የትግራይ ቴሌቪዥን እና የድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን ስርጭት ከአየር መውረዱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ከበርካታ ማስተንቀቂያ በሁዋላ ምንም መሻሻል ባለማየቱና ይልቁኑም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያነሳሳ ዘመቻቸውን አጠናክረው በመቀጠላቸው ነው። የድምጸ ዋይኔ የአዲስ አበባ ሃላፊ ከቀናት በፊት ምንም የደረሰን ማስጠንቀቂያ የለም ሲሉ አስተባብለው ነበር።

የስርጭቶቹ መዘጋት ተከትሎ ቻናል 29 የሚሰኝ በሙከራ ላይ ያለ የቴሌቪዥን ጣቢያ መንግስት ከሳተላይት ባወረደው ምትክ ሆኖ እንደሚሰራ ማስታወቂያ እያሰማ መሆኑን የጀርመን ሬዲዮ ዘግቧል። የዲደብሊው የአዲስ አበባ ዘጋቢ ይህንን ቢልም ስርጭቱ ከየት አገር እንደሚተላለፍ አልገለጸም። ” ይህ ቻናል 29 ከዚህ ቀደም የሙከራ ስርጭት ያካሂድ እንደነበረ እና መቀመጫው የት እንደሆነ እንደማይታወቅ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሔር ዘግቦልናል” ሲል ነው ዘገባውን የቋጨው።

Related stories   የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ - ቅንጅት "በተጭበረበረ ተግባር"እንዲሰረዝ ተወስኗል

የትግራይ ቴሌቪዥንና የወያኔ ድምጽ በብሮድካስት ኤጀንሲ ውሳኔ መዘጋታቸውን አስመልክቶ ህወሃት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ቀደም ብሎ ግን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት እያገለገሉ ነው ባላቸው ሶስት የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይ ምርመራ እንደጀመረ ይፋ አድርጎ ነበር።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *