የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጥላጫ ንግግር የሚያደርጉ ሚዲያዎችን እና ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑ ተነገረ ። ኤምባሲ በሰሜን አሜሪካ ተቀምጠው ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፍጅት ለማምጣት የሚሰሩ ሚዲያዎችን እና ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ መስራት የጀመረው ከታዋቂ ኢትዮጵያዊያ ጋር ህብረት በመፍጠር መሆኑ ታውቋል።
በኢትዮጵያ የዘር ፍጅት እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ ሚዲያዎች በበጀት፣ በቴክኒክ ድጋፍና በስትራቴጂክ የቅስቀሳ ስልት እርዳታ እንደሚደረግላቸው በተደጋጋሚ የሚደመጥ መሆኑ ይታወቃል። ይህንኑ ተከትሎ ምንም ምክንያት ሳይኖር በፈጠራ አንዱን ብሄር ከሌላው ጋር ለማጋጨት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ዘመቻቸው ከቀን ወደ ቀን አድጎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
የታዋቂውን ድምጻዊ ሃቻሉ ሁንዴ ግድያ ተከትሎ በእቅድና በትሥሥር እየተከናውነ ያለው አገርን የማፍረስና ህዝብን የማጋደል ሩጫ ያሳሰባቸው ወገኖች ከኤምባሲው መስራታቸው ታውቋል።
እነዚህን የጥላቻ ንግግር የሚያስተጋቡ አካላትን ለህግ ለማቅረብ በሚካሄደው ግብረ ሃይል ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰብ እንዳሉን ከሆነ መረጃዎች በአግባቡ እየተጠናከሩ እንዳለ እና ኤምባሲው መሪነቱን በመውሰድ ክሱን ይመሰርታል፡፡
የዜናው ሃሳብ ናትናኤል መኮንን

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   "የትግራይ ልሂቃን የት ገቡ? ዳያስፖራው ለቆሰቆሰው፣ ወያኔ ላነደደው እሳት ማን እንደሚጠየቅ ለምን ፊትለፊት አይናገሩም ? "

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *