ሰሞኑን ከትግራይ ክልል ሃላፊዎች የሚደመጡት ዜናዎች በይዘታቸው የተለዩ ሆነዋል። የባይቶና ሊቀመንበር ዛሬ ማለዳ ለሸገር መግለጫ ሲሰጡ ” የትግራይን የውስጥ ጉዳይ በአማርኛ ለሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች አንነግርም ” ሲሉ በቁጣ ተናገሩ። ጠያቂው እንዲያብራሩ ሲጋብዛቸው ” የትግራይን የውስጥ ጉዳይ ነው” መለሱ።

ትግራይን በአጭር ጊዜ ወደ ብልጽግና፣ በዓለም ደረጃ ታዋቂ አድርጎ የሚያስተዋውቅ፣ ለትግራይ ብቻ የተቀኘ ፕሮግራም እንዳላቸው ያስታወቁት የባይቶና መሪ ” ለምን ኢትዮጵያን ያገላሉ?” ተብለው ሲጠየቁ ተቆጡ። አከሉና ምርጫ የማድረግ ስልጣን የፌደራል ምርጫ ቦርድ ነው በሚል ጠያቂው ሲያነሳ ” እንደ ጋዜተኛ ሁን፤ አቋም ይዘህ …” መናደዳቸውን በሚያሳብቅ መልኩ አስተያየት ሰጡ።

Related stories   “በአጣዬ እና አካባቢው በተፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ” ኮማንድ ፖስቱ

” የፊደሬሽን ምክር ቤት ፈርሷል። አምባገነን ስርዓት ነግሷል። እንኳን በኮረና በሌላም ነገር ውስጥ ሆኖ ምርጫ ማድረግ ይቻላል” ሲሉ የተደመጡት የባይቶና መሪ ” ራሳችንን ከመከላከል ጀምሮ እስከተፈለገው እርቀት በመሄድ እርምጃ የመውሰድ አቅም አለን” ሲሉ ተደምጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ በንዲህ ደረጃ መንግስትን በሃይል እስከማስወገድ የደረሰ አቅም አለኝ ሲሉ የባይቶናው መሪ ምናልባትም የመጀመሪያ ሳይሆኑ አልቀሩም።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

የትግራይን ክልል አገር የማድረጉ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ግልጽ በሚያደርግ መልኩ ” ጉዳያችንን በአማርኛ አንናገርም” ያሉት የባይቶና ሊቀመንበር ” በአንድ ሰው ሳንባ የሚተነፍስ” ሲሉ መንግስትን ሰድበዋል። ጠያቂው ባያነሳም የትግራይ ክልል ራስዋን እያስተዳደረች ባለችበት ሁኔታ የክልሉ ተቃዋሚዎች ስለምን ስለፌደራል መንግስት አተኩረው በህወሃት ደረጃ እንደሚናገሩ ለበርካቶች ግራ ነው።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *