የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሩሲያ እና የኢትዮጵያን የንግድ ግንኙነቶችን አልገታም- አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ

በሩስያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የኢትዮጵያን እና የሩሲያን የንግድ ግንኙነቶች አለማስቆሙን ገለጹ።

አምባሳደሩ ከሩስያ የዜና አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ወረርሽኙ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር አለማስቆሙን ጠቁመዋል ።

በዚህም ሁለቱም ወገኖች የጠበቀ ትብብራቸውን ጠብቀው እየተጓዙ በመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት ።

Related stories   ከዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ በወቅታዊ ጉዳዮች እና በምርጫ 2013 ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውንአምባሳደሩ አስታውሰው÷ በዚህ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሩሲያ እና የኢትዮጵያ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ትብብርና የንግድ ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል።

አምባሳደሩ በማሳያነትም “የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላኖች በሳምንት ሁለት ጊዜ“ ከሩሲያ ወደ አፍሪካ ፣ ከአፍሪካ ወደ ሩሲያ በማመላለስ በመስራት ላይ መሆኑን ” አንስተዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ በባህላዊ መስክ ያለው ትብብር ጠንካራ ግንኑነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ጠቁመዋል።

Related stories   የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ

በዚህም ታላቁ የሩሲያ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን በኢትዮጵያም ውስጥ እጅግ ተወዳጅ መሆኑን ጠቁመዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ኤምባሲያቸው ከሁለቱም አገራት የተውጣጡ 6 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት የቪድዮ የንግድ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ አያይዘውም በየዓመቱ ሰኔ 6 ቀን የሩሲያ ቋንቋ ቀን በኢትዮጵያም እንደሚከበር ገልጸው÷ ቀኑን “ከሩሲያ ጓደኞቻችን ፣ ተማሪዎች ፣ ፕሮፌሰሮች ፣ የአፍሪካ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በጋራ እናከብራለን ብለዋል፡፡

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

በዚህ ዓመት በወረርሽኙ ምክንያት በአካል መገናኘት ከባድ ቢሆንም ቀኑን በቪድዮ ኮንፈንስ መከበሩን ጠቅሰዋል

ምንጭ፡-የሩስያ ዜና አገልግሎት

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *