አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 853 የላብራቶሪ ምርመራ 195 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 954 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ የእድሜ ክልላቸውም ከ1 እስከ 85 ዓመት የሆኑ 90 ወንዶች እና 105 ሴቶች ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 144 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 12 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 12 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 7 ሰዎች ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 65 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትላንትናው 85 ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 መድረሱንም አስታውቅዋል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ202 ሺህ 214 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 954 ደርሷል።

አሁን ላይ 2 ሺህ 953 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 27 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 934 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ65 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *