Share and Enjoy !

Shares

ህወሃት ከኤርትራ ጋር ድንበር ተከፍቶ ይፋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መጀመር አለበት ባይ ነው

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት በአገራችን ውስጥ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት መሰረት በማድረግ በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መደረክ ጋር መነጋገራቸውን ተከትሎ በአሉታዊና በበጎ ጎኑ በርካታ አስተያየቶች ተደምጠዋል። የጉዳዩ ባለቤቶች ግን ተስፋ ሰጪ አስተያየት እየሰጡ ነው።

የትግራይ ክልል አስተዳደር የሽማግሌዎችን ወደ መቀሌ ማቅናትና መወያየት ጠቅሶ በሰጠው መግለጫ ” ንግግሩና ሽምግልናው አገር አቀፍ ይሁን” ሲል በግል ከህወሃት ጋር የሚደረግ ውይይት አግባብ እንዳልሆነ አመልክቶ ነበር። ሽምግልናውን አስመልክቶ ከመንግስት ወገን  በጉዳዩ ላይ በገሃድ አቋምን የሚያሳይ ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም የሽማግሌዎች መማክርት ተስፋ ሰጪ ጉዳይ መኖሩን ዛሬ ገልጸዋል።

ከሁሉም ወገን በግልጽ የሽምግልናውን ጉዳይ ሲያነሱ አይግለጹት እንጂ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የምታደርገው ስምምነትን አስመልክቶ ህወሃት ደህንነት ስለማይሰማው፣ እንዲሁም የተከፈቱ ድንበሮች ዳግም መዘጋታቸውን ስለሚቃወምና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ባስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ያላቸው ፍላጎት መጓተቱ የቅሬታው ዋና ምሰሶ ነው።

Prime Minister Abiy Ahmed's miscalculations that helped TPLF, the ...

” መርሃ አልባ ” የሚሉት የሁለቱ መሪዎች ግንኙነት ህወሃት ላሰበችው የወደፊት እቅድ እንቅፋት በመሆኑ፣ ፐሬዚዳንት ኢሳያስን የማስወገዱ ዘመቻና ሙከራ በተደጋጋሚ መክሸፉ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ህወሃትን አምኖ በሩን መክፈት በኤርትራ በኩል ኪሳራ ስለሚያስነሳ ህወሃት እንደሚፈልገው ማድረግ እንደማይቻል በኤርትራ ወገን መረጃ አለን የሚሉ በተደጋጋሚ የሚገልጹት ጉዳይ ነው።

Related stories   ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

በዚህ ዋና ማጠንጠኛና በሃይል አሰላለፍ፣ እንዲሁም በወቅቱ ፖለቲካ አሰላለፍ የብልጽግና ፓርቲ መመስረት ያልተዋጠለት ህወሃት ቀደም ሲል የማያስበውን ወይም ” በመቃብሬ ካልሆነ ” የሚለውን የሽግግር መንግስት ጥያቄ እንዲያነሳ አድርጎታል። በዚህም የማመቻቻ ጊዜ ተቀምጦ አሁን ያለው መንግስት እንደ አንድ ወኪል ሆኖ በሽግግር መንግስት ውስጥ የሚሳተፍ እንዲሆን ህወሃት ታላቅ ፍላጎቱን እያሳየ ነው። በዚህም መልኩ ከኦሮሞ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ ላይ ናቸው።

ሽምግልና የሄዱት አካላት ህወሃት በርካታ ጥያቄ አቅርቦ፣ ነገር ግን ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑንን  ቢያሳውቁም መነሻዎቹ ጉዳዮች ከላይ ያሉት እንደሆኑ ወይም የብልጽግናን ፓርቲ አቅም ማሳጣት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው። በተለያዩ መልኩ ሃሳብ የሚሰጡ ወገኖችም በድጋፍ ይህንኑ ሃሳብ በየፊናቸው ሲያሰራጩ ነው የሰነበቱት።

 

ፋና ከታች ያለውን ዘግቧል።

Related stories   ስዩምና አባይ ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ፣ ደብረጽዮን እጅ እንዲሰጥ ተከቦ 24 ሰዓት ተሰጥቶታል

ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምእራፍ ለማሸጋገር የአካባቢያችንን ችግር በአካባቢያችን ሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በኩል ለመፍታት የጋራ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር ሽማግሌዎች መማክርት አስታወቀ። የህወሃት አመራሮች በርካታ ጥያቄዎች እንዳላቸውና ያንንም ለመማክርቱ ያቀረቡ ሲሆን፥ በጋራ ተግናኝቶ ለመነጋገር ግን ዝግጁ መሆናቸውን ነግረውናል

የመማክርቱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከሌሎች የመማክርቱ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ዛሬ በሰጡት መግለጫ መማክርቱ ከዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን የሚታዩ ችግሮችን በባህልና ወጋችን መሰረት ለመፍታት የጋራ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውሰዋል።

ይህን ወደ መሬት ለማውረድም ከአምስት ወራት በፊት የየክልሉ ታላላቅ የሀገር ሽማግሌ ተወካዮችን ማካተት የተቻለ ሲሆን፥ ይህንን መሰረት አድርጎ ስራዎችን መስራት ጀምሮ ነበር ነው ያሉት።

ነገር ግን ብዙም መራመድ ሳይቻል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከሰቱ በሚፈለገው ፍጥነት መጓዝ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

ሆኖም ወረርሽኙ ከሰላምና አንድነታችን በላይ ስለማይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ወደ ስራችን ገንበተናል ብለዋል።

መማክርቱ በመጀመሪያው ዙር በህወሃትና ብልጽግና ፓርቲ መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለመመልከት ባቀደው መሰረት ማክሰኞ ወደ ትግራይ ክልል እንዳመራና በዚያም ከህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ጋር እንደመከረ ተናግሯል።

በምክክሩም የሰላምና አንድነት ጉዳይ የውዴታ ግዴታ በመሆኑ ሁሉም በሀላፊነት ሊቆምለት የሚገባ ጉዳይ ነው በሚለው መግባባት ላይ ተደርሷል።

Related stories   ስብሃት ነጋ የትህነግን የውጪ አገር ሃብትና ንብረት "ለትግራይ ሕዝብ ጥቅም ሲባል" ይፋ እያደረጉ ነው

ከዚህ ውጭ ግን የህወሃት አመራሮች በርካታ ጥያቄዎች እንዳላቸውና ያንንም ለመማክርቱ ያቀረቡ ሲሆን፥ በጋራ ተግናኝቶ ለመነጋገር ግን ዝግጁ መሆናቸውን ነግረውናል ብሏል።

መማክርቱ በአዲስ አበባም ከብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር በህወሃት በኩል የተነሱ ጥያቄዎች ማቅረብን ጨምሮ በሰላምና አንድነት ጉዳይ እንዲሁም ተገናኝቶ መነጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ከስምምነት መድረስ ተችሏል ነው ያለው።

በዚህም መማክርቱ በሁለቱ አካላት መካከል ቀርቦ ያለመነጋገር እንጂ ቢነጋገሩ በልዩነት ውስጥ ተስማምቶ በጋራ መቀጠል የሚቻልበት እድል እንዳለ ለመገንዘብ ተችሏል ብሏል።

የመማክርቱ ምክትል ሰብሳቢ ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ እና ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ አሁን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምእራፍ ለማሸጋገር የውስጥ አንድነት ወሳኝ በመሆኑ እስከ መጨረሻው ድረስ ይህን በጎ አላማ እንደሚያስቀጥሉት ተናግረዋል።

መማክርቱ በቀጣይ ከሁለቱም አካላት የሚወያዩበትን ሀሳቦች ተመልክቶ በአንድ ላይ ለውይይት እንደሚጠራና ወደ መፍትሄ መምጣት እንደሚቻል ተስፋ እንዳለው አመላክቷል።

ምክክሩ በህወሃትና በብልጽግና ፓርቲዎች ብቻ የሚያበቃ አይደለም ያለው መማክርቱ በቀጣይ በኦሮሚያና ሌሎች አካባቢዎችም ባሉ ልዩነቶች ላይ ምክክር እንዲደረግ ከዚያም ወደ መግባባት እንዲመጣ እሰራለሁ ብሏል።

FBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *