Share and Enjoy !

Shares

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ ዛሬ [ረቡዕ] ማምሻውን ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመሆን ለመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የማክሰኞው የጃዋር መሐመድ እንቅስቃሴ የሰኔ 15 ግድያ ለመድገም ያለመ ነበር ሲሉ ተናገሩ።

ኮሚሽነሩ አክለውም አዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባ የሚያልቅ የአመጽ እንቅስቃሴ የመምራት እቅድ ወጥቶ፣ በጀት ተበጅቶለት አመራሮችን ለመግደል ሲመራ የነበረ ነው ሲሉ የተፈጠረውን ሁኔታ ገልፀውታል።

በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ በበኩላቸው ስለ እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ሁከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ ቤተሰቦቹ እየተወሰደ ሳለ “መንገድ በማስቀየር፣ በመቀማት አመፁን አዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባ እንዲያልቅ ሲቀሰቀስ” ነበር ካሉ በኋላ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሞ ባህል ማዕከል ስብሰባ ላይ እንዳሉ እያወቁ በቀጥታ ወደዚህ ተቋም ጥበቃውን ሰብረው መግባታቸውን ተናግረዋል።

Related stories   ሱዳን ባዘጋጀው መድረክ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ልዩነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አምባሳደሩ አሳሰቡ

በወቅቱ የተፈጠረውን ሲገልፁም ትጥቅ አቀባብለው በመግባት አመራሮቹ ላይ ጭምር ተጨማሪ የሰኔ 15 ዓይነት ተግባር ለመፈፀም እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ በኦሮሞ ባህል ማዕከል የነበረው የፖሊስ ኃይል አመራሮቹ በሌላ አዳራሽ እንዳሉ በመናገር ወደዚያ እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ገልፀው በመካከል ግን የአንድ የፖሊስ ህይወት ይዘውት ከመጡት ታጣቂ ቡድን በተተኮሰ ጥይት መሞቱን ገልፀዋል።

በስፍራው የነበረውን የፀጥታ ኃይልም “በዚህ መካከል የመልስ ምት አለማደረጉ እንጂ የበርካታ ሰዎች ህይወት፣ የበርካታ አመራሮች ግድያ በዚያ ባህል ማዕከል ለመፈፀም እቅድ ነበረ” ሲሉ ተናግረዋል።

የፖሊስ ምርመራ በዚህ መንገድ የእየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ “የታቀደ፣ የተጠና ረዥም ጊዜ የደም ማዕበል ለመፍጠር ሴራ የነበረ መሆኑ ለመግለጽ እንወዳለን። ምርመራችንም የሚያሳየው ይህንኑ ነው” ብለዋል።

Related stories   አባይ ወልዱና ዶ/ር አብርሃም ተያዙ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ከሃጂ ጀነራሎችና መኮንኖች ከነጭፋራቸው ተደመሰሱ

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ማምሻውን በሰጡት በዚህ መግለጫ ከዚህ በፊትም ወደኋላ ሄደን የበርካታ ሰዎች ሕይወት ያለፈበትን የጥቅምቱን ግርግር መነሻ ያደረገ ምርመራም ከዚሁ ምርመራ ጋር አብሮ የተያያዘ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ኮሚሽነሩ የ97 ሰዎች ህይወት ያለፈበት ምርመራ በዚህ መንገድ አብሮ ይታያል ሲሉ አረጋግጠዋል።

“በተለያየ ጊዜ በሚዲያ ላይ እየወጡ የሚጠሯቸው የተለያዩ የጦርነትና ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት፣ ስርዓት ለማፍረስ የሚደረጉ የተለያዩ ቅስቀሳዎች ጭምር በዚህ ውስጥ ተካትተው የሚታዩ ይሆናል።”

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ በበኩላቸው ስለ እስክንድር ነጋ ሲገልፁ “የመልስ ምት ያስፈልጋል፤ ኦሮሚያ ላይ እኔ የምወክለው እኔ የምታገልለት ህዝብ ነው እየተጎዳ ያለው፤ ስለዚህ አዲስ አበባ ያለህና ሌላ ቦታ ላይ ያለህ የዚህ ቡድን የሆንክ ተነስ” መልስ ስጥ የሚል ቡድን በአዲስ አበባ ውስጥ ተደራጅቶ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነበር ብለዋል።

Related stories   ስብሃት ነጋ የትህነግን የውጪ አገር ሃብትና ንብረት "ለትግራይ ሕዝብ ጥቅም ሲባል" ይፋ እያደረጉ ነው

በዛሬው እለት እስከአሁን ድረስ በመረጃ 10 ወጣቶችን በተለያዩ 10 ቦታዎች በመመደብ ተሽከርካሪ በመመደብ የተለያዩ ሎጀስቲኮችን በማመቻቸት ቅስቀሳዎች ሲደረጉ እንደነበር ገልፀዋል።

bbc amharic

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *