የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በሰጠው መግለጫ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አብን እና ባልደራስ በአዲስ አበባ የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ከትናንት ጀምሮ በመዲናዋ የጸጥታ መደፍረስ እንዳጋጠመ አስታውቀዋል።

የግል እና የመንግሥት ተሽከርካሪዎችን መሰባበር እና ማቃጠል፣ የዜጎችን ያፈሩትን ሃብት እና ንብረት የመዝረፍ እንቅስቃሴ ነበር” ያሉት ኮሚሽነሩ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከተማዋ ሁከት እና ብጥብጥ በመፍጠር ህብረተሰቡ እርስ በእርሱ እንዲጋጭ እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ እንደነበር ገልፀዋል።

የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ከቀላል እስከ ሞት ድረስ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ኮሚሽነሩ “ዛሬ እና ትናንት 57 የሚሆኑ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል” በማለት ሁለት አባላት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

በዜጎች ላይ ደረሰ ባሉት ጉዳት “ትናንት እና ዛሬ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል” ካሉ በኋላም፣ ነዋሪዎች ህይወታቸው ያለፈው “በቦምብ፣ ጥይት፣ በድንጋይ እና በመሳሰሉት ነው” ብለዋል።

ንብረትነታቸው የግሰብ እና የመንግሥት የሆኑ 250 ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል፣ 20 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ሲሉም አክለዋል።

“የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጭምር የተሳተፉበት በተለይ የባልደራስ እና አብን አመራሮች እና አባላት በግልጽ ቲሸርት በመልበስ እና የፓርቲያቸውን ባንዲራ በመያዝ የከተማዋ የተለያየ አከባቢ ላይ በመንቀሳቀስ የብሔር ግጭት ለመፈጥር ሰፊ እንቅስቃሴ ለመፍጥር ሲደረግ ነበር” ብለዋል።

“በተለያዩ የከተማው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ አንዱ ብሔር ሌላውን ሊጠቃ እንደመጣ፤ እየተወረረ እንደሆነ” በማሳወቅ “እንዲከላከል” ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር ብለዋል።

በከተማዋ ሰዎችን በማስቆም መታወቂያ የመጠየቅ እንቅስቃሴም እንደነበረ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

BBC Amharic

Related stories   ሰዓረ በተገዛ ጠባቂያቸው ተገደሉ፣ የአማራ ክልል ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት አልፈዋል፤ "አሳምነው ጽጌ እርምጃ ተወስዶባቸዋል" ቢባልም መንግስት መሸሻቸውን አስታውቋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *