ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የ10 ዓመት ህጻን ልጁን የደፈረው ፖሊስ በ9 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ዞን ማረሚያ ቤት የሥራ ባልደረባ የሆነው ዋ/ሳጅን በላይ ታየ የገዛ ልጁን የ10 ዓመት ህጻን አስገድዶ የደፈራት መሆኑን የካማሽ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አቤቱታ መቀበል መመርመር ዋና ስራ ሂደት ባለቤት ዋና ኢንስፔክተር ቃበታ መልካ ገልፀዋል፡፡
ግለሰቡ ነዋሪነቱ ካማሽ ከተማ 02 ቀበሌ ዕለቱ ሰኞ ታህሳስ 08/04/2012 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ የህጻኗ እናት ቤተሰብ ሞቶባት ለሃዘን በሄደችበት ወቅት ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሰክሮ በመምጣት የ10 ዓመቷን ህጻን ልጁን ከደበደባት በኋላ አስገድዶ የደፈራት መሆኑ ተገልጿል።
ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የሰውና የህክምና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ለካማሽ ወረዳ ዐ/ህግ ያስተላለፈ ሲሆን ዐቃቢ ህጉም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ከተመለከተ በኃላ በወ/ል/መ/ቁ/ 122/12 ክስ በመመስረት ለካማሽ ወረዳ ፍ/ቤት አስተላልፏል፡፡
የካማሽ ወረዳ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ክስ ሲመረምር ከቆየ በኃላ ግለሰቡ የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት መከላከል ባለመቻሉ የዐቃቢ ህግን ማስረጃ በመንተራስ ፍ/ቤቱ በ17/10/2012 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑ በመረጋገጡ በ9 /ዘጠኝ/ ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም
Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው