“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሃጫሉ ተሸኘ ! ” ሃዘን መቀመጥ እንኳን አልቻልንም ያሳዝናል” ቤተሰቦች

የሃጫሉ ወንድም ሃብታሙ ሁንዴሣ አሳፋሪውን የአስከሬን ቅርምት ተከትሎ  “ያሳፍራል፤ ያሳዝናል፤ (ሃጫሉ) ባለትዳር ነው፤ ሚስቱ አምቦ እንዲቀበር ትፈልጋለች፤ ቤተሰብ አለው – ቤተሰቡ አምቦ እንዲቀበር ይፈልጋሉ፤ ወንድሞች አሉት – ወንድሞቹ አምቦ እንዲቀበር እንፈልጋለን፤ ሃጫሉ በሕይወት እያለ ስሞት ዕትብቴ በተቀበረበት አምቦ ቅበሩኝ ብሏል፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ አስከሬኑ ላይ የሚደረገው ግብግብ ለምን እንደሆነ አይገባንም፤ ከሞቱ ይልቅ ያዋረዱት እዚህ ላይ ነው” ሲል ከሽኝቱ በሁዋላ ለቪኦኤ ተናግሯል

ሃጫሉ ከአስደንጋጩ የህልፈቱ ዜና በሁዋላ አነጋጋሪ የሆነውና የበርካቶችን ልብ የነካው አስከሬኑ በሰላም እንዳያርፍ የነበረው ፍትጊያና ውንብድና ነው። ወንድሙ ሃብታሙ ሁንዴሳ አፍረናል። አዝነናል ሲል በአጭሩ እንደገለጸው ብቻ ሳይሆን የሞራል ማጣትም ጭምር ነው። እጅግ ልብ የሚሰብር መሆኑንን አሁንም ቤተሰቦቹ ” ሃዘናችን እንዳንወጣ፣ ለቅሶ እንዳንቀመጥ ሆን” ሲሉ ያስረዳሉ።

ሚስት፣ ቤተሰብ፣ ወንድሞች ፍላጎታቸው  ራሱ ሃጫሉ በሕይወት እያለ ” ስሞት አምቦ ቅበሩኝ” እንዳለው ይህንኑ ተግባራዊ ማድረግ ነው። ወንድሙ ሃብታሙ ለቪኦኤ  ” ከእኛ ፈቃድ ውጪ … ” ሲል በተፈጠረው ሁሉ ማዘኑንና ወንድሙ ሁለቴ መሞቱን አመልክቷል። እንግዲህ ቤተሰብ ይህንን እያለ ነው ፖለቲከኞች ከቤተሰብ በላይ ሆነው የአስከሬን ባለቤት እንሁን ያሉት።

ይህን ጀግና ለራስ አላማና ፍላጎት ሲባል ከሞተም በሁዋላ ማንገላታት፣ በሰላምና በክብር አስከሬኑ እንዳያርፍ ማድረግ፣ አልፎ ተርፎም ለቅሶ ላይ የተቀመጡ ቤተሰቡን መሳጣት ምንስ ትርጉም የሰጠዋል? በብዙ ትንቅንቅ ለቤቱ የበቃውን አስከሬን ቤት ድረስ ሄዶ እንደገና አምጡ ማለትስ ምን የሚሉት ድፍረት ነው? ከቤተሰብ ፍላጎት ውጪ የአስከሬን ነጠቃ የተፈለገውስ ልምንድን ነው?

Related stories   ኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነትን " ወግድ አለች" መንግስት መግለጫ ሰጠ

አሁንም የሃጫሉ ወንድም ” ምክንያቱን መረዳት ያስፈለጋል፣ ዝም ብሎ በስሜት መረዳት አግባብ አይደለም፤ በጥቅሉ ያሳዝናል፤ ሃጫሉን ማክበርም አይደለም ” ሲል ሳያመዛዝኑ አድርጉ የሚባሉትን ለማድረግ የሚረባረቡትን አንጀቱ እየተቃጠለ መክሯል።

አስከሬኑ በክብር ወደ አምቦ እየሄደ ባለበት ወቅት ቡራዩ ኬላው አካባቢ በመጠበቅ ” አዲስ አበባ ነው የሚቀበረው” በማለት ግርግር የፈጠሩ አካላት ያከናወኑትን ፖሊስ ሲናገር ውሸት መሆኑንን የሚናገሩ በርካታ ነበሩ። አሁን ግን አባት፣ ወንድምና ቤሰሰብ ከዛም በላይ ሚስት ” በኛ ፈቃድና ጥያቄ ነው አስከሬኑ ወደ አምቦ እንዲመጣ የተደረገው” በማለት አደባባይ ሲናገሩ እኒህ ክፍሎች ምን ይሉ ይሆን? እንዴትስ ያስተባብሉታል? ወይስ ቤተሰብን ” አሁን ጉዳዩ ገባን” ሲሉ ይቅርታ ይጠይቃሉ?

ሃጫሉ በቅጥረኞች ሞት። ድንገት የተሰማው ዜና ሃዘኑ ክፉኛ ሆነ። በመቀጠል በባህላችንና በእምነታችን ክቡር የሆነውን አስከሬን እየተጓተቱ ተሻኮቱበት ይህ ለሃጫሉ ከጥይቱ በላይ ዳግም ሞት ሆነ። ሁሉም አልፎ ቤቱ ድረስ በመሄድ አስከሬኑንን ከቤተሰቡና ከባለቤቱ ጉያ እንውሰድ የሚሉ ሃይሎች አጎቱ ያልፉ ዘንድ ምክንያት ሆኑ። ህዝብ ሃዘኑንን እንዳያከናውን ተደረገ። ይህ ላጀግናችን ሌላው ሞት ሆነ። ባንዶችና አገር አፍራሾች ይህ ሁሉ እየሆነም አላፈሩም። አሁን ደረስ ሃጫሉን ዳግም እየገደሉት ነው። አይ መርከስ!!

ሃጫሉ የግድያ ማስፈራሪያ ይደርሰው እንደነበር በይፋ ተናግሯል። አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ አስታውቋል። ቤሰሰቦቹም መስክረዋል። ባልደረቦቹም ስጋቱን ይፋ አድረገዋል። እንግዲህ ማስፈራሪያው ከመንግስት ወገን ከሆን ሃጫሉ በምንም መስፈርት አገር ጥሎ ይወጣል እንጂ ኢንቨስትመንት ውስጥ ገብቶ አይሰራም ነበር። ይህ ተራ ሂሳብ ነው።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

ሚሌኒየም አዳራሽ ከመዝፈኑ በፊት ለሃጫሉ ቤት፣ መኪናና ብር እንስጥህ ሲሉ የህወሃት ሰዎች እንደጠየቁት በአንደበቱ ከሁለት ሳምንት በፊት አስታውቋል። ማስፈራሪያ እንደበዛበትም ደግሞ አስታውቋል። ከእነ ጃዋር ጋርና አሁን አክርረው የተቃውሞ ዘመቻ ላይ ያሉትን በገሃድ የሚተችና ዳግም ከወያኔ ጋር ህብረት መፍጠራቸውን ” ክህደት” እያለ በተደጋጋሚ ይነቅፍ የበብረው ሃጫሉ፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ አለያ እርምጃ እንደሚወሰድበት በይፋ በፊስቡክ ተጽፎ ነበር። እንግዲህ ይህን ሁሉ መረጃ በመገጣጠምና አስከሬኑ አዲስ አበባ ይቀበር የሚለውን ግብግብ በማያያዝ ምላሹን መፈለግ የአስተዋይ ዜጎች ተግባር ይሆናል። ወንድሙ ሃብታሙም ያለው ይህን ነው። እናስብ!!

የ36 ዓመቱ ወጣት ሃጫሉ ዛሬ ተሸኝቷል። ተወልዶ አደገባት አምቦ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አስከሬኑ አርፏል። ሃጫሉ የሚረሳ አይሆንም። በታሪካና በኪነ ጥበብ የሚታወስ እንዲሆን ተደርጎ መታሰቢያ ይቆምለታል ተብሏል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቤተሰቦቹና ሃብታሙ ሁንዴሳ አስተያየት ከመስጠታቸው በፊት የሚከተለውን ብለዋል። ትርጉም ፌስቡክ

ሃጫሉን በኖረበት በእዚሁ ከተማ እንድንቀብረው ዝግጅት ነበረን። ቤተሰቦቹ በትውልድ መንደሩ እንቅበረው ስላሉ የነርሱ ፈቃድ ማከበር ነበረብን፣ ሃጫሉ አንድ ቀን ይገድሉኛል እንዳለ አለፈ፣ ሃጫሉን አንድ ግዜ ብቻ አይደለም የገደሉት ፣
አስከሬኑ ወደቤተሰቦቹ እየተሸኘ ሳለ መሣሪያ የታጠቁ አስከሬኑን ነጥቀው ወደ አዲስ አበባ መለሱት ፣ ህዝብ በተኩስ ለውጥ እንዳይጎዳ ብለን ዝም አልናቸው ፣ ይህም አንሶ የብልፅግና ፅ/ቤት ድረስ ዘልቀው ሥራ ላይ የነበረውን ሰው በመግደል ግጭት ለመቀስቀስ ሞከሩ፣ ያንንም በትዕግሥት አለፍነው ፣ በትናንትናው እለት ደግሞ ኦነግ ሸኔና የወያኔ ታጣቂዎች በቅንጅት ወላጆቹ ቤት ድረስ ዘምተው አጎቱን በጭካኔ ገደሉት፣ ይህ ለሃጫሉ 3ኛ ሞት ነው ።
ለሃጫሉ ግድያ ተጠየቂዎቹ ኦነግ ሸኔ ወያኔና በህዝብ ትግል ገብተው እዚህ አዲስ አበባ ቁጭ ብለው ህዝብ የሚያምሱ ናቸው ፣ ሃጫሉን ለእርድ ያዘጋጁት የግዲያው ተባባሪዎች ከሳምንት በፊት ሚዲያቸው ላይ አቅርበውት ምን እንደጠየቁት ማንም ሰው የሚያውቀው ነው፣ ያ ቃለመጠይቅ የተዘጋጀው ለሴራቸው ስኬት ህዝብን ከህዝብ ለማባላት በማሰብ እንደነበር ግልጽ ሆኖአል።
ከጥያቄያቸው አንዱ ትግራይ ሂዶ ከወያኔ ጋር መነጋገር እንዴት ወንጀል ነው ትላለህ ? ድሮ ድሮ ኦሮሞ ኦሮሞ ትል ነበር አሁን ቋንቋህን ቀይረሃልም ነበር ያሉት ።
ሃጫሉ እነርሱ የግል ህይወታቸውን ሲያደላድሉ ከጠላት ጋር ግንባሩን ሰጥቶ ተናነቅ የኖረና ጨቋኝ ሥርአት ለማንኮታኮት መስዋእት የከፈለ ጀግና ነው ፣ በነፃነት ወደ አገራቸው ሲመለሱ አክብረን የተቀበልናቸው ግን ለህልፈቱ ተባባሪ ሆኑ ።
ከአሁን ቦሃላ ትዕግሥታችን ተሟጦአል። ያሳየነው ትእግሥትና ፍቅር ከፍርሃት የመነጨ አይደለም። ወያኔ፣ ኦነግ ሸኔና አዲስ አበባ ሆኖ ውጥረት የሚያመርተው ቡድንና ከግብፅ ጋር ተባብረው አገራችንን እንዲያተራምሱ የሚፈልጉ ሃይሎች አላማቸው አይሳካላቸውም ፣ ክልላችን ሰላም እየነሱ ያሉ እነዚህን ሃይሎች የገቡበት ገብተን ከክልላችንን እናጠራቸዋለን።
ከበሰበሰው ሥልጣን ጠራርገን ያባረርነው ወንጀለኞች እርስ በርስ አባልተውን ዳግም ወደሥልጣን ሊመለስ አይችልም ። ኦሮሞ ግንድ ነው፣ አባት ነው ፣ታላቅ ነው በኖረው ባህልህ ከሁሉም ህዝብ ጋር በፍቅር መኖርህን ቀጥልበት። እርስ በርስ በመባላት ለጠላቶቻችን ሴራ እንዳንመች አደራ እላለሁ ……”
ሳሙአል

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0