ኢትዮ ጎልጉል – ጦር ሰራዊት መስለው መድረክ ላይ የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከፊትለፊታቸው ለተቀመጠው አገር አረጋጊ ሃይል ” ተኳሹ ብቻ ሳይሆን አስተኳሹን ” አሉ። ቀጥለውም አስተኳሹ ሌብነቱ እንደማይታውቅ አስመስሎ ፣ በውስጥ የተሰገሰገ፣ የሚሰራ የሚመስልና በብሄር ጥላ የተመሸጉ መሆኑን ጠቆሙ። ይህ ሃይል ተኳሹ እንደተያዘ ሁሉ እነዚህ አስተኳሾች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይገባል አሉ። መዋልም አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።

ከማሳሰቢያቸው በፊት ግን የኢትዮጵያን መለዮ ለባሾች፣ የካቢኔ አባሎችን፣ የክልል አመራሮችን፣ ጥቅል የጸጥታ ሃይሎች፣ እንዲሁም ሽማግሌዎሽ፣ ወጣቶችና አባገዳዎች ጸጥታ እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጾኦጽዖ ” ክብር ይገባችኋል” ሲል አመስግነዋል። ባልደረቦቻቸውን ቢሮ እያደሩ በቁርጠኛነት አገራዊ ሃላፊነታቸውን ስለተወጡ በተመሳሳይ ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብይ የባዶ ህልም ቅዠት እንደሆነ የገለጹትን የፌስቡክ ትግል ” ባዶ ህልም እንደሆነ ማሳየት ይገባል” ካሉ በሁዋላ አሁን የሆነውና እየሆነ ያለው ሁሉ ድራማ እንደሆነ ጠቁመው ” ድራማው በርካታ ደራሲያንና ተዋናዮች አሉበት” ሲሉ ገልጸዋል። “እናም” አሉ አብይ ” እናም በዚሁ የባዶ ህልም ቅዠት የከተማ ጦርነት ሊያስተምሩን የፈለጉትን የከተማ ጦርነት እንዴት እንደሆነ እናስተምራቸዋለን” ሲሉ የረዥም ጊዜ ውጥኑ መክሸፉን አብስረዋል።

Related stories   ጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል – በትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪ ሆነው ተሾሙ

በገንዘብ፣ በሚዲያ፣ በሰላማዊ ትግል ስም ህዝብን ለማተራመስ፣ እርስ በእርስ ለማባላትና ለማጫረስ ሲታቀድ ኖሮ ሳይሳካ የከሸፈው ትግል ካሁን በሁዋላ ዳግም እንዳይከሰት አስተኳሾች በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባና ይህንንም ማድረግ ለነገ እንደማይባል አብይ ይፋ አድረገዋል። ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ጋር በማበር የባንዳነት ሚና የሚጫወቱና በባንዳነት የተካኑትን አስመልክቶ በይፋ ባይናገሩም መንግስት ካሁን በሁዋላ እንደሚያመርና ህግን እንደሚያስከበር ግን አስረግተው ተናግረዋል።

Related stories   የባይደን አስተዳደር ፖሊሲ አምስተኛው ምሰሶ የኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን ቡድን መወሰንና የ 2021 ምርጫን ማዋደቅ (1ኛ ክፍል 2)

ካለፉት ሶስት ሰኔዎች ትምህርት መወሰዱን ያስታወቁት አብይ ” ካሁን በሁዋላ ሰኔ ለእርሻ ብቻ” ሲሉ የህግ ማስከበሩና የአስተኳሾች ላይ ዘመቻ ያለ አንዳች ማቅማማት ተጋባራዊ እንደሚሆን አስታውቀዋል። ከፊታቸው የተቀመተውንም ሃይል ሌት ተቀን በመስራት ይህንኑ ተግባሩን እንደሚወጣ እምነታቸውን አስታውቀዋል።

የፍርድ ሂደቱ እንደቀድሞው ጥፍር በመንቀል፣ ጨለማ ቤት በማስቀመጥ፣ በመግረፍና በማሰቃየት እንደማይሆን ማረጋገጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስርትሩ፣ ህግን በህግ እናስከብራለን ሲሉ ተደምጠዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *