“Our true nationality is mankind.”H.G.

ስለ አሃዳዊነት ስብከትና ፕሮፓጋንዳ ማንን እንመን? የሃዋሳን ሕዝብ ወይስ አጨብጫቢዎችን ?

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስረኛ የፌዴራል ክልል ሆኖ ለሚደራጀው የሲዳማ ዞን የስልጣን ርክክብ ማድረጉን ተከትሎ አብዛኞች የውጤቱ ባለቤት መስለው የደስታ መግለጫ እያጎረፉ ነው። ህወሃትና አቶ ጃዋር ደግሞ ቀዳሚ ናቸው። ሁሉንም የደስታ መግለጫዎች ተከትሎ ግን ከሃዋሳ የተሰማው ዜና ለየት ያለ ነው። በተለይም ስለ አሃዳዊነት!!

“በሲዳማ ክልል መሆን አሃዳዊያን እየተንጫጩ ነው” ሲል ጃዋር በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። ቅድሚያ ወስዶ በሚዲያ ” የሲዳማ ክልል መሆን እንደምታው ምንድን ነው?” ተንትኗል። የትግራይ ክልል አክቲቪስቶችም ላለፉት 28 ዓመታት ሰለ ሃዋሳ ሳይተነፍሱ ኖረው፣ ክልሉ በውክልና ሲተዳደር በላየ አልፈው ዛሬ አበባ በታኝ ሆነዋል።

የሃዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ግን ሁሉንም በአንድ አጣፍተዋል። ” ብልጽግናን እናመሰግናለን” በማለት። አያይዘውም ላለፉት ሃያ ስምንት ዓመታት ጥያቄው ሲነሳ ማሰር፣ ማንገላታት፣ ማሳደድና መግረፍ የወቅቱ መሪዎች ምላሽ እንደነበር ያወሱት ከንቲባው ” የሕዝብ ጥያቄ መልስ ያገኘው አሁን ብልጽግና መሪ ድርጅት ሲሆን ነው” ሲሉ ድርጅቱን ለሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ምስጋና አቅርበዋል። አወድሰዋል። ብልጽግና የአሃዳዊነት እሳቤ አራማጅ ነው የሚባለውን ቅስቀሳ ተራና ማስረጃ ቢስ መሆኑንን በአጭሩ ” በተግባር አይተነዋል” ሲሉ ገልጸዋል። ይህንን ጉዳይም ለተራ የፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ተቀባይነት እንደሌለው አመልክተዋል።

Related stories   ይናገር ደሴ -"እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም"

በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤው ላይ የስልጣን ርክክብ መደረጉ የመጨረሻ ድል እንዳልሆነ ከንቲባው ሲያስታወቁ ” አሁን አስተማማኝ ሰላም መመስረት፣ ወደ ልማት መዞር፣ ስራ መፍጠር፣ በአብሮነት እሳቤ በፍቅር ከሌሎች ጋር መኖር…” ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል። ሃዋሳ በአብሮነት ስሜት እንደምትቀጥል ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናግረዋል።

ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርእስቱ ይርዳው ክልል የሚባል አደረጃጀት ከመምጣቱ በፊት ህዝቡ ለዘመናት አብሮ የኖረ በመሆኑ አሁን ተግባራዊ የሆነው አደረጃጀት ሊያሳስብበው አይገባም ብለዋል። የስልጣን ማስረከቢያ ደብዳቤውን የተቀበሉት የቀድሞው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሰለሞን ላሌ በበኩላቸው የሲዳማ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ እንኳን ደስ አለን ብለዋል። አሁን የተገኘው የመደራጀት መብት የብሄሩ ታጋዮች ባደረጉት ጥረትና ከሁለት ዓመታት ወዲህ የመጣው የለውጥ አመራር በፈጠረው ነፃነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

በቀጣይም የሲዳማ ህዝብ እስከ ዛሬ አብሮ ከኖራቸው ህዝቦች ጋር በመሆን ድህነትንና ኋላ ቀርነትን እንደሚታገል አቶ ሰለሞን በንግግራቸው ጠቅሰዋል። ዛሬ በተከናወነው የሲዳማ ዞን የስልጣን ርክክብ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ተቋማት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ።

ከክልሉ የሚወጡት ስሜቶች ቀና ሲሆኑ ሌሎችን ለመቀስቀሻና ክልል ካልሆንኩ ወደሚል ማተራመስ የሚመሩ በርካታና ተደጋጋሚ ቅስቀሳ የቀረበበት የሲዳማ የክልልነት ምላሽ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ” የሁሉም ጥያቄ በሂደት ይፈታል። እስከዛው ግን የወረዳም፣ የዞንም፣ የቀበሌም መዋቅሮች ይቀጥላሉ። ይህንን ማስተጓጎል ከንቱ ነው። አይጠቅምም ዋ!” ሲሉ በግልጽ አስጠንቅቀዋል። ክልሉ ሁሉን በህግና በሂደት ጥያቄያቸውን ሲያስተናግድና ሲጨርስ እንደሚከስምም አስታውቀዋል።

የደቡብ ክልል እንዲበታተንና እንዲወላልቅ ነዳጅ የሚያርከፈክፉ አካላት ፍላጎት ምንድን ነው? አንድ ወረዳና አነስተኛ ዞን ክልል የሁን፣ ራሱን ይምራ፣ በሚል ሌት ተቀን የሚቀሰቅሱት ምን ፈልገው ነው? ምን ልዩ ጥቅም ያገኛሉ? ለሚለው ባለሙያዎች የሚሉት ባጭሩ ” ሌሎችን በፍነካከት ሃያል የመሆን ህልም” ሲሉ ነው የሚገልጹት።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ኦሮሚያ በታሪክ አጋጣሚና አሁን ባለችበት ሁኔታ አገር መሆን እንደማትችል ጃዋርን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። በይፋም ይመስክራሉ። እውነታው ይህ ከሆነ ወደፊትስ ቢሆን ለራሳቸው የማይበጃቸውን አደረጃጀት እንዲሰፋ መጣራቸው ለምን ይሆን? ለሚለው እነዚሁ ክፍሎች ” የማዕከላዊ መንግስቱን ፋታ ማሳጣት፣ እረፍት መከልከልና በጫና ውስጥ ለመክተት የሚጠቅም መሳሪያ ስለሆነናቸው ” ሲሉ ነው ሃሳቡን የሚገልጹት።

አሃዳዊ አመለካከት እንዳለው በተደጋጋሚ የሚከሰሰው ብልጽግና ፓርቲ ከሚነገርበት ይልቅ በተግባር የፌደራሊዝምን አካሄድ እንደሚያምንበት በተግባር ማሳየቱ “ከጆሮና ከአይን የቱ ይቅደም? ማን ይታመን” የሚለውን ብሂል ከማስታወስ ያለፈ ትርጉም እንደማይሰጥ በሃዋሳ አስተያተ የሰጡ መስክረዋል። ክልሉም ቀደም ሲል ብልጽግናን እንደሚቀላቀል ማሳወቁና በሰላም ጉዳይ ላይ ጥብቅ አቋም እንደሚይዝ ይፋ ማድረጉ በሃዋሳ ዙሪያ ያሉ ምኞቶችን የሚገራ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል። ይህ ከሆነ ደግሞ በአዲሱ ክልል አመራሮች ላይ የሚዲያ ዘመቻው ይጀመራል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0