“Our true nationality is mankind.”H.G.

ግብጽ ድርድሩን አቋረጣ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ዳግም አመራች፤ የአገሪቱ መገናኛዎች ስለ ህዳሴው ግድብ እንዳይዘግቡ አገዳ ጣለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ” ምንም የማትሰጥ፣ መቀበልን ብቻ የምትመኝ፣ በቀድሞ ዘመን ውል የተቸከለች፣ የድርድር መርህን የማትቀበል፣ በውሃው ላይ አንድም አስተዋጾ የሌላት፣ የቅኝ ግዢን ውል በ21ኛው ክፍለዘመን ሙጥኝ ያለች፣ ስግብግብ” ሲሉ የገለጿት ግብፅ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በማቋረጥ በድጋሚ ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ማምራቷ ተሰማ።
ኢትዮጵያ ግብጽ ይህንን ድርድር ተጋባራዊ የማታደርገና ጥላ የምትወጣ ከሆነ ደግም ወደ ድርድር እንደማትመለስ ቀደም ሲል አስታወቃ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ ግብጽ ድርድሩን በማቋረጥ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ማምራቷን ይፋ ያደርጉት የውሃ ሚንስትሯ ሳሜህ ሽኩሪ ለጋዜጠኖች በሰጡት መግለጫ ነው። በመግለጫቸው የሶስትዮሹ ድርድር ውጤት አላመጣም ብለዋል።
ስምመንቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት አቶ ገዱ ” ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን የሚይስገድዳት አንዳች ውል የለም” ሲሉ አስታውቀው ግብጽ ካላት የግብገብነት አባዜ መረን መውጣቱን ለማሳየት ” በኢትዮጵያ ድህነት የመዝናናት ስሜት አላት” ሲሉ የግብጽ ባለስልጣናትን አመለካከት መጠየፋቸውን አስረድተዋል። ቃል በቃል ይህንን ባይሉም ስሜታቸው ግን ይህንን የሚያስረዳ ነበር።
ኢትዮጵያ በተናጥል ውሀ መያዝ እንዳትች የፀጥታው ምክር ቤት እንዲያስቆምላት ግብጽ እንደጠየቀች  የውሃ ሚኒስትሯ እንደ አዲስ ዛሬ ይፋ ቢያደርጉም፣ ከአንድ ወር በፊት በፊት ተመሳሳይ ደብዳቤ ለጽጥታው ምክር ቤት አስገብታ ነበር። በመልሱ ኢትዮጵያም “በራሴ ተፈጥሯዊ ወንዝ የማንንም ፈቃድ አልጠይቅም ውሀውን መጠቀሜንም እቀጥላለሁ” የሚል ፈርጣማ ምላሽ ሰጥታ ነበር።
በዚህም መነሻ ነበር  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽ ችግር የምትለውን በሶስትዮሽ ድርድር እንድትፈታ ጫና ያሳደሩት። ይህንንም  ተከትሎ ወደ ግብጽ ወደ ድርድሩ ብትመለስም ጉንጭ አልፋ ከመሆን እንዳላለፈ ገዱ አንዳርጋቸው በከረረ መልኩ ነበር የገለጹት።
ይሁንና የተጀመረው የሶስቱ አገራት የውሀ ሚንስትሮች ውይይት ሳይጠናቀቅ ግብጽ በድጋሚ ድርድሩን ማቋረጧን ማስታወቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል እንዳስታወቀችው ካሁን በሁዋላ ድርድር የማትቀመጥ ቀጣዩ የግብጽ አቋም ምን እንደሚሆን ይፋ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አመራሮች በይፋ እንዳስታወቁት ግብጽ ወደ ሃይ ርምጃ የምታመራ ከሆነ ኢትዮጵያ ራስዋን የመከላከል ማናቸውንም ምላሽ የመስጠት አቅም እንዳላት ይፋ አድርገዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብጽ በአገሪቱ ባሉ ሚዲያዎች ስለ ኮሮና ቫይረስና ስለ ናይል ግድብ ምንም ዘገባ እንዳያቀርቡ ማገዷ ተሰምቷል። ግብጽ የባይን ጉዳይ በከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ የሚያጫውቱላትን ሚዲያዎች  ከዚህ ስራቸው ማገዷ ባለስልጣናት ብቻ የሚያወጡትን መረጃዎች እንዲያትሙና እንዲያሰራጩ በሚል ነው።
የግብጽ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የሃገሪቱ የሚዲያ አውታሮች ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ ስለ ኮሮና ቫይረስ፣ በሊቢያ እና በሲና በረሃ ከታጣቂዎች ጋር ስላለው ግጭት እንዳይዘግቡ እገዳ ጣለ።
ምክር ቤቱ የሚዲያ አውታሮች በሃገሪቱ ባለስልጣናት የሚወጡ መግለጫዎችን ብቻ እንዲጠቀሙም አስጠንቅቋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የሚዲያ አውታሮቹ ስለ ህዳሴው ግድብም ሆነ ክልከላ በተጣለባቸው ጉዳዮች ላይ ማወያየትም ሆነ ዘገባ መስራት አይችሉም ነው የተባለው።
ይህን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይም እርምጃ ይወሰዳል ነው ያለው ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ።
በተጨማሪም የህትመት ሚዲያዎች ክልከላ በተጣለባቸው ጉዳዮች ላይ መስራት የፈለጉትን ዘገባ ከማሳተማቸው በፊት ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማስገምገም እና ፈቃድ ማግኘት አለባቸውም ነው ያለው።
የወጣውን ክልከላ ተከትሎም በርካታ የሃገሬው ዜጎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን በተለይም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ድርጊቱን መረጃን ከዜጎች ለመደበቅ ያለመና ነጻነትን የሚጋፋና በሚል ተችተውታል።
ምክር ቤቱ አሁን ላይ ሃገሪቱ ደህንነቷን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ ጠንካራና የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅበት አደገኛና ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ መሆኗን በመግለጫው አመላከቷል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤
0Shares
0