“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኦነግ ሸኔና ህወሃት ከሃጫሉ ሁንዴ ግድያ ጀርባ መጠርጠራቸው ይፋ እየሆነ ነው!! በሽሬ የሻዕቢያ ተቃዋሚዎች ልምምድ

መንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የ«ኦነግ» ጦርና  ከምንግስትነት ወደ ተቃዋሚነት የተዛወረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ «ሕወሃት» ከሃጫሉ ግድያ ጀርባ አሉበት በሚል መጠርጠራቸውን  የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኤፒ ጥርጥር አለው እንጂ የኦሮሚያ ክልላልዊ መንግስት በይፋ ስም ጠርቶ ህወሃትን ከሷል። ኦነግንም ተጠያቂ አድርጓል። በሽሬ የሻዕቢያ ተቃዋሚዎች ልምምድ ላይ መሆናቸው ተሰማ።

በሟች የሞባይል ስልክ፣ ከጉዳዩ ጋር ተጠርጥረው የተያዙ እንዲሁም በተካሄዱ አጣዳፊ ምርመራዎች መረጃ መገኘቱን የመንግስት የተለያዩ ሃላፊዎች ፍንጭ ቢሰጡም ከታማኝ መረጃዎች መስማት እንደተቻለው የሃጫሉ ገዳዮች፣ አሰማሪዎች፣ እቅድ ነዳፊዎች፣ ከግድያው በሁዋላ ምንም እንደሚደረግ ታስቦ በቅንጅት እንዲሰራ ዲዛይን የነደፉት አካላት  በሙሉ ታውቀዋል።

” እቅዱ መገነቱ ሴራው በአስቸኳይ እንዲከሽፍ አግዟል” የሚሉት ክፍሎች መንግስት ሲራውን ከህዝብ ጋር ሆኖ ያከሸፈው በዚሁ መነሻ ቢሆንም አስቀድሞ በቂ ክትትል እያደረገ እንደነበርም ጠቁመዋል። መንግስት የፍርድ ሂደቱ እንደቀድሞው እንደማይጓተት ያስታወቀው ለዚሁ እንደሆነ ያመለከቱት ክፍሎች የምርመራው ሪፖርት ሲቀርብ ህዝብ ተዓምር እንደሚሰማ ገልሰዋል።

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

” ፊሽካ ገዝተን በመጠራራት ለዝርፊያ የመጡትን አባረናል” ስትል የሳሚት ነዋሪ እንደገለጸችው ወደ አካባቢው የመጡት ጭፍሮች የተደራጁ መሆናቸው ያስታውቃል። ዓላማው ግን ከዝርፊያ በዘለለ የገባቸው አይምመስልም።

ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በያዝነዉ ሳምንት በተቀሰቀሰዉ ግጭት 97 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ ሲል የጀረመን ድምጽ ይህንን ዘግቧል። ዐብይ ክስተቱን «የተቀናጀ ሙከራ » ማለታቸዉን የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬዚስ ዘግቦአል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ዉይይት ባደረጉበት ወቅት ሲሆን በሃገሪቱ ለነበረዉ ፀጥታ መደፍረስ ተጠያቂ የሚያደርጉት ማንን እንደሆን በግልጽ አልተናገሩም። በዉይይቱ መጨረሻ ላይ ግን፤ በኢትዮጵያ ለነበረዉ ረብሻ መቀስቀስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠያቄ የሆነ ሁሉ ሕግ ፊት ይቀርባሉ ማለታቸዉ ተዘግቦአል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ስብሰባ ላይ የጦር ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰዉ እንደነበር በብሔራዊ ቴሌቭዥን የተሰራጨዉ ዜና ያሳያል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ትናንት ይፋ ባደረጉት መግለጫ በፀጥታ ኃይላት እንዲሁም በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ97 ሰዎች ሕይወት ጠፍቶአል።

Related stories   ይናገር ደሴ -"እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም"

በተመሳሳይ ዜና የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ  በተነሱ ተቃውሞዎች ላይ በተፈጠሩ ግጭቶችና በደረሰው የንብረት ውድመት የተጠረጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን የሁለት ከተሞች ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ፖሊስ በድሬዳዋ 272 ተጠርጣሪዎችን ማሰሩን አስታውቋል።በሐረር ደግሞ 17 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።በሐረር የተያዙት ሰዎች ቁጥር በከተማዋ ከደረሰው ጥፋት ጋር የሚመጣጠን አይደለም እየተባለ ነው። ከሃጫሉ ግድያ በኋላ ውጥረት ሰፍኖባት የቆየችው የድሬዳዋም ሆነ ሃረር አሁን ወደ ቀድሞው እንቅስቅሴያቸው እየተመለሱ መሆኑም ታውቋል።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

በትግራይ ክልል ድንበር በስደት ወደ መጠለያ ካምፕ የፈለሱ የኤርትራ ስደተኞችን ሽሬ ላይ እያሰለጠነ መሆኑ ተሰምቷል። የኤርትራ አክቲቪስቶች እንደሚሉት የአገራቸው መንግስት ሙሉ መረጃ አለው። ይሁን እንጂ አድሮ በትግራይና በኤርትራ ድንበር አካባቢ ውጥረቱን ሊያባብስ ያባብሰዋል። ትግራይን ህዝብ ሳይፈቅድ አገር አደርጋለሁ የሚለው ህወሃት ከመሃል አገርና ከኤርትራ ጋር በእኩል ሰዓት ችግር ውስጥ እንዳይወድቅ በትግራይ አክቲቪስቶች በኩልም ቅስቀሳውና ውትወታው ከፍተኛ ነው። በሁለቱ አገሮች መካከል ድንበር ላይ ያለው የአገር መከለከያ ሰራዊት የሚታዘዘው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲሆን ሰሞኑንና ቀደም ሲል አመራሮች መለዋወጣቸው የሚታወስ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0