“Our true nationality is mankind.”H.G.

ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ ከወጣች ኢትዮጵያ ዳግም ወደ ድርድር እንደማትመለስ አስጠነቀቀች

“ግብፅ በድርድሩ በተለመደው ሁለት አካሄዷ ቀጥላበታለች። አንድ እግሯን ድርድሩ ላይ፣ አንድ እግሯን ደግሞ የፀጥታው ምክር ቤት አስቀምጣ መደራደርን መርጣለች። በድርድሩ የፈለጉት እና የጠየቁት ሁሉ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፣ የሚሰጡት ግን የላቸውም”
ካሁን በሁዋላ ግብጽ የተጀመረውን ድርድር አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ኢትዮጵያ ዳግም ለድርድር እንደማትቀመጥ በይፋ አስታወቅች። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ሰሞኑን እየተካሄደ ያለውን የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
አቶ ገዱ  በመግለጫቸው እንዳመላከቱት ግብጽ ከዚህ ቀደም የያዘችውን አቋም ሳትቀይር በድርድሩ ስታሳየው የነበረውን ሙሉ የዓባይ ውኃ ይገባኛል አካሄድ አሁንም እየተከተለች ነው፡፡
“በ19ኛውና በ20ኛው ክፍለ ዘመናት የተከተሉት ይህ አካሄድ ለአሁኑ የ21ኛው ክፍለ ዘመን እሳቤ በምንም መልኩ የማያስኬድና የማንቀበለው ነው ” በማለት አቶ ገዱ የኢትዮጵያ ትዕግስት መሟጠጡንና በግድቡ ለመጠቀም የተያዘውን እቅድ በፍትሃዊ መልኩ ማስቀጠል ለአፍታም ቢሆን የሚተው ጉዳይ እንዳልሆነ አስረግተው ተናግረዋል።
“ግብጽ አሁንም ፍላጎቷ ድርድሩ እንዲቋረጥ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት በ2015 (እ.አ.አ) ከነበረው የመርህ ስምምነት ውጭ ሌላ መተሳሰሪያ የሌለን በመሆኑ ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ከዚህ በኋላ ለድርድር የምንቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡
“እየተደራደርን ያለነው ሁሌም እኔ ብቻ ልጠቀም ከምትለው፣ እድሜ ልኳን የኢትዮጵያን ጥቅም ከምትጻረረው፣ ሀገራችን ዘላቂ ጥንካሬ እንዳይኖራት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከምትሠራው ግብጽ ጋር ነው” አጠንክረው  የግብጽን አቋም አሳይተዋል። የግብጽ ሕዝብ መንግሥታቸው ምክንያታዊና ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ተመስርቶ እንዲደራደር ጫና እንዲያሳድሩም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?
0Shares
0