“Our true nationality is mankind.”H.G.

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ

በአዲስ አበባ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ። ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በውደቀ ቤት ውስጥ ተገኝተው የሚያሳየው ምስል እጅግ ልብ የሚነካና እንደዚህ አይነት ዜጎች ባሉባት አገር ይህ ሁሉ የፖለቲካ ውዝግብ መታየቱ አሳፋሪ መሆኑንን አመልካች ነው።
ቤታቸው በላያቸው ላይ ወድቆ መሬት ፍራሽ ላይ ተቀምተው የሚታዩት ዛውንት እናት ልብ ያሳምማሉ። እሳቸውን የሚመስሉ ሚሊዮኖች እናቶች ያሉባት ኢትዮጵያ ናት ከ22 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተዘረፈችው። ባለስልጣኖቿ የሚያልቧት ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ዜጎችን ይዛ ነው። አዲስ አበባን በአደራ የመሯት ከንቲባ ብርሃነ ደሬሳ ይህንን አይተው ነበር ” ከኢትዮጵያዊያን ላይ መስረቅ ከአጥንት ላይ ስጋ የመጋጥ ያህል ነው። ያማል። እዚህ ስፍራ ስመጣ የተረዳሁት ይህንን ነው” ያሉት። ፋና የሚከተለውን ብሏል
በአዲስ አበባ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር ከዚህ አንጻር እጅግ ዋጋ አለው። ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል።
በየአካባቢው የሚገኙ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካማዎች መኖሪያ ቤታቸው የሚታደስ ሲሆን÷በመኖሪያ ቤት እድሳቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችና የተለያዩ አካላት የሚሳተፉ ይሆናል ነው የተባለው። ከቤት እድሳት መርሀ ግብር በተጨማሪም “አንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው” እርስ በእርስ የመደጋገፍ መርሀግብር በይፋ ይጀመራል።
በመርሀ ግብሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ በአቅራቢያው ላለ የኑሮ አቅሙ ደከም ላለ ቤተሰብ ድጋፍ የሚያደርግበትና ያለውን የሚያካፍልበት ነው ተብሏል።
“በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው” መርሀግብር የከተማዋ ነዋሪዎች፣በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ታዋቂ ግለሰቦች፣የከተማዋ ባለሀብቶችና የከተማዋ አመራሮች እንደሚሳተፉ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ
0Shares
0