የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ  “በአገሪቱ ውስጥ የሚከናወኑትን እንቅስቃሴዎች ትኩረት ሰጥተን የምንከታተልበት ወቅት ላይ እንገኛለን” ሲሉ አስታወቁ።  የድምጻዊ ሃጫሉን ህልፈት ተከትሎ ባሰራጩት አጭር መልዕክት ” ውድ ህይወት አጥተናል” ብለዋል። የሃጫሉ ህይወት ማለፍ ከተሰማ ጀምሮ በጥልቅ ሃዘን ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ሁሉ መጽናናት ከተመኙ በሁዋላ ድርጊቱን ” ክፉ” ብለውታል።

የፖሊስ ምርመራ ውጤት እየተጠባበቁ መሆኑን ካስታወሱ በሁዋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  “በአገሪቱ ውስጥ የሚከናወኑትን እንቅስቃሴዎች ትኩረት ሰጥተን የምንከታተልበት ወቅት ላይ እንገኛለን”  ካሉ በሁዋላ ” ሃዘናችንን ራሳችንን በመጠበቅና ተጨማሪ ወንጀል በመከላከል እንግለጽ” ብለዋል።

Related stories   አራዊት ጤንነቱ ታውኳል፤ ወደ አገር ቤት ለመመለስ አብነት ገብረመስቀል ምላሹ እየተጠበቀ ነው

የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግድያውን ” ህዝብን ከሕዝብ ሆን ብሎ ለማጋጨት የተወጠነ ነው” ብሏል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ይዟል። ነገ ማለዳ አጠቃላይ መረጃ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የ36 ዓመትና የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ሃጫሉ ሁንዴሳ ከሁለት ሳምንት በፊት በኦ ኤም ኤን በኩል የሰጠው መግለጫ እጅግ ሰፊ መነጋገሪያ መሆኑንን ተከትሎ ዜናው ሳይበርድ አርቲስቱ መገደሉ ድርጊቱን የአኩራፊዎች ሴራና የፖለቲካ ስሌት ያሰሉ ያከናወኑት እንደሆነ አመላካች ነው ተብሏል።

Related stories   ሱዳን ክፉኛ ተመታ የወረረችውን መሬት ማስረከቧ ተረጋገጠ፤ ከዱላው በሁዋላ " ከኢትዮጵያ ጋር መረዳዳታን መልካም ግንኙነት እንሻለን" አለች

ከወራት በፊት የቀድሞው የጦር መኮንን ከማል ገልቹ ታዋቂ ኦሮሞ በመግደል ክልሉን ማተራመስ የሚል አጀንዳ እንዳለ መናገራቸው አይዘነጋም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *