በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ መልኩን የሚቀያይር የሁከት፣ የማፈናቀል፣ የግድያ፣ የዝርፊያ እንዲሁም ዘርን የለየ ጥቃትና ዩኒቨርስቲዎችን የትርምስ ማዕከል ያደረጉ በርካታ ወንጀሎች በተደራጀ መልኩ ሲከናወን መቆየቱ የሚታወስ ነው። ሁሉም ወንጀሎች የተፈለገውን ውጤት ሳያመጡ ሲቀሩ የቅጥር ነብሰገዳዮችን በማሰማራት ባለስልጣናትን የመግደል እቅድ መዘጋጀቱን የተለያዩ አገር ወዳድ ነን የሚሉ ሲናገሩ መቆየታቸውም የሚዘነጋ አይደለም።

ዛሬ መረር ባለ ቃል መግለጫ የሰጡት የፌደራል አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ ይህንኑ አረጋግጠዋል። የአርቲስት ሃጫሉን መገደል አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሯ እንዳሉት መንግስት መረጃው ቢኖረውም እንደ ሃጫሉ ባሉት ላይ ግን ይህ ይከናወናል ተብሎ እንዳልታሰበ አመልክተዋል። ከቀን በፊት የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳም በተመሳሳይ ይህንኑ ተናግረው ነበር።

” በሰው ልጆች ህይወትና ደም ፖለቲካ መጫወት ያበቃል” ያሉት አዳነች አቤቤ በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራና በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የተካሄደውን አፈና ያካሄዱት ላይ ስለተደረገው ምርመራና ተጠርጣሪዎች ስለመያዛቸው አውስተው የፍርድ ሂደቱ የተጓተተበትን ምክንያትም ግልጽ አድረገዋል።

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

የቀድሞው የደህነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋና ሌሎች ተፈላጊዎች ባለመያዛቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረጉት ተጠርጣሪዎች ላይ ብይን ለመስጠት ጊዜ መውሰዱን ያመለከቱት አዳነች አቤቤ ” አቶ ጌታቸውን በሃይል ለመያዝ ያልተሞከረው ከትግራይ ሕዝብ ጋር መጣላት አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው” በለዋል። ሆኖም ግን አሁን በቅርቡ የፍርድ ሂደቱ እንደሚጠናቀቅ ይፋ አድርገዋል።

የአማራ ክልልና የጀነራል ጸአረም ገዳዮች የፍርድ ሂደት በተመሳሳይ ያልተፋጠነበትን ምክንያት የጠቆሙት ሚኒስትሯ፣ የሃጫሉን ግድያ አስመልክቶ በአፋጣኝ ህግ ተጋባራዊ እንደሚደረግና ካሁን በሁዋላ ህግን ተግባራዊ ለማድረግ ማፈግፈግ እንደማይታይ አረጋግጠዋል።

” እስካሁን” አሉ ሚንስትሯ ” እስካሁን የታፈነ ህዝብ መብቱን ይጠቀም፣ ይለቀቅ በሚል ነው ትዕግስትን የመረጥነው” ሲሉ መንግስት ለዴሞክራሲ ግንባታ በርካታ ዋጋ መክፈሉን አመላክተዋል።

Related stories   "በፕሮፓጋንዳ እስካሁን የተወናበድኩት ይበቃኛል ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ይገባል ... ወጣቱን ያለ እድሜው ህይወቱን ይቀጩታል"ሌ.ጀ ዮሐንስ

ፖሊስ በተመሳሳይ በሰጠው መግለጫ ከነገ ጀምሮ ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ይመለሳል። ይህንን ለማስተጓጎል የሚደረግ ሙከራ በትዕግስት አይታለፍም። ፖሊስ፣ የድህንነት ተቋም፣ የሰላም ሚኒስትር፣ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ሃይልላት ይህንን ተግራዊ እንዲያደርጉ በህግ በተሰጣቸው ስልታን መሰረት መታዘዛቸውን ይፋ አድርጓል። መክሯል።

ዝርፊያ ለማካሄድና ፣ የብሄር ግጭት ለማነሳሳት የተደራጁ ሃይላትን የጸጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ያስታወቀው ፖሊስ ” ሊያጠፉህ ነው፤ ራስህን ተከላከል” በሚል አንዳችም የጥቃት ምልክት በሌለበት ሲቀሰቅሱና ሲያስተባብሩ የተደረሰባቸው መያዛቸውን ይፋ ያደረገው ፖሊስ አብንና ባላደራ የሚሰኙት ፓርቲዎችም የዚሁ ድርጊት ተባባራሪና ተሳታፊ ሆነው ከጭብጥ ማስረጃ ጋር መያዛቸውን አመክቷል።

በርካታ የግልና የመንግስት ንብረቶች መቃጠላቸውን ይፋ ያደረገው ፖሊስ ካሁን በሁዋላ ይህ እንደማይቀጥል ይፋ አድርጓል።

በአምቦ የሃጫሉን አስከሬን እንወስዳለን በሚል ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ወገኖች በወረወሩት ፈንጂ የሟች አጎት ህይወት ማለፉ ታውቋል። ሌሎችም ለቀስተኞች ተጎድተዋል። ተጨማሪ የሞቱ እንዳሉም ተሰምቷል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

በተለያዩ አካባቢ ዝርፊያን ማዕከል ያደረጉና ንብረትን በማውደም ላይ የተሰማሩ ሃይሎችን የጸጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑንን ፖሊስ አስታውቋል። አምቦና ቡራዩ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ከህወሃትና ከኦነግ ሸኔ ጋር መልዕክት መቀባበላቸውን የሚያረጋግጥ የጽሁፍ መረጃ ማግነቱን የኦሮሚያ ክልል አስታውቋል።

በርካታ በቅጥር ነበሰ ገዳይነት የሰለጠኑ ሃይሎች ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀደም ሲሉ ያስታወቁ ወገኖች እንደሚሉት አገሪቱን ለማተራመስ ይጠቅም ዘንድ በተመረጡ ዜጎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ሊቀጥል እንደሚችል ስጋታቸው አስቀምጠዋል። ህዝብ አካባቢውን በንቃት የመጠበቅና ከመንግስት የጸጥታ ሃይላት ጋር በህብረት ሊሰራ እንደሚገባ የጊዜው ሁኔታ የገባቸው እየወተወቱ ነው።

ይህ ሁሉ የሚሆነው ባቋራጭ ወደ ቤተመንግስት ለማምራት ሲሆን መንግስት እንዳለውና በተለያዩ ሚዲያዎች እንደተሰማው ጦርነቱን አዲስ አበባ ጀምሮ ለመጨረስ የተያዘው እቅድ እንዲተገበር የሆነ ነው።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *