ሃጫሉ ሁንዴሳ !! የጌሬርሳው ንጉስ፣ የኦሮሞ አፍ፣ የመድረክ ሃዋርያ፣ የማይረሳው ዋርካ፣ ጊዜና ታሪክ የማይረሳው፣ አንበሳው አታጋይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ሃይሎች  መገደሉ ተሰምቷል። ግድያው አገሪቱን ወደ እርስ በእርስ ግጭት ለመውሰድ የታቀደ ሴራ መሆኑ ከወዲሁ እየተገለጸ ሲሆን፣ ግድያው ሃጫሉ ሰሞኑንን ከሰጠው አስተያየት ጋር እንዲያያዝ ሆን ተብሎ  እንደተካሄደም አስተያየት እየተሰጠ ነው።

አርቲስቱ ምሽት ላይ በአዲስ አበባ ገላን ኮንዲሚኒየም አካባቢ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለኢቢሲ እንደተናሩት፥ የከተማዋ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠሩ የተወሰኑ ግልሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ህዝብ እንዲረጋጋና ሰላሙን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

በአካባቢው ነበርን ያሉ ምስክሮችን ጠቅሰው የማህበራዊ ሚዲያ እድምተኞች እንዳሉት፣ ማንነታቸው ያልታወቀ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ሃጫሉን ከገላን ከተማ ጀምሮ  ሲከታተሉት ቆይተው ነው የገደሉት። አብረውት የነበሩት ጠባቂዎችቹም ቆስለዋል። የአይን ምስክር የተባሉት ወገኖች ስለገዳዮቹ ማንነት ግን እስካሁን ፍንጭ የሚሰጥ ነገር አላነሱም።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Hachalu Hundessa - Maalan Jira! **NEW**2015** (Oromo Music)

ሃጫሉ ሰሞኑንን አጤ ሚኒሊክን አስመልክቶ በሰጠው ነጻ የግል አስተያየቱ ከፍተኛ የፖለቲካ ገበያ ያደረጉት ” የሴራ” አምራቾች የሃጫሉን መገደል ከማንም ቀድመው በስፋት እያሰራጩት ይገኛሉ። ይህንን የታዘቡ እንዳሉት የአርቲስቱ የግል አስተያየት ለፖለቲካ ገበያ የዋለበት መንገድና ዛሬ የተሰማው ግድያ ተለያይተው የሚታዩ አይደሉም።

” ቴዲ አፍሮ መቀሌ ተደበቅ” የሚለውን ጨምሮ የሃጫሉን ግድያ ወደ ብሄር ግጭት፣ በተለይም ምስኪን የአማራና ኦሮሞ ህዝብ ለማጫረስ እንደ ቤንዚን የሚያገለግሉ ጽሁፎች በማሰራጨት ቅድሚያ የያዙ ክፍሎች፣ ግድያው ሊቀጥል እንደሚችል ምልክት እየሰጡ ነው። የዛሬ ዓመት ልክ በአማራ ክልል እንደተደረገውና እንደከሸፈው አይነት ሙከራ ለማድረግ እቅድ እንዳለም መረጃ ሲያፈተልክ ቆይቷል።

የመድረክ ላይ ግለቱ፣ የመድረክ ላይ ወላፈኑና በፉከራ / ገሬርሳ  አየር የሚሸፍነው ሃጫሉ ለአርት ክብር ባላቸው ወገኖች ዘንድ ከበሬታ ያለው፣ በኦሮሞ ዘንድ ማህተም የሆነ የአምቦ ፍሬ ነው። ሃጫሉ ሞቱ የሚሊዮኖች ሞት ነው። በሃጫሉ ሞት የፖለቲካ ንግድ መነገድና ሃቻሉን አክብሮ ፍትህ እንዲበየንለት መጠየቅ፣ መታገል፣ መትጋት እጅግ የሚለያዩ ጉዳዮች ናቸው።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

” ቀጣዩ ቲዲ አፍሮ ነው” በሚል በተለይም ሁለት ህዝብን ለማጫረስና በሁለት ህዝቦች መጫረስ ውስጥ ተጠቃሚ ለመሆን ላኮበኮቡ ሃይሎች መጠቀሚያ መሆን እንደማይገባ የትግራይና የኦሮሞ አክቲቪስት ዜናው በተሰማ ቅጽበት ሴራ አምራቾች ያሰራጩትን የማጫረሻ ሃረጎች እየተረጎሙ ህዝብ እንዲጠነቀቅ ሲመክሩ አምሽተዋል።

ሃጫሉ ህወሃት የተሰናበተበትን ትግል በሙያውና በወኔው ያስተባበረ መሆኑንን ያወሱት አክቲቪስቶች እንዳሉት ዛሬ ዋና የሚባሉት የኦሮሞ ድርጅቶችና ምሁራን  ከህወሃት ጋር ዳግም መግጠማቸውን ስም ጠቅሶ  ” ይህ ለኦሮሞ ውርደት ነው” በማለት በግልጽ የተቃወመው ሃጫሉ በህወሃት ዘንድ እጅግ ቂም ከተያዘባቸው ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ነው። የፈንቅል መሪ የማነ ንጉሱ ይህንን ሁሉ ካለ በሁዋላ ግድያውን ወደ ህወሃት ወስዶታል።

መስፍን በበኩሉ ” ሃጫሉን ማንም አይገድለውም፤ ህወሃት ወይም ሸኔ ነው የሚገሉት” ሲል ከማብራሪያ ጋር አስቀምጧል። አያይዞም ” ኦሮሞ አስተውል፣ አስብ፣ ንቃ ” ሲል በዚህ ሴራ ውስጥ ራስህን ከተህ የሴረኞች መቀለጃ እንዳትሆን ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ በስፖንስር አድራጊዎች አማካይነት መልኩን እየቀያየረ ሲፈጸም የነበረው አገሪቱን የማተራመስ እቅድ ሲመክን፣ ታዋቂ ግለሰቦችንና ባለስልጣንን ለይቶ የመታት ስትራቴጂ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሞ ነበር። በተለያዩ ክልሎች በተለይም አማራና ኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ የሆነው ይህ እቅድ ዛሬ ማምሻው ላይ በሃጫሉ ላይ ተወስዷል።

አብዛኞች እንደሚመክሩት ሁሉንም ጉዳይ በርጋታ መመርመርና በፊስቡክ አርበኞች የሴራ ፋብሪካ ዜናዎች፣ እንዲሁም መቀመጫቸውን በውጭ አገር ካደረጉ ሚዲያዎች የማጫረስ ዘመቻ ዜና ህዝብ ራሱን መጠበቅ አለበት። ይልቁኑም የማረጋጋትና የማጫረስ ዜና አምራቾችን መረጃ በማክሸፍ ሊተጋ ይገባል።

አዘጋጁ

ሃጫሉ ሁንዴሳ አንተ ፈርጥ ባለሙያ፣ አንተ የመድረክ ኮከብ፣ አንተ ደመ ግቡ፣ አነት ባለሙሉ ጀዝመና … አትረሳም!! አምላክ ነብስህን በአጸደ ገነት ያኑርልህ፤ ለመላው ቤተሰቦችህ፣ አፍቃሪዎችህ እንዲሁም ወዳጆችህ መጽናናት ይሁን!!

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *