ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በትግራይ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሊሰቀል ነው፤ ” አብይ የውሳኔ አሰጣት ፍጥነቱ አዙሮብናል”

ኢትዮ ጎልጉል -ከአዲስ አበባ ለስራ መቀሌ የከረመ አንድ የአይቲ ባለሙያ ጠዋት ወደ ስራ ሲሄድ ሰዎች ዘፍ ስር ተቀምጠው ያያል። ባልደረባውን “ሰዎቹ ምን እየሰሩ ነው?” ብሎ ይጠይቃል። ባልደረባው እቁብተኞች መሆናቸውን ይነግረዋል። ይህ ሰው ከስራው ሲመለስ ሰዎችሁ እዛው ዛፍ ስር ተቀምጠው ያያቸዋል። ከዛም ባልደረባው የአካባቢው ነዋሪ በመሆኑ ” ሰዎች እስካሁን ምን እየሰሩ ነው” ሲል ደጋሚ ይጠይቃል።

ነገሩ አንድ ሰው እቁቡን መልቀቅ ፈልጎ የተደረገ ስብሰባ ነበር። ተሰብሳቢዎችሁ ሰውየው እቁብን ለምን መልቀቅ ፈለገ? ገንዘቡን ምን ሊያደርገው ነው? ከእቁቡ እንዲወጣ ከጀርባ ሆኖ የሚገፋው ማን ነው? ማን አነሳሳው? በሚሉና መስል ጉዳዮች ሲነታረኩ ነው ቀኑንን ሙሉ ስብሰባ የዋሉት። ይህንን ከዓመታት በፊት የተደመጠ ገጠመኝ ማስታወስ የተፈለገው ዛሬ ከተሰማው አዲስ መረጃ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው።

የህወሃት ሰዎች ” የአብይ ፍጥነትና የውሳኔ አሰጣጥ አዙሮብናል” ማለታቸውን የአካባቢው ነዋሪ የሆነ የቅርብ ሰው ይናገራል። ይህ ውስጥ አዋቂ ብቻ ሳይሆን ዶክተር ደብረጽዮንም የዶከተር አብይን ኤርትራ ደርሰው ነገሮችን የቀያየሩበትን ፍጥነት እጅግ በመደነቅ በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ጉባኤተኛውን እያሳቁ መገረማቸውን ሲናገሩ ታይቷል።

ላለፉት አርባ ዓመታት አጀንዳ ለመቅረጽ ወር፣ ተሰብስቦ ለመወሰን ወር፣ ወደ ተጋባር ለመቀየር ወር ሲፈጁ ህዝብ ይጠብቅ ነበር። ሁለጊዜ ግምገማ ሲካሄድ ህዝብ ቁጭ ብሎ የግምገማ ውጤት ሲጠብቅ ነበር። የለውጡ ሰሞን ሰላሳ ቀናት ግምገማ ሲቀመጡ በተመሳሳይ ህዝብ ቁጭ ብሎ ይጠብቅ ነበር። ዛሬም ድረስ በስብሰባና በግምገማ ጊዜ መብላት በህወሃት ቤት የተለመደ መሆኑ ቅሬታ እያስነሳ ነው።

እነሱ አንድ ጉዳይ ይዘው በዛ ጉዳይ ሲመከሩ ዶከተር አብይ በላይ በላይ ውሳኔ እየሰጡ መብረራቸው ለህወሃት ራስ ምታት ሆኗል። ዶክተር አብይ ያለ አንዳች የወረቀት ሪፖርት የፖሊስ፣ የመከላከያ፣ የድህንነት፣ የሴክተር ተቋማት፣ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና አስፈላጊ የስራ ሪፖርቶች በኔት ወርክ ቢሯቸው ስለሚደርስ ጊዜ አይፈጁም። በአንድ ወቅት ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የወረቀት ሪፖርት ጋጋታ አይስፈልግም ሲሉ በኔት ዎርክ ሁሉም ሪፖርት እንደሚደርሳቸው መናገራቸው ይታወሳል።

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜያቸውን በወጉ በመተቀም እዚህ ታይተው፣ ሌላ ቦታ ሲከውኑ መዋላቸውን ማድመጥ፣ ከራሳቸው የማህበራዊ መረቦች ማንበብ የተለመደ በመሆኑ የህወሃት ግራ መጋባት ብዙም አይገርምም። የሃሳቡ መነሻ የሆነው የህወሃት የቅርብ ሰው እንደሚለው ዶከተር አብይ ጠዋት ችግኝ ይተክላሉ፣ ቆየት ብለው ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ይታደማሉ። በድንገት የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ። መከላከያ ያዘምናሉ። ማምሻውን ዛፍ ውሃ ያጠጣሉ። የግንባታ ክትትል ያደርጋሉ። የፕሮጀክት አፈጻጸም ይከታተላሉ። ይህንን ሁሉ እያደረጉ በአጭር ኦረንቴሽን ውሳኔ ይወስናሉ፣ ያስወስናሉ። ይህ ፍጥነታቸው አርባ ዓመት ለወራት መሰብሰብ የለመደችውን ህወሃትን አዙሮባታል። እናም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መሰረታዊ እሳቤ ማነቆ ሆኖባት አዲስ ነገር ላይ ከማተኮር ይልቅ በተዘጋና ባለቀ ጉዳይ ላይ ለማተኮር ተገዳለች። ይህ አካሄድ ጉድ እያደረጋት ነው።

ውስጥ አዋቂው የብልጽግና ፓርቲን አመሰራረት እንደ ትንግርት ያስቀምታሉል። አንድ ትልቅ የኦሮሞ ፓርቲ እነ አቶ ለማ መገርሳ ይዘው እንዲመጡ፣ በውቀቱ ተዳክሞ የነብረው ብአዴንና እየወላለቀ ያለው የደቡብ ህዝብ ፓርቲ አንድ ላይ ተቀምጠው መንግስት ለማዋቀር ህወሃቶች አቅደው እንደነበር ያነሳሉ። በማይታመን መልኩ ዶከተር አብይ ጃዋር ባደራጀው የኦሮሞ ፓርቲዎች ህብረት ላይ ዶከተር አብይ ሳይታሰብ ተገኝተው በለማ መገርሳ ምትክ ባለቀ ሰዓት ፊርማቸውን አኑረው እቅዱን አመከኑት። በዛን ቀን ዶከተር አብይ ሳይታሰብ በውህደቱ ላይ መገኘታቸው በሚስጢር ሴራውን ሲሰሩ ለነበሩት የመብረቅ ያህል ድንጋጤ የፈጠረባቸው ሲሆን፣ ለኦዲፒ ሰዎች ግን የህብረታቸው መጀመሪያ ቀን ነበር ማለት ይቻላል። በውስጣቸው የነበረውን ልዩነት አስወግደው እንደ ደርጅት የወጡበት አጋታሚምም ሆኖላቸዋል።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ኦዲፒ ሳያውቅ ኦዲፒን አምክኖ በአዲስ የኦሮሞ ፓርቲ ከህወሃት ጋር አዲስ መንግስት ለመመስረት የተወጠነው ሴራ እንዴት ከሸፈ ? የሚለውን ሪፖርት እናስከትላለን። የሆነ ሆኖ ግን ይህ በሆነ ማግስት የህወሃት ሰዎች ከንቅላፋቸው ሲነሱ ኦዲፒ ራሱን ማምከኑንን ይፋ ማድረጉን ሰሙ። በዛው ቅጽበት አጋር ፓርቲዎችና እሀት ድርጅቶች ራሳቸውን ማክሰማቸው ተሰማ። ይህንን እንደ አክሺን ፊልም ላይ በላይ የሚደራረብ ፈታን ውሳኔ ህወሃቶች በዜና ከመስማት የዘለለ እድል አልነበራቸውም። ሳይውል ሳያድር ብልጽግና እውን ሆነ። አሁን ዜናውን የሰሙት ህወሃቶች የድርጊቶች ፍጥነት የማሰቢያ ጊዜ ስለነሳቸው በደፈናው ብልጽግና የሚባለውን ፓርቲ ህጋዊ እንዳልሆነ ጠቅሰው ከመከራከር የዘለለ እድል ሊያገኙ አልቻሉም።

” እንነጋገር፤ ትግራይ ሄደን ተወያይተን እስክንመለስ ጠብቁን” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም የተቅላይ ሚኒስትሩ ፍጥነት ያንን እድል የሚሰጥ ባለመሆኑ ሲንቀራፈፉ የተቃዋሚ ፓርቲ ማዕረግ ተሸክመው ቀሩ። በዚሁ ውዝግብ ይኸው ዛሬ ድረስ አሉ። ይህ ውሳኔ ለመወሰን የመሰብሰብና ጊዜ የመውሰዱ የአርባ ዓመት ለምድ አኡአዋታም የሚሉ አሁን ብቅ ያሉትም በዚሁ መነሻ ሲሆን እነዚህ ክፍሎች ለዚህ የተንቀረፈፈ አሰራርና ተሸናፊነት የዳረጋቸው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር ጥገኛ መሆናቸው ያመጣባቸው ጣጣ በመሆኑ ይህ እምነት መቀየርና ባልተንዛዛ አሰራር ውሳኔና አቋም መያዝ የሚያስችል ነጻ ስርዓት መተከል አለበት እያሉ ነው።

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

” የድርጅታችን የአብዮታዊ ዴሞክራሲን መስመር ተካደ” በሚል ብልጽግናንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲከሱ ከነበሩት መካከል ዛሬ ይህን የቀደመ ” እምነት” እንቀይር የሚሉ ወገኖች የመውጣታቸው ዜና ውስጥ ውስጡን እየተብላላ ቢሆንም፣ ውስጥ አዋቂው እንደሚሉት ይህን ሃሳብ የሚያራምዱት ወገኖች ” በዚህ መልኩ መቀጠል የለብንም። ወደ ፌደራሉ ሲስተም ባስቸኳይ መመልስ አለብን” የሚሉት ክፍሎች በገሃድ ሚና ለይተው የሚወጡበት ሰዓት ደርሷል።

” መቶ በመቶ እርግጠኛ ነን” ሲሉ ምንጩ እንደሚናገሩት “ህወሃት ምርጫ አያካሂድም። የአገር ምስረታ የሚሉትም የፖለቲካ ውጥረት ለመፍጠር ነው። አብዮእታዊ ዴሞክራሲን እንስቀለው የሚሉት ሃይሎች በቅርቡ ይፋ የሆናሉ” ብለዋል። እነማን እንደሆኑ እንዲያስረዱ ተጠይቀው ” እነዴት ወደ መቀሌ እንደመጣሁ አይገባኝም” ሲሉ የተናገሩት ስብሃት ነጋና የዶክተር ደብረጽዮን ቡድን የዚህ ሃሳብ አቀንቃኝ መሆናቸውን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

የእነ ጌታቸው አሰፋ አሰላለፍ ወደ አገር ምስረታ መሄድ ቢሆንም አሁን ወደ ፌደራል ምመለስ አለብን የሚሉት ወገኖች ያላቸው አንድ ፍርሃቻ ከተመቻቸላቸው ሳይውል ሳያድር ሃሳባቸውን ተጋባራዊ እንደሚያደርጉ ምንጩ አስረድተዋል። ፍራሃቻው ምን ይሆን በሚል ለተጠየቁት “ከነኘጮቹ ጋር እየተነጋገሩ ስለሆነ ወደፊት ይፋ ይሆናል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ላለፉት አርባ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ ማእከላዊነት ስም ኢህአዴግን አንቆ የያዘው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምንጩ እንዳሉ ይሰቀል ይሆን?

ይህ በንዲህ እንዳለ መንግስት የትግራይ ቴሌቪዥን ካሁን በሁዋላ አቋሙን አስተካክሎ ካልሄደ በውሰት የሚጠቀምበትን እድል እንደሚዘጋብት አስጠንቅቋል። የድምጸ ወያኔ መዘጋትን ተከትሎ ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የመጡ የህወሃት ባለስልጣኖች በግልጽ የተነጋርቸው ይህ ሲሆን ለበርካታ ሚዲያዎች ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥቷል።