መናገራቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ሳለ ” አንድ መሪ ለድርድር በሩ ክፍት መሆኑ እንዴት ያስወቀሳል” ሲሉ በርካቶች እየጠየቁና እየተገረሙ ነው።
መንግስትን ለመስደብና ለማሽሟጠጥ እጅግ ሰፊ ጊዜ የሚወስዱ ወገኖች አሁን አገሪቱን ሊበላት ስለተዘጋጀው ኮሮና ትኩረት የማይሰጡት ከዩቲዩብ የሚያገኙት ገቢ እንዳይቀንስባቸው ነው ሲሉም የሚወቅሷቸው አሉ። አገር ሰማን ከሆነ ስራ ስለሚጠፋ ጸብ መዝራቱ ኪስን ከማደለብ አንጻር እጅግ ሰፊ ዋጋ እንዳለውም እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአገር ሽማግሌዎች ጥምረት  የፌድራል መንግሥት እና በትግራይ መካከል የተካረረውን ልዩነት ለማስታረቅ ወደ መቐለ ያመሩት የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ፈቃዳቸውን በማሳየታቸው እንደሆነ ለጀርመን ራዲዮ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ከመንግስት ወገን ምን ዓይነት ምላሽ እንደተሰጣቸው ያሉት ነገር የለም።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የኢትዮጵያ የየሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሐጂ መስዑድ አደም የኢትዮጵያ ነባራዊ ፖለቲካ የሐይማኖት መሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎችን “ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ሲያስታወቁ ፣ ለሽምግልናው ይሁንታ የሰጡት የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች በሚያደርጉት ጥረት የተሳካ ውጤት እንደሚያመጡ እመነታቸውንም ገልጸዋል።

አቶ ታዬ በፊስቡካቸው የጻፉት

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ
የሀገራቸዉ ጉዳይ የሚያሳስባቸዉ አባቶች ችግሮችን በእርቅ ለመፍታት ማሰባቸዉ ያስመሰግናል። ደግሞ እርቀሰላም የብልፅግና አንዱ መርህ መሆኑም ይታወቃል። ከወያኔ ጋር የሚደረግ ሽምግልና ግን በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል። ወያኔ በአፉ እርቅ እያለ በእጁ ተንኮል ይሸርባል። በ2000 ዓም ዋዜማ ከቅንጅት ጋር የነበረዉ ታሪኩ ይህን ይመሠክራል። ስለዚህ ቅድመ ሁኔታ ያስፈልጋል። ወያኔ እርቅ ከፈለገ የደበቃቸዉን ዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ለፌዴራሉ መንግስት ያሰረክባል። በምርጫ ስም የኢትዮጵያን ህገ-መንግስት ለመናድ የሚያደርገዉን መፍጨርጨር ያቆማል። ላለፉት 27 ዓመታት ዘርፎ ውጭ ሀገር ያከማቸዉን የሀገር ሀብት ቆጥሮ ይመልሳል። ይህ ከመሆኑ በፊት ስለሽምግልና ማዉራት ግን የኢትዮጵያዊያንን ቁስል ማመርቀዝ ይሆናል። ብልፅግና እስከ አሁን ጉዳዩን እንደማያዉቅ በአክብሮት ይገልፃል!
እኛ ብልፅግናዎች ነን! በመደመር መንገድ ለኢትዮጵያ ብልፅግና እንጓዛለን!

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0