“Our true nationality is mankind.”H.G.

እንግሊዝ የኮሮና ተጠቂዎችን ሞት የሚቀንስ መድሃኒት ሰራሁ አለች!

እንግሊዝ የኮሮና ተጠቂዎችን ከሞት የሚታደግ መድሃኒት ማግኘቷን አስታወቀች፡፡ የሃገሪቱ የጤናዉ ዘርፍ ተመራማሪዎች እንዳሉት፣ህክምናዉ ብዙ ወጭን የማይጠይቅ በመሆኑ ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡
መድሃኒቱ የሰዎችን የበሽታ መከላከል አቅም በማሳደግ ቫይረሱን በቀላሉ እንዲቋቋሙ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በ2 ሺህ ታማሚዎች ላይ በተደረገ ጥናት የሟቾችን ቁጥር እስከ 40 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል። ይህ መድሃኒትን ሰዎች በህክምና እንደሚታዘዝላቸው የመድሃኒት መጠን መሰረት ከ4 እስከ 35 ፓውንድ ወጪ ሊያወጡ ይችላሉም ተብሏል።
መድሃኒቱ ቀደም ብሎ መገኘት ቢችል በሃገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ከሞቱ ሰዎች ዉስጥ ቢያንስ 5 ሽህ ያህሉን ማትረፍ ይቻል እንደነበር ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
የመድሃኒቱ ወጭ ዝቅተኛ በመሆኑም በተለይም ለድሃ ሀገራትም ጭምር በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ይቻላል ነዉ የተባለዉ፡፡
ዴክሳ ሜታሶን የተሰኘዉ ይህ መድሃኒት የተገኘዉ በአለማቀፋ የመድሃኒት ጥናት አማካኝነት ሲሆን ለፈዋሽነቱ ማረጋገጫ እንደተሰጠዉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ
0Shares
0