ኢትዮ 360 የሚሰኘው የዩቲዩብ ቻናል በውስጡ በየተነሱ የሃሳብ ልዩነቶች ሳቢያ በመሰንጠቅ ማግስት ላይ መሆኑን ተሰማ። ልዩነቱ ” ጥላቻን እየሰበክን መጓዙ አያዋጣም” በሚል የተነሳው የሃሳብ ልዩነት ተካሮ አደባባይ ሊወጣ መሆኑም ታውቋል።

ከኢትዮ 360 ባልደረቦች መካከል አንዱ የሆነው ለኢትዮ ጎልጉል እንዳስታወቀው ልዩነቱ ከለት እለት ተካሯል። ” አንድ ሰው ላይ የሚያጠነጥን ጥላቻ እየሰበክን መቀጠል አንችልም፤ ዘወትር ሁሉንም ጉዳይ በመቃወም የትም መድረስ አንችልም” የሚሉ ወገኖች ሚዲያው አሰራሩንና መልኩን እንዲቀይር በግልም በህብርትም ጠይቀዋል።

ለጊዜው ማን ምን አለ የሚለውን ጉዳይ ማንሳት ያልፈለገው የመረጃው ምንጭ ከቦርድና ከቴክኒክ ሰራተኞች በድምሩ ስድስት ሰዎች  360ን እንደተለዩ አስታውቋል።

ቀደም ሲል የቀድሞው የአቶ በረከት ስሞኦን ምክትል የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ የመሰንጠቁ አካሄድ ስለገባው ምንአላቸው ስማቸውን  በመያዝ ንግድ ላይ ያተኮረ መረብ ለመጀመር ሃሳብ ማቅረቡ ሌሎች ዘንድ መሰማቱ ጉዳዩን ይባስ እንዳጋለው ታውቋል። አሁን ላይ ልዩነቱ ሲባባስ አቶ ኤርሚያስ ከቀድሞው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ሃብታሙ አያሌው ጋር ሚዲያውን ለማስቀጠል እየተጋ መሆኑን ምንጩ ይፋ አድርጓል።

Related stories   “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”

360 በማንና ለምን እንደሚደጎምና አጠቃላይ የሃይል አሰላለፉ ምን እንደሚመስል የኸው ምንጭ በጽሁፍ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግና በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ አገር ሚዲያዎች ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የአሜሪካ የኢትዮ ጎልጉል ዝግጅት ተባባሪ  360ን ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት መጨረሻ ላይ አስታውቋል። እንደተሳካ እናካትታለን

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *