ያለፈዉ ታሪካችንን በተመለከተ አለመግባባቶችና ንትርኮች በየጊዜዉ ይነሳሉ፡፡ በታሪካችን ላይ ያለዉ አለመግባባት የሚነሳዉ ከሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ይመስለኛል፡፡ አንደኛዉ ምክንያት የዘመናዊ ኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት በተመሰቃቀለ የታሪክ ሂደት እና ብዙ ጉዳቶችን በማስከተል ያለፈ መሆኑ ላለመግባባቱ አንድ መነሻ ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ጉዳይ በየጊዜዉ የሚነሱ የፖለቲካ የልሂቃን ዘመኑን የዋጀ የፖለቲካ ሃሳብ በማመንጨት ትዉልዱን ወደ ፊት ከማራመድ ይልቅ ያለፈዉ ታሪክ አንድ ጽንፍ ላይ ብቻ በመመርኮዝ ጽንፍ በያዘ አስተሳሰብ ታሪክን በማጠቀስ ብቻ ደጋፊን በቀላሉ ማሰባሰብ ላይ ያተኮረ የፖለቲካ ሞቢላይዜሽን አባዜ ነዉ፡፡ በአንደኛዉ ወገን ያሉት የፖለቲካ ሊህቃን ያለፈዉ ታሪካችን ምንም ግድፈት እንደሌለበት፣ ያለፉት ገዢ መደቦችን እና ነገስታትንም ቅዱሳን እና ሀገር አቅኚ አስመስለዉ የማቅረብ አካሄድን ይከተላሉ፡፡ ኢትዮጵያ የብዝሃነት ሀገር መሆኗን ይዘነጋሉ፡፡ ያለፉትን ገዢ መደቦች ይበልጥ ባወደሱ መጠን ደጋፊዎቻቸዉ ዘንድ የበለጠ ተቀባይነት እንደሚያስገኝላቸዉ ያምናሉ፡፡

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

በሁለተኛዉ ጎራ የሚሰለፉት ደግሞ ያለፉትን ገዢ መደቦች እና ነገስታትን ጥፋቶችን ብቻ አጉልተዉ በማሳየት ሰይጣን አድረገዉ የማቅረብ አካሄድን በመከተል ደጋፊዎቻዉ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ፡፡በዚህ ጎራ ያሉት የፖለቲካ ሊሂቃን ያለፉትን ገዢ መደቦች ይበልጥ በረገሙ ቁጥር የበለጠ ተቀባይነት እንደሚያስገኝላቸዉ ያምናሉ፡፡ ኢትዮጵያ የብሔሮችን ፣ ሐማኖቶችን እኩልነት ከመስተናገድ አኳያ ነበሩትን ክፍተቶች ወደ ሌላ ጽንፍ የሚወስዱ ናቸዉ፡፡ እነዚህ በሁለት ዋልታ ረገጥ ጎራ የሚቆሙ የፖለቲካ ሊህቃንና ሀሳቦቻቸዉ ተቃርኖ ያላቸዉ ቢመስልም አንድ የሚያደርጋቸዉ ነገሮቸም አሏቸዉ፡፡ የሁለቱም ወገኖች ወደ ፊት ከመመልከት ይልቅ ያለፈዉ ዘመን ዉስጥ የሚኖሩ ናቸዉ፡፡ ለአዲሱ ትዉልድ አዲስ ራዕይ አና ተስፋን የሚሰጡ ሳይሆኑ ያለፈዉን ታሪክ በማብሰልሰል፣ ቁስልን በማከክ ከትብብር ይልቅ እልህ እና ፉክክርን ፣ከፍቅር እና ይቅርታ ይልቅ ጥላቻ እና ቂም በቀልን የሚያበረታቱ ናቸዉ፡፡

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

በሁለቱም የፖለቲካ ሊህቃን ወገኖች የሚቀነቀነዉ ዋልታ ረገጥ ተረኮች የሀገራችንን የሀገረመንግስት ቅቡልነት (state legitimacy) ፈተና ላይትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በነዚህ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ምክንያት ሀገራችን ባለመግባባት እና በግጭት አዙሪት ዉስጥ እንድትኖር አስገድዷታል፡፡በየጊዜዉ የሚከሰቱ ግጭቶችም ግጭቶች በሀገራችን ህዝቦች መካከል የዘመናዊ የፖለቲካ ዕሴቶች ማለትም የወንድማማችነት፣ እኩልነት እና ነጻነት ዕሴቶች እንዳይዳብሩ አድርገዋል፡፡

ከዚህ አዙሪት ለመዉጣት መፍትሄዉ ያለፈዉን ታሪክ በመደመር መነጽር ማየት ብቻ ነዉ፡፡ ያለፈዉ ታሪካችን መልካም መልካም ያልሆኑም ጎኖች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ የዛሬዉ ትዉልድ ለፈዉን ታሪክን በአግባቡ ማወቅ፣ መልካም መልካሙን እንደ ትዉልድ ላለብን ተልዕኮ መነሳሻ ስንቅ፣ መጥፎ መጥፎዉ ደግሞ በኛ ትዉልድም ሆነ ቀጥሎ በሚመጣዉ ትዉልድ እንዳይደገም መማሪያ አድርጎ መዉሰድ ግድ ይላል፡፡ የሀገራችን ታሪክ እንደሌሎቹ ሀገራት ሁሉ በመልካምም በመጥፎም የሚገለጥ ገጾች እንዳሉት በአግባቡ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ያለፈዉ ታሪክ መልካሙም ሆነ መጥፎዉ ገጽ ባለፈዉ ትዉልድ የተሰራ ነዉ፡፡ እኛ የዛሬ ትዉልዶች ወደ ኋላ ተመልሰን ያለፈዉን መጥፎም ሆነ በጎ ተግባር መቀየር አንችልም፡፡ ያለን ዕድል ከታሪክ ተምረን በጎ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክረን ስህተቶችን ላለመድገም ተጠንቅቀን ወደፊት መራመድ እና የራሳችንን አዲስ ታሪክ መስራት ብቻ ነዉ፡፡ ወደኋላ ተመልሰን ያለፈዉ ታሪክ ዉስጥ እንኑር ካልን በተለይ ከሀገራችን ምስቅልቅል የምስረታ ታሪክ እና የፖለቲካ ሊህቃን ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ጋር ጋር ተያይዞ ያለፈዉ ታሪክ ሊያወዛግበን፣ሊያካርረን ብሎም እርስ በርስ ማጋጨት ከግጭት አዙሪት ዉስጥ ለዘመናት ሊያኖረን ይችላል ይችላል፡፡

Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

ባለፈዉ ታሪክ ዉስጥ ከመኖር አባዜ እንዉጣ! ወደ ፊት እንመልከት! ካለፈዉ ይልቅ የሚመጣዉ ጊዜ ይበልጣል፡፡ አባቶቻችን ከሰሩት ታሪክ በላይ እኛም በዘመናችን የራሳችን ታሪክ የመስራት ዕድል አለን!

ቸር እንሰንብት!
Addisu Arega Kitessa

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *